ቲም ታም ወጣት ጥንዚዛ ስትሆን እስካሁን የራሷ የሆነ ነቁጥ የላትም። ነቁጦችን ለመፈለግ ከእናቷ ጋር ትወጣና በእያንዳንዱ ነጥብ ባገኘችው መጠን እያደገችና ትንሽ የበለጠ ነፃ እየሆነች ትሄዳለች። ልጆች ቀጣዩን ነጥብ ራሳቸው እንዲፈልጉ በሚጋብዙ ጥበባዊ ሥዕላዊ መግለጫዎች የታጀበ ስለ ማደግና ስለ ነፃነት የሚያሳይ አዲስ መጽሐፍ።
የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች
ቲም ታም የተባለች ልጅ ጥንዚዛ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጥቦችን ፍለጋ ትወጣለች – የእድገት ጉዞ ላይ ትወጣለች። እናቷ ቲም ታም ብቻዋን ነጥቦችን ማግኘት እስክትችል ድረስ ታስተምራታለች። ታዳጊዎች ነጻነታቸውን ለማወቅ የመጀመሪያ እርምጃዎችን በመውሰድ ከቲም ታም ጋር መለየት ይችላሉ፦ እርሷም ችሎታዋን ለማዎቅ ትማራለች፤ ታዳብራለች። ከመጽሐፉ ጋር ያሉት ልዩ ሥዕላዊ መግለጫዎችን እንድንፈልግና ትኩረት እንድንሰጥም ይጋብዙናል።
ሰማይ ላይ እደግ ብሎ መታ የሚያደርገው እድል የሌለው ሳርና አረም የለም!
[ብሬሺት ራባ 10፡6]
ማተሚያ ቤት:
עם עובד
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ה 2024-2025