תרבות עברית
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ማቆየት
ውይይት - መምረጥና ማዋል
ስለ ሲሪልና ጦብያ ምርጫ መወያየት ተገቢ ነው- በእርስዎ አስተያየት ለምን ሁሉንም ወርቅ ላለመጠቀም የመረጡ ይመስልዎታል? አስገርሞዎታል? በእርስዎ አስተያየት ለምን ወርቁን በትምህርት ላይ ለማዋል መረጡ?
ማቆየት
ስዕላዊ መግለጫዎች– ፍየሏ የት አለች?
ፍየሏ በሙሉ ታሪኩ ውስጥ ከሲሪልና ጦብያ ጋር አብራ ትሄዳለች። በመጽሐፉ ስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ፍየሏን መፈለግ ይችላሉ፦ ምን እየሰራች ነው? ከቤተሰብ ጋር ያላት ግንኙነት ምን ይመስላል? ከፍየሏ እይታ አንጻር ታሪኩን ለመናገር ይሞክሩ – በመጽሃፉ ውስጥ ምን ይገጥማታል?
ማቆየት
ጨዋታ– ሃብቱን መፈለግ
ለቤተሰብ አባላት መስጠት የሚፈልጓቸውን ትንንሽ ስጦታዎች ይሰብስቡ፦ ስዕል፣ ቡራኬ ወይም እቃ። በተራው መሰረት ከቤቱ አባላት አንዱ የራሱን ስጦታ ይደብቃል። ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም ሀብቱን በምልክቶች ይፈልጉታል፡- “ቅርብ-ሩቅ”፣ “ትኩስ-ቀዝቃዛ” ወይም በቤቱ ዙሪያ የተበታተኑ ቀስቶች።
ማቆየት
ታሪኩን መስማት
ታሪኩን መስማት
የQR ኮዱን ስካን ማድረግ ወደ ታሪኩ ማጀቢያ ይመራዎታል። አብረው በቤት ውስጥ፣ በጉዞ ላይ ወይም በማንኛውም በሚመርጡት ቦታና ጊዜ ማዳመጥ ይችላሉ።