דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ

በ: ዳቲያ ቤን ዶር ምሳሌዎች: ዓናት ሐኒት

በዝናብ ውስጥ መራመድ እንዴት አስደሳች ነው፤ ዣንጥላ የሌለው ሰው ግን ምን ያደርጋል? - የታወቀውና የተወደደው የልጆች ዘፈን ዣንጥላ ስላላት አንዲት ልጅ ይተርካል። እርሷን እንዲቀላቀል የሚፈልግን ሁሉ እየጋበዘች አብሮ ጉዞ ማድረግ ምን ያክል የበለጠ አስደሳች እንደሆነ ትገልጣለች።

የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች

ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

በዝናብ ውስጥ የሚደረግ ጥሩ የእግር ጉዞ በዳቲያ ቤን ዶር ተወዳጅ ግጥም ውስጥ እንደ ጓደኝነት ምልክት ይሆናል። በዣንጥላው ስር ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ አለ። ማንም ሰው እርጥብ ሆኖ አይቆይም። በቀላል ጊዜያት እንደ ድንገት ዝናብ መዝነብ ሲጀምር ወይም በጓሮው ውስጥ እየተጫወቱ እያሉ ለሌሎች ርህራሄ የመስጠትና የልብ ጡንቻዎችን የማሰልጠን እድሉ አንዳንዴ ይገለጣል። ምክንያቱም እኛ ሁልጊዜ “ቦታ አለን”

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

קרדיט: ערוץ כאן חינוכית - שירים וסיפורים | מתוך התוכנית פרפר נחמד

ማተሚያ ቤት:

מודן

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025