דילוג לתוכן המרכזי בעמוד
የወሩ መጽሐፍ

ድመት ውሻ አይደለም!


በ: ሾሻና ካርባሲ ምሳሌዎች: ራሔል ስቶርሎ ሐይም

አንድ ልጅ ውሻ ይፈልጋል። ግን ድመትን በስጦታ ይቀበላል። ድመቷ እንደ ውሻ አይጮኽም፣ ሲታዘዝ አይቀመጥም፣ ኳስ አያመጣም። ምክንያቱም ድመት ውሻ አይደለም። ግን ... ያም ሆኖ ምናልባት ከልጁ ጋር ሊስማማ ይችል ይሆን? ስለ ተስፋዎች፣ ብስጭቶችና አንዳንድ ጊዜ በትክክል ያልፈለግነው ነገር ለእኛ ምርጥ ነገር ሆኖ እንዴት እንደሚሆን የሚናገር አስደሳች ታሪክ።

የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች

የመጽሐፉ ጀግና ውሻ ፈልጎ ነበር። ነገር ግን ይልቁንስ ድመት ያገኛል። ከሚፈልጉት የተለየ ነገር ሲያገኙ ምን ይሆናል? አንዳንድ ጊዜ ብስጭት ወይም ንዴት ያጋጥምዎታል። አንዳንድ ጊዜ ከዚህ በፊት የማይወዱትን መውደድ ይማራሉ። በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ ድመቱ ውሻ አለመሆኑን ሲያይ በጣም ባዘነበትና በተበሳጨበት ወቅት ከእርሱ “እንደ … መሳም ዓይነት ጣፋጭ መሳም”ን ያገኝና በእርሱ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ለማየት ችሏልና አንዳንድ ጊዜ ብስጭት እንኳን ወደ ፍቅር ሊለወጥ እንደሚችል አውቋል።

“ይህም ለበጎ ነው” ማለትን አሩ ይልመድ።”
(ኦርሖት ጻዲኪም፣ ሻዓር ሃሢምሐ)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

קרדיט: חוה אלברשטיין

ማተሚያ ቤት:

הקיבוץ המאוחד

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025