በድንገት አንድ ትልቅ አዞ ባቡሩ ውስጥ ይገባና ማንንም ሳያስብ ሙሉ ጋሪ ለራሱ ይወስዳል። ወደ እርሱ ለመቅረብ ማን ይደፍር ይሆን? አዞውስ በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ግምት ውስጥ ለማስገባት ይስማማ ይሆን? - ስለ ጭፍን ጥላቻና ለሌሎች አሳቢነት የሚይሳይ መጽሐፍ።
የእድሜ ክልል: ቅድመ ትምህርት ቤት
ለአካባቢው የማያስብ ሰው እንዴት እናስጠነቅቀዋለን? ደስ የማይል ነገር ሊሆንና ወደ ግጭት ሊመራ ይችላል። አንድ አዞ በባቡር ውስጥ ገብቶ አንድ ሙሉ ሰረገላ ለራሱ ሲወስድ የተናደዱ ግን የፈሩ ተሳፋሪዎች ሊያስጠነቅቁት አልደፍሩም። በእውነት ትንሿ ጫጩት ናት ድፍረትን ሰብስባ ከእምነት የተነሣ ያለአንዳች ጭፍን ጥላቻ ወደ አዞው የቀረበችው። ጫጩቷ በራሷ መንገድ የምታስተምረን አንዳንድ ጊዜ መድፈርና ከልብ ወደ ልብ መናገር ብቻ አስፈላጊ እንደሆነ ነው።
“የባልንጀራህ ክብር እንደራስህ ውድ ይሁን”
(ሚሽና፣ ማሴኼት አቮት – ምዕራፍ 2፣ ሚሽና 10)
ማተሚያ ቤት:
ספרית פועלים
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ה 2024-2025