አንድ ትንሽ ልጅ ወደ መዋእለ ህጻናት እየሄደ ሲሆን በዚህ በጣም ደስተኛ ነው። እርሱ መንገዱን ከሚያቋርጡ ሰዎች ሁሉ ጋር በኩራት ይሳተፋል- ዶሮ፣ ድመት፣ ወፍና ቢራቢሮ። ሁሉም ሰው በተሳካለት ጉዞ እንኳን ደስ ያለህ ይሉታል። ወደ መዋእለ ህጻናትና ወደ አዲሱ ቀን በሚወስደው መንገድ ላይ ከልጁ ጋር አብሮ የሚሄድ ክላሲካል።
የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች
አዲስ ቀን መጀመር
ጥዋት መጥቷል፤ አዲስ ቀን ይጀምራል። ከቤት በመለየት መውጣትና ወደ ሕጻናት ማቆያ መግባት መላመድን የሚጠይቅ በዓመቱ መጀመሪያ ላይና በአጠቃላይም ፈታኝ ሊሆን ይችላል። በመጽሃፉ ላይ ያለው ትንሽ ልጅ ሽግግሩን የሚያቃልል “እንደምን አደራችሁ”ን ስነ ስርዓት ያከናውናል። አካባቢውን ይከታተላል፤ የሚያገኛቸውንም ሁሉ መልካም የጠዋት ሰላምታን ይሰጣል። በዚህም ቀኑን በደስታ ለመጀመር ማበረታቻና በራስ መተማመንን ያገኛል። “ማለዳው ለተግባራዊ ታሪክ፣ ከውሻ ጋር ለመነጋገር፣ ኳስ ለመያዝና ሁሉም በጥሩ ዓይን የሚታይበት ጊዜ ነው” ያኖሽ ኮርቻክ “የክብር ልጅነት”፣ ገጽ 239 የቤት ሎሐሜ ሃጌታኦት ሙዚየም]
ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ
ማተሚያ ቤት:
ספר לכל
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ד 2023-2024