דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ታሪክ ይስሙ

በ: ሻሓር ሲትነር ምሳሌዎች: አሲያ አንስታይን

ሻሐር በእርሷ ላይ ስለሚደርሱት ልዩ የሆኑ ነገሮች ለጓደኞቿ መንገር ትወዳለች፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ትንሽ ታጋንነዋለች። ልጆቹ "ውሸታም" ብለው ሲጠሯት ከትምህርት ቤቱ ጽዳት ሄርጼል ጋር ለመነጋገር ትሄዳለች። ሄርጼል በውሸትና በተረት መካከል ያለውን ልዩነት እንድትረዳ ያግዛታል። ለእርሱ ምስጋና ይግባውና ታሪኮችን መናገር የምትቀጥልበት ቀላልና አስደናቂ መንገድን አግኝታለች።

የእድሜ ክልል: ሁለተኛ ክፍል

ሻሐር በሕይወቷ ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ክስተት ወደ አስደናቂ ታሪክ ትለውጣለች። ጓደኞቿ ሲያዳምጧት ደስተኛ ትሆናለች። ነገር ግን ለምን በድንገት እንደሚናደዱ ለመረዳት ይከብዳታል። ታድያ እርሷ ከዓሣ ይልቅ ሻርክ ብትለውስ? እርሷ ታሪኩ አስደሳች እንዲሆን ብቻ ፈለገች! ጥበቃው ሄርጼል የሻሐርን ታሪኮችና ችግሮች ያዳምጣል፤ የፈጠራ መፍትሔንም እንድታገኝ ይረዳታል። እንደ ሻሐር ሁሉ ልጆች ሁሉ የሚያዳምጣቸው፣ የልባቸውን ሐሳብ የሚረዳና ታሪካቸውን እንዲናገሩ የሚረዳ አዋቂ ያስፈልጋቸዋል። “ሕፃኑ በባዕድ አገር እንግዳ ነው። ቋንቋውን አይረዳም… ሕግና ወግ የማያውቅ… መሪ ያስፈልገዋል። ጥያቄውን በትሕትና የሚመልስለት፣ ላለማዎቁ ክብር… ለውድቀቱና ለእንባው ክብር”
[ያኖሽ ኮርቻክ “የክብር ልጅነት”፣ ገጽ 365-366 የቤት ሎሐሜ ሃጌታኦት ሙዚየም]

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

ספרית פועלים

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024