דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ספר החודש

በጣም አስደናቂው ነገር

በ: ኤሽሊ ስፓይረስ ምሳሌዎች: ኤሽሊ ስፓይረስ

እየሞከሩ አለመሳካት ተስፋ አስቆራጭ ነው። ነገር ግን በታሪኩ ውስጥ ያለችው ልጅ ተስፋ አትቆርጥም። ምንም እድል የሌለው ቢመስልም የምታስበውን አስደናቂ ነገር ለመገንባት ደጋግማ ትሞክራለች። በራእይና በእውነታው መካከል ስላለው ክፍተት፣ ስለ ቆራጥነት፣ ታታሪነትና ጥሩ መንፈስ ላይ የሚያሳይ ፈጠራዊና ስሜታዊ ታሪክ።

የእድሜ ክልል: ሁለተኛ ክፍል

አንዲት ልጅና ረዳቷ ሊታሰብ የሚችል እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነውን ነገር ለመገንባት ይሞክራሉ። ነገር ግን ምናብና እውነታው አንዳቸው ከሌላው በጣም የራቁ ናቸው። በጣም አስደናቂው ነገር መንገዱ ቀላል አይደለም፦ እቅድ ማውጣትን፣ ሙከራንና ስህተትን፣ እልኽ አስጨራሽና ብዙ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያካትታል። ልክ በሕይወት ውስጥ ሁለቱ ፍጹምነት የጎደለው ነገር ሊሆን እንደሚችል ይማራሉ – አስደናቂ!

የምትወድቀው መሞከር ስታቆም ብቻ ነው።
(አልበርት አንስታይን)

ማተሚያ ቤት:

כנפיים וכתר

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025