דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ጥንቸል በባቡር ላይ ተቀምጣለች

በ: ቶቫ ሺንበርግ ምሳሌዎች: ኦራ አይል

አንዲት ልጅ የባቡር ወንበሮችን ረድፍ ትለውጣለች፤ እርሷንም በምናባዊ ጉዞ ላይ አሻንጉሊት፣ ጥንቸል፣ ቴዲ ድብና ሁለት ድመቶች ተቀላቅለዋታል። በግጥሞችና ድምጾች በተሞላ ታሪክ ውስጥ አንባቢዎች ጉዞውን እንዲቀላቀሉና በመስኮቱ ላይ የሚታየውን እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል- ተራራ፣ ባህር፣ ዛፍ፣ የአትክልት ስፍራና ሌላስ?

የእድሜ ክልል: ጨቅላ ህፃናት

በባቡር ጉዞ ላይ ምን ከሰታል?

መጽሐፉ ህጻናትን በስርዓትና ዜማ፣ ግጥሞችና ድምፆች እንዲሁም የሚነሱና የሚወድቁ ገፀ-ባህሪያት ያለው አስደሳችና አስደናቂ ጉዞን ያስቃኛል። ባቡሩ የተወደደውን “ቱ ቱ ቱ” የሚል ድምጽ ያሰማና በእርሱ አማካኝነት ተራራ፣ ባህር፣ ድመትና ቢራቢሮ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ። ታዳጊዎች በየቀኑ ጉዞዎች ይሄዳሉ – ወደ መዋእለ ሕጻናት መንገድ፣ በመኪና ውስጥ፣ በአካባቢው በእግር ጉዞና በቤት ውስጥም ጭምር። በዙሪያቸው ያለውን ዓለም መመልከትና አጠገባቸው ካሉ አዋቂዎች ጋር ስለ እርሱ መማር ያስደስታቸዋል።

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

የተሰራጩት ቅጂዎች:

23,100

ማተሚያ ቤት:

הקיבוץ המאוחד

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024, ታሽፓግ 2022-2023