የመጽሐፉ ጀግና የሆነችው ያስሚን ከአባቷ ጋር መጫወትና "እንደ ትልልቆቹ" ዓይነት ዓለምን መፍጠር ትወዳለች። የጋራ ጨዋታው ታዳጊ ሕጻናቱ ስሜትን እንዲገልጹ፣ ሚናዎችን እንዲቀያይሩ፣ እንዲዝናኑ፣ እንዲስቁና በራስ መተማመንን እንዲያጠናክሩ ያስችላቸዋል። ጨዋታው ወላጁ ወደ ታዳጊው ዓለም እንዲቀርብና ለአፍታም ቢሆን ራሱ እንደገና ልጅ እንዲሆን ያስችለዋል።
የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች
ልጅን እንደ መንገዱ አስተምረው
(ምሳሌ 22 6)
“እንደገና!” – ታዳጊ ሕጻናቱ በመጽሐፉ ከተደሰቱ እንደገና ማንበብ አለብዎት። ተደጋጋሚ ንባብ ታዳጊዎችን አስደሳች ልምዶችን እንደአዲስ እንዲያዩ ያስችላቸዋል (“እንደገና” የሚለውን ሁለት ጊዜ ላለመድገም)። ይህ ደግሞ አዳዲስ ቃላትን የሚማሩበት፣ ከሁኔታዎችና ስሜቶች ጋርም በጥልቀት የሚተዋወቁበት መንገድ ነው (በቀደመው አንቀፅ ላይ የታየ ነው) – የታሪኩ መጨረሻ አስቀድሞ የሚታወቅ ነውና።
የተሰራጩት ቅጂዎች:
23,100
ማተሚያ ቤት:
מודן
የስርጭት ዓመት:
ታሽፓግ 2022-2023