דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ספר החודש

ጸብከመጥረጊያጋር

በ: ዖዴድ ቦርላ ምሳሌዎች: ያኒብ ሺምዖኒ

ከሁሉም ሰው ጋር ስለሚጣላ ልጅ፦ ከልጆች፣ ከእንስሳትና ከእቃዎች ጋር እንኳን ሳይቀር። አንድ ቀን ከመጥረጊያ ጋር መጣላት ጀመረ፤ ይሄንን ተአምር እዩ እስኪ - መጥረጊያው ምላሽ ይሰጣል፤ ግዳጅ ውስጥ ሳይገባ ይቀራል! ታሪኩ በቀላልና በሚያዝናና መልክ በጸብ ጊዜ የልጆችን ስሜት በመግለጽ ምንም እንኳን ሁሉንም ነገር ሁል ጊዜ ማስተካከል እንደሚቻል ያስታውሰናል።

የእድሜ ክልል: ቅድመ ትምህርት ቤት

“ቁጣ፣ ደስታ፣ ሳቅና ብስጭት – ወንድና ሴት ልጆች በቀን ውስጥ በብዙ ስሜቶች ይጥለቀለቃሉ። በተናደዱ ጊዜ, በሙሉ ልባቸው ይናደዳሉ። ደስተኛ ሲሆኑም ደስታቸው ታላቅ ይሆናል። “”ጸብ ከመጥረጊያ ጋር”” የሚለው መጽሐፍ ልጆች ስሜታቸውን በፈገግታ መመልከት እንዲችሉና ሁሉም ሰው እንደነርሱ ደስ የማይል ስሜቶችን እንደሚሰማቸውና በቀልድ እገዛ እንዴት እነርሱን መቋቋም እንደሚችሉ ለመረዳት ያስችላቸዋል።

አንዳንድ ጊዜ – አስደናቂ ነገሮች ይገጥሙኛል
አንዳንድ ጊዜ – በጣም መጥፎ ነገሮችም ይከሰታሉ
አንዳንድ ጊዜ – ጥሩ ይሆናል
አንዳንድ ጊዜ – ደስ ያሰኛል
አንዳንድ ጊዜ – ያበሳጫል – ግን አንዳንድ ጊዜ ብቻ።
[“”አንዳንድ ጊዜ””፣ ዖዴድ ቦርላ፣ ከ””መዝሙሮች ከትኼሌት ባዳሽ አበባ ጋር”” የተወሰደ፣ አርታዒ፦ ሐኒ ባርካት፣ የዳኒ መጻህፍት 2008]

ዖዴድ ቦርላ (1915–2009) – እስራኤላዊ ደራሲ፣ ገጣሚና ሠዓሊ ሲሆን ብዙ የህፃናት መጽሃፎችን የጻፈና የሳለ ነው። የቦርላ መጻህፍት በቀልድ፣ ምክንያት አልባና አዝናኝ ቃላት የተሞሉ ናቸው።”

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

קליפ מתוך ארכיון התאגיד. חני נחמיאס, עוזי חיטמן ואבי יקיר - המטאטא - באדיבות כאן מוזיקה

ማተሚያ ቤት:

המבוך

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ד 2023-2024