דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ቀጣዩ ተረኛ

በ: ኤፈርት ሌቪ ምሳሌዎች: ጌፌን ራፋኤል

ከሐኪሙ በር ውጭ ወረፋው ረዥም ነው - ዝንጀሮ፣ ዝሆን፣ አዞና ቀጭኔ እየጠበቁ ነው። መጀመሪያ ማን እንደሚገባው እንዴት ይወስናሉ? ቀጣዩ ተረኛ ስለ ትዕግስት፣ ሌሎችን ስለመርዳትና ሌሎችን ስለማሰብ የሚያሳይ ታሪክ ነው።

የእድሜ ክልል: መዋዕለ ሕጻናት

ተሰልፎ መጠበቅ በጣም የሚያበሳጭ ነገር ሊሆን ይችላል። ኮፊፍ ወደ ክሊኒኩ ሲደርስና የመጨረሻውን ቁጥር ሲቀበል የተሰማው እንደዚህ ነው። እርሱና እንደ እርሱ እያንዳንዱና እያንዳንዷ ወረፋ የሚጠብቁት ጉዳያቸው ከሁሉም የበለጠ አስቸኳይ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በመጠባበቅ ላይ እያሉ የገቢዎቹን ቅደም ተከተል የሚወስነው ምን እንደሆነ አብረው ለማወቅ ይሞክራሉ። ስለዚህ ሳይታወቃቸው መተዋወቅና መግባባት በመካከላቸው ይፈጠራል። ጣፋጭ በሆነና በሚማርክ ታሪክ አንባቢዎች ወረፋ መጠበቅ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም እንኳን ለርህራሄ፣ መተሰሰብና ሌላውን ማየት ለሚያስችሉ ግንኙነቶች መክፈቻ እድል እንደሆነ ይገነዘባሉ።

“አንድ ሰው በጓደኛው ፊት ተቀምጦ ችግሩን ሲያጋራ… ቀኙን በቀኙ ግራውን በግራው አድርጎ በመስታወት ራሱን እንደሚያየው … ሊያየው ተገቢ ነው። ራስህን አይተሃል እንደማለት ነው”
(ከ“ጻዲክ ይሶድ ዖላም” ከተሰኘው የራቢ አርዬ ሌቪን ጽሁፍ ገጽ 426)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

כנרת

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025