סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ውይይት፦ ቀዳዳዎች በመርከቧ ውስጥ
ልክ እንደ ሽላፍኖቼዎቹ መርከብ በቤት ውስጥም አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ወይም ‘ጥፋቶች’ አሉ። መፍትሔው የጋራ ጥረት ይጠይቃል። ታሪኩን በመከተል በጋራ መነጋገርና ማሰብ ይችላሉ፦ በየትኞቹ ሁኔታዎች በቤተሰብ ውስጥ አንድን ሀሳብ ወይም መፍትሔ ማሰብ አለብን? የጋራ ጥረት መቼ ያስፈልጋል? መቼ ነው ችግር እንዳለ ተረድተን ነገር ግን መፍትሔ ለማግኘት ጥረት ሳናደርግ ስለ ጉዳዩ ብቻ የምንነጋገርበት ሁኔታ መቼ ይከሠታል? በእነዚህ አጋጣሚዎችስ የትኛው ‘ወፍ’ ሊያድነን ይችላል?
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
ቤተሰባዊ የሆነ ፈታኝ ነገር
በታሪኩ መጨረሻ ላይ በቂ መፍትሔ በማይኖርበት ጊዜ “አራቱ ሽላፍኖቼዎች በአንድ ትንሽ ቁም ሳጥን ላይ” ይሰበሰባሉ። እንዲሁም ለመዝናናትና ለመፈተሽ መሞከር ይችላሉ – ስንት የቤተሰብ አባላት በአንድ ትንሽ ምንጣፍ ላይ መሰብሰብ ይችላሉ? በመጋሊቦሽ ላይስ? ወይም በመረጡት ሌላ ቦታ ላይ። አንድ ላይ ለማሰብ ይሞክሩና በዚህ ፈታኝ ነገር ውስጥ የሚረዱዎትን የፈጠራ ሀሳቦችንና መፍትሔዎችን ያቅርቡ።
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
አስቂኝ ስሞች ያሏቸውን ፍጡሮች መፍጠር
ሽላፍኖቼ ምን አይነት አስቂኝ ስም ነው? ለእንደዚህ አይነት ተጨማሪ አስቂኝ ስሞች ሀሳብ አለዎት?
ሃምቡልባሊኖስ? ሃሽቱቲፑሎች? የእራስዎን ምናባዊና አስቂኝ ፍጥረታትን አንድ ላይ መፍጠር የሚችሉ ሲሆን በዓይነ ሕሊናዎ በመሳል ቀለም ይስጧቸውና ለእነርሱ ረዥምና አስቂኝ ስም ይወስኑ።
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆኑ ምክሮች
ወንድና ሴት ልጆች ምስሎችን መመልከት ያስደስታቸዋል። በታሪኩ ውስጥ የማይታዩ ዝርዝሮች ላይም ትኩረት ይሰጣሉ። በማንበብ ጊዜ እነርሱን መቀላቀል አለብዎት። መጽሐፉን አብራችሁ በመመልከት ስዕሎቹ በጽሑፍ ለተጻፈው ጽሑፍና የጋራ የንባብ ልምድ እንዴት ደስታንና መዝናኛን እንደሚጨምሩ ይወቁ።
የሆነነገር
ሳያውቁ መቀላቀል
ውጤቱ ምን እንደሚሆን አስቀድመው ሳያውቁ ወደ አንድ እንቅስቃሴ ተቀላቅለው ያውቃሉ? ከልጆች ጋር እንደዚህ ያሉ የጋራ ጊዜዎችን ለማስታወስ ይሞክሩ – ለምሳሌ፦ ወደማይታወቅ መዳረሻ የቤተሰብ ጉዞ ያደረጉበት ወይም አዲስና ያልተለመደ ምግብ አብረው ያዘጋጁበት።
የሆነነገር
የሆነ አንድ ነገር!
ክብ ነገር ነው? አረንጓዴ የሆነ ነገር? ጥሩ ነገር? በቤተሰብ ፍንጭ ጨዋታ መደሰት ትችላላችሁ – እያንዳንዱ በተራው ስለ አንድ ነገር ያስባል። የተቀረው ቤተሰብ የመግለጫ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምን እንደሆነ ለመገመት ይሞክራል – “የሆነ ነገር” ምን እንደሆነ ለማወቅ ይችላሉ?
የሆነነገር
በጀምበር መዝናናት
በታሪኩ ውስጥ ያሉ ጓደኞች ከባህሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ጀንበር ስትጠልቅ በመመልከት ደስ ይላቸዋል – እርስዎም ወደ ባህር ዳርቻ ፣ ወደ መናፈሻ ወይም ወደ ጎዳና እንድትሄዱ ተጋብዘዋል ፣ እና ፀሐይ ስትጠፋ የሰማይ እይታ ይደሰቱ። እንዲሁም አንድ ገጽ እና ቀለሞችን ከእርስዎ ጋር ይውሰዱ እና የእራስዎን የፀሐይ መጥለቅ ወይም ሌሎች ዙሪያውን ብቻ ካዩ ሊያደንቋቸው የሚችሏቸውን ነገሮች አንድ ላይ ይሳሉ።
የሆነነገር
ውይይት - ቤታችን
ሁሉም ቤቶች በግድግዳዎችና በጣሪያ፣ በበሮችና በመስኮቶች የተገነቡ ናቸው፦ ስለ ቤትዎ ልዩ ነገር ምንድነው? የእናንተ የሚያደርገው ምኑ ነው? በቤትዎ ውስጥ ስላሉ ነገሮችና ልዩ እቃዎች ብሎም በቤት ውስጥ አብረው ስለሚሰሩ ነገሮች ማውራት ትችላላችሁ።
ቤት እንዴት ይገነባል
ቪዲዮ - ከሳጥኖች የተሠራ ቤት
በቤት ውስጥ ከሳጥኖች ምን ሊሰራ ይችላል? እውነተኛና ምናባዊ የሆነ የቤት ሀሳቦችን ለማግኘት የQR ኮዱን ስካን ያድርጉ።
ቤት እንዴት ይገነባል
ፈጠራ - ቤትን ማን ይሠራል?
ከብርድ ልብሶች፣ ከሣጥኖች፣ ከዱላዎችና ከልብስ መቆንጠጫዎች ለራስዎ ቤት መፍጠር ይችላሉ! ሌላስ ምን ያስፈልጋል? ቦታውንና የስራውን ደረጃ በመወሰን እቃዎችንና አጋዦችን ይሰብስቡና ጉዞ ያድርጉ።
ቤት እንዴት ይገነባል
ጨዋታ - የቤት ውስጥ ታግ
በእያንዳንዱ ዙር ከተሳታፊዎች አንዱ ርዕስን ያስታውቅና ሁሉም ተሳታፊዎች ተባብረው ተገቢውን ዕቃ መፈለግ አለባቸው፦ “ቀይ” ሲባል በቤቱ ውስጥ ያለ ቀይ እቃ ይፈልጉ። በሚቀጥለው ዙር ሌላ ተሳታፊ በፍለጋው ርዕስ ላይ ይወስናል፤ የተቀረው ደግሞ ፍለጋውን ይቀጥላል። ከማስታወቂያው ጋር የሚዛመዱ ነገሮችን መፈለግ ይችላሉ፦ “ትልቅ”፣ “ትንሽ”፣ “ቆንጆ”፣ “አሮጌ”፣ “በቀለም ያሸበረቀ”፣ “አናዳጅ” ወይም “ጎማ”።
ቤት እንዴት ይገነባል
ማንበብ እና ማቀፍ
ታሪክን እያነበቡ ሳለ አዲስ እንስሳ ቡድኑን በተቀላቀለ ቁጥር ማቀፍ ይችላሉ። የመተቃቀፍ ጨዋታውንም መጫወት ትችላላችሁ፡ እርስ በርሳችሁ ተራራቁ፡ “ሶስት፣ አራት” ቆጥራችሁ ከዚያ አንዳችሁ ወደ አንዳችሁ ሩጡና ተቃቀፉ!
ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ
የተጨናነቀ ነው ግን ያ ምንም አይደለም!
የተቀሩትን ቤተሰቦች ከእርስዎ ጋር ሶፋ ላይ፣ ምንጣፍ ላይ ወይም ፍራሽ ላይ አብረው እንዲቀመጡ ይጋብዙ። እንዲሁም አሻንጉሊቶችን ወይም የቤት እንስሳትን ማካተት ይችላሉ። አብራችሁ ተቀራርባችሁ ተቀመጡ፣ ከዚያ ራቅ ብላችሁ፣ እናም ያረጋግጡ፦ መቀራረቡ ምን ያህል አስደሳች ነው?
ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ
ምን አይነት ድምጽ ነው የምፈጥረው?
ውሻ እንዴት ብሎ ይጮኻል? ድመት እንዴት ብላ ትጮኻለች? እና ላም እንዴት ብላ ትጮኻለች?– ታዳጊዎች በታሪኩ ውስጥ ካሉ እንስሳት ጋር መቀላቀል ይችላሉ።
ሌላ እንስሳ ወደ ውስጥ ማምጣት ይፈልጋሉ? እና ያ እንስሳ ምን ድምጽ ያሰማል?
ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ
ስለ ጎመን ዘምሩ
“ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ (I sat on a cabbage)” የምትዘምሩት፣ እንቅስቃሴ የሚጨምሩበት፣ የሚዳንሱበት እና የምታጨበጭቡበት መዝሙር ነው።
ኮዱን ሲቃኙ ዘፈኑ ይሰቀላል፡-
QR – ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ – ኮዱን ይቃኙ እና አብረው ዘምሩ!
ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ
ጎመን ላይ ተቀምጫለሁ
ውይይት
ለልደትዎ የትኛውን ፍጹም ስጦታ ማግኘት ይፈልጋሉ? ካላገኙት ምን ይሰማዎታል? የሆነ ነገር በጣም ፈልገው ያውቃሉ ነገር ግን አልተቀበሉትም? ይህ መጽሐፍ የምንጠብቀውን እንድንወያይ ያነሳሳናል – ይህ ለምን ልዩ ስጦታ? የምር ይፈልጉታል ወይስ ሌላ ሰው እንዳለው ስላየን ዝም ብለን እንቀናለን? ስለ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች እና እነሱን እንድንቋቋም ስለሚረዱን ነገሮች መወያየት ይፈልጉ ይሆናል።
ፍጹሙ ስጦታ
ፍጹም ስጦታዎች
የራስዎን የቤተሰብ አባላት ምን ያህል ያውቃሉ፣ እና ለእነሱ ፍጹም ስጦታ የሚሆነው ምን ይመስልዎታል – የሚገዙት ነገር ወይስ የልምድ ስጦታ፣ ለምሳሌ፦ አብራችሁ የምታሳልፉት ጊዜ፣ ወይም ምናልባት የሆነ ቦታ የሚደረግ ጉዞ ነው? ጨዋታ ስለመጫወት እና ስለማወቅስ? በእያንዳንዱ ዙር፣ ሁሉም ተሳታፊዎች አንድ ተሳታፊ እንደ ስጦታ ምን ማግኘት እንደሚፈልግ ለመገመት ይሞክራሉ። ግምታቸው በጣም ቅርብ የሆኑት ያሸንፋሉ… ፍጹም የቤተሰብ እቅፍ።
ፍጹሙ ስጦታ
የሰው የመኪና ጨዋታ
መኪኖች ብቻ በገመድ ተያይዘው ይሽከረከራሉ ያለው ማነው? ሰዎችም ይችላሉ! ከእናንተ ሁለቱ የረጅም ገመድ ሁለቱን ጫፎች እርስ በርሳችሁ በግራ፣ በቀኝ፣ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት እየመራችሁ ልትይዙ ትችላላችሁ። ከደከምዎ፣ ትንሽ ያቁሙ እና እንደገና ይጀምሩ።
ፍጹሙ ስጦታ
የአብሮነት ጊዜ
“ከአባቴ ጋር መኪና ፍጹም ስጦታ ነው” እና ፍጹሙ ስጦታ ምን እንደሆነ ይገነዘባሉ? ከአባትዎ ወይም ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር እርስዎ ምን ማድረግ ይፈልጋሉ? የተበላሹ ነገሮችን ማስተካከል፣ የሆነ ነገር መገንባት ወይም መሰብሰብ፣ ወይም ምናልባት አንድ ላይ መሳል፣ መጋገር፣ መትከል ወይም መደነስ ይችላሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አብራችሁ ጊዜ እሰካሳለፋችሁ ድረስ፣ የሚፈልጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላሉ።
ፍጹሙ ስጦታ
Pinterest – ጥበቦች እና እደ-ጥበቦች እንዲሁም ሌሎች ተግባራት በ PJLibrary Pinterest ላይ ባለው The Perfect Gift ገጽ ላይ ይገኛሉ
ፍጹሙ ስጦታ
ውይይት - በአንድ ላይና በተናጠል
ብቻን ምን ማድረግ ይቻላል? አንድ ላይስ ምን ቢያደርጉ ይመረጣል? ከሌሎች ጋር መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ከልጆች ጋር መወያየትና ለራሳቸውም ምን ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስቡ አድርጉ። ከማን ጋር ነገሮችን በአንድ ላይ ማድረግ ይወዳሉ? የቤተሰብ አባላት? ጓደኞች? ምናልባትም የቤት እንስሳ?
በአንድ እግር ላይ
ጨዋታ - በአንድ እግር
እናንተም በአንድ እግር ላይ መቆም ትችላላችሁ? ኑ እንሞክረው!
የጨዋታ ሳጥንን ይጣሉ፣ በአንድ እግር ላይ ይቁሙና ከሳጥኑ በወጣው ቁጥር መሠረት መቁጠር ይጀምሩ፦ አንድ፣ ሁለት፣ እ … ሊወድቁ ነው? አጠገብዎ ከሚገኝ ሰው እጅዎትን በመዘርጋት እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።
በአንድ እግር ላይ
የስራ ተሳትፎ
በቤት ውስጥ በመተባበር ደስ የሚያሰኙና ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን ዝርዝር ማዘጋጀት ይችላሉ፦ ክፍሉን ማስተካከል፣ ምግብ ማዘጋጀት ወይም የሚወዱትን መጽሐፍ ማንበብ። ከዚያም እያንዳንዱን ድርጊት በተለየ ካርድ ላይ ይቅረጹና ያስጊጡት። ካርዶቹን በልዩ ሳጥን ውስጥ ማቆየትና በየቀኑ አንድ ካርድ በማውጣት መመርመር፦ ዛሬ ቤቱን በመጥረግ መተባበር እንፈልጋለን? ወይስ በሚስብ የቤተሰብ ጨዋታ? ምናልባት በአዲስ ነገር ላይ መተባበር እንፈልጋለን?
በአንድ እግር ላይ
እንቅስቃሴ - በአንድ ወይም በሁለት እግሮች ላይ
በቤት ውስጥ የእንቅስቃሴ መስመር ማዘጋጀትና በአንድ እግር፣ በሁለት እግሮች መገስገስና በአራትና በሦስት ላይ ራሱ … መሳብ ይችላሉ። ገመድ በመጠቀም ወለሉ ላይ መስመር ይፍጠሩና በእያንዳንዱ ጊዜ መስመሩን እያስረዘሙ ይራመዱ፦ አንድ ጊዜ በአንድ እግር ላይ በመዝለል፣ አንድ ጊዜ ትራስን ጭንቅላት ላይ በማድረግ ሚዛንን በመጠበቅ፣ አንድ ጊዜ በመሳብና አንድ ጊዜ ጥንድ በመሆን፣ እጆችን በማጣመር፤ ምክንያቱም በአንድ እግር ላይ ለሁለት መዝለል ስለሚቀልል ነው።
በአንድ እግር ላይ