שירה
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ቀለል ባሉና በግጥማዊ ታሪኮች ውስጥ እንኳን ጠቃሚና ትርጉም ያለው መልእክት ሊኖር ይችላል። መጽሐፉን ለውይይት ይጠቀሙበት። አስተያየትዎን በመግለጽ እንደ “በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ምን ይሰማዎታል ብለው ያስባሉ?” የሚሉ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።
የከዋክብቱ ዛፍ
“ደስታን ይጎናጸፉ...”
አያት ከኮከቦቹ ጋር በመመለሱ ደስተኛ ሲሆን ውድ ሀብት ብሎ በማሰብ ከገንዘብ የበለጠ ዋጋ እንዳላቸው ያስባል። ታሪኩን ተከትሎ ከልጆችዎ ጋር “ደስ የሚያሰኝዎትና በገንዘብ የማይገዙት?” ላይ ልጆችዎትን ይጠይቁ። ስዕል ይሳሉ? የመኝታ ታሪክ ጊዜ? ምናልባት ጥሩ የጠዋት እቅፍ ሊሆን ይችላል? እናንተ ወላጆች ማጋራት የምትችሉት – ሀብታችሁ ምንድን ነው?
የከዋክብቱ ዛፍ
ዛፎቻችን
የራስዎ ምናባዊ ዛፍ ቢኖራችሁ – በእርሱ ላይ ምን ይበቅላል? ልቦች? ፊኛዎች? ምናልባትስ ኮከቦች? ያሰቡትን ቅርጽ መሳልና መቁረጥ፣ ማስጌጥና በውስጡም ምኞትን ወይም የጋራ ትውስታዎችን መፃፍ ይችላሉ። ውጤቱ በአበባ ማስቀመጫ፣ በቅርንጫፍ ላይ ወይም በቤትዎ አቅራቢያ ባለው ዛፍ ላይ ሊሰቀል ይችላል።
የከዋክብቱ ዛፍ
ከዋክብትን መመልከት
እውነተኛ የኮከብ ዛፍ ላያገኙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ምሽት ላይ የእግር ጉዞ ለማድረግና በሰማይ ላይ የሚያበሩትን የከዋክብትን እይታ ማድነቅ ይችላሉ። መጽሐፉን ከእርስዎ ጋር ወስደህ በከዋክብት ስር አንድ ላይ ማንበብ ትችላለህ
የከዋክብቱ ዛፍ
መዝሙሩን ያዳምጡ፡-
ገጣሚ ላይብ ሞርገንቶይ 1905-1979 በፖላንድ በፒንስክ ከተማ የተወለደ ግጥሙን በዪዲሽ ቋንቋ በ1938 ደርሷል።በዮራም ታሄር ሌቭ ተተርጉሞ በኑሪት ሂርሽ የተቀናበረው በሐቫ ኤልበርትስታይን በ1969 ታትሟል።
ኮዱን ስካን ያድርጉና መዝሙሩን ያዳምጡ፡-
የከዋክብቱ ዛፍ
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምከር
በሥዕል የተደገፈ መጽሐፍ የሚሆን የተቀናበረ ግጥም አንባቢዎች በተለየ መንገድ እንዲለማመዱት፣ እንዲረዱት ወይም እንዲያውቁት ዕድል ይሰጣል። ስለዚህ ይህንን ዓይነት መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ስታነቡ “መጽሐፉን ለመዘመር” መሞከር የለብዎትም ነገር ግን ለሁሉም ነገር እንደ ታሪክ ሆኖ ያንብቡት።
ዓይን ሂሌል (1926-1990) ድንቅ የህፃናት መጽሃፍ ደራሲና ገጣሚ ተወልዶ ያደገው በኪቡዝ ሚሽማር ሀዔሜክ ነው። በሙያው የመዋእለ ህጻናት አርክቴክት ነበር። ነገር ግን ለትንንሽና ትልልቆች መዝሙሮችን መጻፍ ከሁሉም በላይ ይወድ ነበር። በእሥራኤል ውስጥ ካሉት አንጋፋ ሠዐሊዎች አንዱ የሆነው ዳቪድ ፖሎንስኪ ለፊልሞች አኒሜሽን ፈጥሯል፣ በብዙ ኤግዚቢሽኖች ላይ አሳይቷል፣ ሽልማቶችንና ዓለም አቀፍ እውቅና አግኝቷል።
ዛፎቹ ምን ያደርጋሉ
ጊዜው እንዲሁ ያልፋል
ጥያቄዎች ውይይትንና ሀሳብን ያበረታታሉ። በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ምሳሌዎች መመልከትና መጠየቅ ይችላሉ፦ ልጁ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ምን ያደርጋል? የመጽሐፉን መጀመሪያ እንዴት ይመለከታል? መጨረሻውንስ? በምስሎች ተመስጦ ካለፉት ጊዜያት ፎቶዎችዎን አንድ ላይ ማየት ይችላሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንዴት እንዳደጉ ይመልከቱና ጥያቄዎችን ይጠይቁ – የአንድ ዓመት ልጅ ሳለሁ ምን አደረግሁ? አሁንስ ምን አደርጋለሁ? ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምን አገኘሁ እና ተማርኩ?
ዛፎቹ ምን ያደርጋሉ
ምን እናድርግ?
የልብስ ማጠቢያ ማሽን ምን ያደርጋል? ጣሪያውስ ምን ያደርጋል? ታሪኩን ተከትለው በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በመራመድ በዙሪያዎ ስላዩዋቸው ነገሮች መጠየቅ ይችላሉ “ምን እያደረጉ ነው?”
ዛፎቹ ምን ያደርጋሉ
ዓለምን ማግኘት
መጽሐፉ የተለያዩና አዝናኝ መልሶች ያላቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉት። መጽሐፉ በጥልቀት እንዲያጤኑና አብረው እንዲመረምሩ ይጋብዝዎታል። ልጆችዎን መጠየቅ ይችላሉ – ዛፎቹ ሌላ ምን ያደርጋሉ? ደመናዎችስ ሌላ ምን ያደርጋሉ? እንዲሁም የራስዎን የጥያቄና መልስ መጽሐፍ በመያዝ በጋራ መስራት ይችላሉ። ይጻፏቸውና ይሳሉዋቸው እና ሌላ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር ወደ ታሪኩ ጨምረው መልሱን መፈለግ ይችላሉ።
ዛፎቹ ምን ያደርጋሉ
QR ኮድ
በጣም የታወቀውና የተወደደው የዓይን ሂሌል መዝሙር የተቀናበረው በኑኃሚን ሼሜር ሲሆን ቀድሞውኑ የእስራኤል ክላሲክ ሊሆን ችሏል። ለማዳመጥ ኮዱን ስካን ያድርጉ።
ዛፎቹ ምን ያደርጋሉ
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር የዓረፍተ ነገር ድግግሞሽ
ብዙዎቹ የህፃናት መፃህፍት ታዳጊዎቹ ታሪኩን እንዲከታተሉና በንባብ እንዲቀላቀሉ የሚረዳ ተደጋጋሚ ዓረፍተ ነገር አላቸው። በልዩ ድምጽ በመታገዝ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ወይም የንባብ ፍጥነትን በመቀየር በማንበብ ጊዜ የተደጋገመው ዓረፍተ ነገር አጽንዖት ሊሰጠው ይችላል። ለምሳሌ፡- “ከእኛ ጋር ና” ሲል የሚጋብዝ የእጅ ምልክት ማከል ወይም የዓረፍተ ነገሩን መጨረሻ ማራዘም ይችላሉ፦ “እኛም ዘንድ ቦ-ታ አለን”።
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
ጓደኞችን ማስተናገድ
በመጽሐፉ ውስጥ ያለችው ልጅ ልጆቹን ወደ ዣንጥላ እንዲመጡና ከእርሷ ዘንድ “እንዲስተናገዱ” ትጋብዛለች። ልጆቹን በቤታቸው ማስተናገድ እንደሚፈልጉና ማንን ማስተናገድ እንደሚፈልጉ መጠየቅ ይችላሉ።
ታዳጊዎች እቤት ውስጥ ሲያስተናግዱ አንዳንድ ጊዜ ጨዋታቸውን ማካፈል ይከብዳቸዋል። በዚህ ላይ ተወያይተው በመጽሐፉ ውስጥ እንዳለው ዣንጥላ ልጅቷ ወደ መጽሐፉ እንዲገቡ ስትጋብዝ የልጅቷ ሆኖ እንደሚቀረው ሁሉ የግል ንብረታቸውም የእነርሱ እንደሆነ ማስረዳት ይችላሉ።
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
የQR ኮድ
ከ”ደስ የሚል ቢራቢሮ” ፕሮግራም ላይ ዘፈኑን በካን ሒኖኺት ማዳመጥ ይችላሉ። ዘፈኑን በድምጽና በእንቅስቃሴ መቀላቀል ይችላሉ። ግጥምና ዜማ፦ ዳቲያ ቤን ዶር ኦፕሬተር፦ አስቴር ራዳ፣ ኡሪ ባናይ፣ ሜታል ራዝ፣ አሚ ዌይንበርግ።”
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
ቤተሰብና ዣንጥላ
በአንድ ዣንጥላ ስር ስንት የቤተሰብ አባላት ሊገቡ ይችላሉ? በብርድ ልብስስ ስር ምን ያህል? በመመገቢያ ጠረጴዛው ስርስ? በመፅሃፉ ተነሳሽነት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በደስታና በሳቅ እንዴት ሁላችሁ በጋራ መሰባሰብ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይችላሉ።
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
የዝናብ ላይ የእግር ጉዞ
ዝናባማ በሆነ ቀን ራስዎን በቦት ጫማዎች፣ ኮትና ዣንጥላ ያስታጥቁና በዝናብ ውስጥ ለመራመድ ይውጡ! ወደ ኩሬዎቹ ውስጥ ገብተህ በዝናብ ጊዜ በአካባቢው የሚለዋወጡትን ልዩ ነገሮች መመልከት ትችላለህ – ምን ያህል ሰዎች ውጪ አሉ? ሰማዩ ምን ይመስላል? ዝናቡ መሬት ወይም ንጣፍ ጋር ሲገናኝ ምን ይሆናል? በአየር ውስጥ ምን ሽታ አለ?
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
טיפ לקריאה
ከልማዶች፣ ምልክቶችና የበዓል ምግቦች ጋር የተያያዙ መፃህፍት የበዓሉን ልምድ የሚያበለጽጉት ሲሆን ለእርሱም መጠባበቅንና ጉጉትን ለማዳበር ይረዳሉ። በበዓል ወቅት ከልጆችዎ ጋር መጽሐፉን ማንበብ አለብዎት። ከዚያም በኋላ እንኳን – ውብ የሆኑትን ጊዜያት አንድ ላይ የሚያስታውሱ ዜማዎች፣ ቀለሞች፤ ጣዕምና ሽታዎች ይኖራሉ።
ልያ ናኦር በ1935 በሄርጼሊያ ተወለደች። ለህፃናት መጽሃፎችን፣ ድራማዎችን፣ ስክሪፕቶችንና መዝሙሮችን የደረሰች ሲሆን በርካታ መጽሃፎችን ወደ ዕብራይስጥ ተርጉማለች። ተከታታይ የሆነው “ዶክተር ሴውስ” ከእነርሱ ውስጥ ይጠቀሳል። መጻህፍቶቿና የትርጉም ስራዎቿ ብዙ ሽልማቶችን አሸንፈዋል።
ምን? ምን? ድንች!
ውይይት - በጋራ ማብሰልና መርካት
በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት ስለሚወዷቸው ምግቦችና ስለ ዝግጅቱ ሂደት ማውራት ይችላሉ – ምን ዓይነት ንጥረ ነገሮች ጥቅም ላይ ይውላሉ? በምን መሳሪያዎች? በእያንዳንዱ ደረጃ ምን እናደርጋለን?
ምን? ምን? ድንች!
የQR ኮድ
“ምን ምን? ድንች!” የሚለውን ዘፈን ያዳምጡ በመዝሙርና በዳንስ መቀላቀል ብሎም የራስዎን እንቅስቃሴ መፍጠር ይችላሉ።
ምን? ምን? ድንች!
ምስሎቹ ምንድን ናቸው?
በእያንዳንዱ ንባብ በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጹት ምስሎች ውስጥ አዲስ አስደሳች ዝርዝሮችን ይፈልጉ – በቀቀኑ የት አለ? በእያንዳንዱ ምስል ላይ ምን እያደረገ ነው? አባትየውና ልጆቹ ምን እያደረጉ ነው? በጠረጴዛው ላይ ምን ምን ዕቃዎችና ቁሳቁሶች አሉ? በኩሽና ውስጥ ምን ዓይነት ዕቃዎችን ያውቃሉ? ምናልባትም በቤትዎና በኩሽናዎ ውስጥ ሊያገኟቸው ይችሉ ይሆናል።
ምን? ምን? ድንች!
የፓን ኬክን የምግብ
የፓን ኬክን የምግብ አዘገጃጀት
ግብዓቶች፡-
5 ድንች
አንድ ትልቅ ቀይ ሽንኩርት
2 እንቁላል
ግማሽ ኩባያ ዱቄት
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ስኳር
አንድ የሻይ ማንኪያ ጨው
ለመጥበሻ የሚሆን ዘይት
የዝግጅት መመሪያዎች፡-
1. ቀይ ሽንኩርቱንና ድንቹን በድስት ውስጥ በመፈቅፈቅ ይላጡ። ፈሳሾቹን በደንብ በማሸት በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ያስቀምጡ
።
2. ሁሉንም ሌሎች ንጥረ ነገሮች ወደ ሳህኑ ውስጥ ይጨምሩ – እንቁላል፣ ዱቄት፣ ስኳርና ጨው (ከፈለጉም ተጨማሪ ቅመሞች) እና በደንብ ይደባልቁ።
3. በሁለቱም በኩል ወርቃማ እስኪሆን ድረስ ፓን ኬኩን ሞቅ ባለ ዘይት (አንድ ጭልፋ ወይም ጭልፋ ተኩል ለእያንዳንዱ ፍሬ) በጥንቃቄ ይጥበሱት።
4. በሚመጥ ወረቀት ላይ ያስቀምጡና መልካም ምግብ ይሁንልዎ!
ምን? ምን? ድንች!
ደረጃ በደረጃ
ፓን ኬክን ወይም ሌላ ተወዳጅ ምግብ በሚዘጋጅበት ጊዜ የዝግጅቱን ሂደት ፎቶግራፎች ማንሳት ይችላሉ። ከፎቶዎቹ ውስጥ ደረጃዎችንና የእርምጃዎችንና የንጥረ ነገሮችን ስም ለመድገም የሚረዳ ትንሽ አልበም መስራት ይችላሉ፦
ምን? ምን? ድንች!
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር- ልምድን ማጋራት
“ብዙ መጻህፍት የህፃናትን የእለት ተእለት ሕይወት ላይ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ይገልፃሉ፦ የማካፈል ችግር፣ የመሰናበት ችግር፣ ከቀን ወደ ማታ የመሸጋገር ፈተናና ሌሎች ብዙ። ታዳጊው ፈተና እየገጠመው መሆኑን ስትረዱ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ መጽሐፍ መርጣችሁ አብራችሁ አንብቡ። መጽሐፉ ስሜትንና ልምዶችን እንድታካፍሉ ይጋብዛል።
የመለ
ያ፣ የማበረታቻና የመቋቋሚያ ሃሳቦችን ማቅረብ ይችላል።
ሊያ ናኦር – በ1935 በሄርጼሊያ ተወለደች። ለህፃናት መጽሃፎችን፣ ድራማዎችን፣ ስክሪፕቶችንና መዝሙሮችን የጻፈች ሲሆን ብዙ መጽሃፎችን ወደ ዕብራይስጥም ተርጉማለች። ከእነርሱም መካከል ተከታታዩ “”ዶክተር ሱስ”” ይገኝበታል። መጽሐፎቿና ትርጉሞቿ ብዙ ሽልማቶችን አሸንፈዋል።”
ዓጋሮች
የእኔ ምንድን ነው የእኛስ ምንድን ነው?
ለእያንዳንዱ የየራሳቸው ከሆኑት ነገሮች በተቃራኒ ለሁሉም የቤቱ አባላት የተለመዱትን የጋራ ነገሮች ላይ መወያየት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፦ “ሁሉም ሰው የራሱ የጥርስ ብሩሽ አለው – የእርስዎ የጥርስ ብሩሽ ምን ይመስላል?” “ቤቱ አንድ ላይ የሁላችንም ነው፤ በእኛ ቤት ውስጥ ማን ማን ይኖራል?
ዓጋሮች
መተወንና መቀያየር
በእንስሳት አሻንጉሊቶች እርዳታ መጽሐፉን መተወንና አንድ ላይ መዝናናት ትችላላችሁ፦ በመዝሙሩ መሰረት አሻንጉሊቶችን በመካከላችሁ ቀያይሩ፣ በተደጋገመው ዓረፍተ ነገር ውስጥም “ከዚያም በቅርብ ጊዜ በሁሉም ውብ ነገሮች ላይ ዓጋሮች እንሆናለን” የሚለው ላይ አሻንጉሊቱን አንድ ላይ በማያያዝ አጋርነት ምን እንደሆነ አሳዩ።
ዓጋሮች
ምስሎችና እንስሳት
ድመት፣ እርግብ፣ ኤሊ፣ ቡችላና ጫጩት – ሁሉም በአንድ መጽሐፍ! ምስሎችን መመልከት፣ አንድ ላይ አንድን እንስሳ መምረጥ፣ ድምፁን ማስመሰልና በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ማስመሰል ይቻላል። ለምሳሌ፦ ኤሊ ከመረጡ “ሙሉ ቤት በጀርባ ላይ” – ትራስ በጀርባዎ ላይ በማስቀመጥ በአራት እግሮች መሄድ ይችላሉ። በጅራቱ ላይ ጭራ ያለው ቡችላ እንዴት ያወዛውዛል?
ዓጋሮች
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ምክር - መንገዳችሁን ማግኘት
ከመኝታ በፊት ተረት ማንበብ አለብህ ያለው ማነው? ምናልባት ከሰዓት በኋላ ማንበብን ይመርጣሉ? ምናልባት ምንጣፉ ላይ አብረው ይተኛሉ ወይስ ለማንበብ የቴዲ ድብን ይቀላቅሉታል? እያንዳንዱ ታዳጊ ህጻን የራሱ ባህርይና ፍላጎት አለው፤ በእርግጥ አዋቂዎችም እንዲሁ የተለያዩ ምርጫዎች አሏቸው። እናንተና ልጆቻችሁ ለማንበብና የራሳችሁን ልዩ የታሪክ ጊዜ ለመፍጠር በጣም ጥሩውን ጊዜና መንገድ መፈለግ አለባችሁ።
ዝንቡ ጠፋብኝ
QR ኮድ
ከጠፋው ዝንብ ጋር መዝፈን ትፈልጋላችሁ? ኮዱን ስካን በማድረግ “ዝንብ ጠፋብኝ” የሚለውን ዘፈን አንድ ላይ አዳምጡ። እንዲሁም አብራችሁ መደነስ፣ መብረርና ጥዝ ማለት ትችላላችሁ።
ዝንቡ ጠፋብኝ
ከእንቅስቃሴ ጋር ማንበብ
በንባብ ጊዜ ልክ በታሪኩ ውስጥ እንዳለው ልጅ ከታዳጊው ህጻን ጋር ዝንብ ማባረር ትችላላችሁ – እጃችሁን በአየር ላይ ማጨብጨብ፣ በሙሉ ሰውነት መዝለል ወይም በመዳፋችሁ ብቻ መዝለል ትችላላችሁ ወይም በትልቅ “እጢሼ” ማስነጠስ ይችላሉ። በመጨረሻም ከጎን ወደ ጎን በመመልከት የጠፋውን ዝንብ ፈልጉ።
ዝንቡ ጠፋብኝ
ጥዝ የሚለው ጣት
ጣታችሁም እንዲሁ ዝንብ ሊሆን ይችላል፦ ጥዝ የሚል ድምጽ በማሰማት ጣታችሁን እንደ ዝንብ በአየር ላይ አንቀሳቅሱት። ታዳጊው “የሚበረው”ን ጣት መከተል እንደቻለ ልብ በሉ። በእያንዳንዱ ጊዜ ጣታችሁን በተለያየ የሕፃኑ አካል ላይ ማድረግ ትችላላችሁ፦ አፍንጫ፣ ጉንጭ፣ እጅ ወይም ጆሮ ላይ። ጮክ ብላችሁ መናገር ትችላላችሁ፦ “ጥዝዝዝዝዝዝ በግንባር ላይ” የአካል ክፍሎችን ስም መለማመድና አንድ ላይ መሳቅ። ታዳጊው ጨዋታውን ካወቀ በኋላ ልክ እንደ ዝንብ በጣቱ እንዲበር ልትጋብዙት ትችላላችሁ።
ዝንቡ ጠፋብኝ
לקרየቤተሰባዊ ንባብ ምክር וא עם פעוטות
የግጥም መጽሐፍን በሚያነቡበት ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድ ግጥም ላይ በማተኮር ብዙ ጊዜ ማንበብ ወይም ዜማ ካለው መዝፈን ይችላሉ። ምስሎችን አንድ ላይ በመመልከት የታዳጊው ወይም የታዳጊዋ ትኩረት የሚሳብበትን ቦታ ማየት ጠቃሚ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመጽሐፉ ውስጥ ሌላ ግጥም በማጣመር ምን አይነት ምላሾች እንደሚያስነሳ ብሎም አስደሳችና ትኩረት የሚስብ መሆኑን ማየት ይችላሉ።
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
እኛና ሌሎች እንስሳት
በመጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ እንስሳትን ያገኛሉ። አንዳንዶቹ ለታዳጊ ህፃናት የተለመዱ ሲሆኑ አንዳንዶቹ አዲስና አስደሳች ናቸው። በአቅራቢያዎ ካለው እንስሳ ጋር ሲገናኙ የታዳጊዎቹን ትኩረት ወደ እንስሳው ልዩ ነገር መምራት ይችላሉ – “ወፉ ምንቃር አለው”፣ “ጉንዳኖቹ በሕብረት ይሄዳሉ” ወይም “ቀንድ አውጣው በጀርባው ላይ ቤት አለው”።
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
በመላው ሰውነት መዝፈን
ዘፈኑን በእንቅስቃሴዎች ማጀብ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ “ደስ የሚል ቢራቢሮ ሆይ ወደ እኔ ና” በሚለው ዘፈን ውስጥ ቢራቢሮውን በእንቅስቃሴ “ና” በማለት መጋበዝ ትችላላችሁ። በእጆችዎ መብረርና የታዳጊውን መዳፍ መንካት። በሳቅ ለሚፈነዳ ዝንጀሮስ የሚስማማው እንቅስቃሴ ምን አይነት ይሆን? ወይስ መሰላሉን ለሚወጣው ድብ?
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
እኔና ሁሉም ዓይነት እንስሳት
የግጥም መጽሐፍን ማንበብ
የግጥም መጽሐፍ ስለ ሴቶችና ወንዶች ልጆች ከተሞክሮ፣ ምናብና ስሜት ዓለም ትንንሽ ታሪኮችን ይነግራል። ግጥሞቹን በቅደም ተከተል ማንበብም ሆነ ሁሉንም ማንበብ አያስፈልግም። በሚያስደንቅ ስዕላዊ መግለጫ፣ በሚስብ ርዕስ መሰረት ወይም እንደ ስሜታችሁ ግጥም መምረጥ ትችላላችሁ። በአንድ ጊዜ አንድ ግጥም ብቻ ማንበብ ወይም እየዘለሉ ማንበብ ይችላሉ። ስለ ዘፈኑ ማውራት አለብዎት፦ ዘፈኑን ወደዱትና ለምን?
በጣም ደስ የሚል – ናሑም ጉትማን
የእስራኤልን ሃገር በደማቅ ቀለም የሳለና ለህፃናት ተረት በቃላትና በስዕላዊ መግለጫ የተረከ ነው። ኮዱን ስካን በማድረግ የናሑም ጉትማን መጽሃፎችንና ስዕሎችን ማወቅና በቴል አቪቭ የሚገኘውን የናሑም ጉትማን ሙዚየምን በቨርቹዋል መጎብኘት ይችላሉ።
መሳል እወዳለሁ
משחק – איזה שיר אני?
በእያንዳንዱ ዙር ከቤተሰብ አባላት ውስጥ አንዱ ቃል አልባ ዘፈን መርጦ ለቤተሰቡ ያቀርባል። የተቀረው ቤት ዘፈኑ ምን እንደሆነ ለመገመት ይሞክራል። እንዲሁም ሁሉም ሰው የሚወደውን ዘፈን መምረጥና አንድ ላይ ማቅረብ ወይም ጮክ ብሎ ማንበብ ብሎም በቃላቱ ላይ ተገቢ እንቅስቃሴዎችን ማከል ይችላል።
መሳል እወዳለሁ
ይፍጠሩና
በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ ባሉ ባዶ ገፆች ላይ ሠዓሊው ናሑም ጉትማንና ደራሲዋ ሚራ ሜኢር እንዳደረጉት እርስዎም ሥዕሎቹን በመከተል ታሪኮችን መሳልና መፍጠር ይችላሉ። ምናልባትም በቀጣዮቹ አንድ ላይ ታሪክ መፍጠር ይፈልጋሉ?
መሳል እወዳለሁ
መሳል እወዳለሁ
ግጥሞችን ማንበብ
በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት ግጥሞች ትንሽ የሕይወት ጊዜዎችን ያቀርባሉ። በእያንዳንዱ የጋራ ንባብ ውስጥ ሌላ ዘፈን በመምረጥ አንድ ላይ ማንበብ አለብዎት። ዘፈኑ በእርስዎ ላይ የደረሰን ነገር ያስታውሳል? ይህ ለእናንተ፣ ለወላጆች ከልጅነታችሁ ጀምሮ ልምዶቻችሁን እንድትካፈሉና በዚህም ከልጅነትና ከልጆች ጋር መቀራረብንና መጋራትን የምትፈጥሩበት እድል ነው።
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ከሐጊት ቤንዚማን ጋር መተዋወቅ
ደራሲ ሐጊት ቤንዚማን መቼ መጻፍ ጀመረች? እርሷ ስለ ምን ትጽፋለች ለምንስ? – የQR ኮዱን ስካን ካደረጉ ፈጣሪዋንና ስራዋን መተዋወቅ ይችላሉ።
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
የቤተሰብን አልበም መመልከት
የወላጆችን የፎቶ አልበሞች አንድ ላይ በማየት ከልጅነት ጀምሮ ልዩ ጊዜዎችን መፈለግ ጥሩ ሀሳብ ነው። እንዲሁም የልጅነትና የልጆች ቀደምት ፎቶግራፎችን ማየትና የተቀረጹበትን አፍታዎች ማጋራት ይችላሉ። በእናንተ ውስጥ ምን ትዝታ ያስነሳሉ?
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
አንድ ላይ ድራማ መስራት
איזה שיר אהבתם במיוחד? – תוכלו להציג אותו יחד, כשהמבוגרים מציגים את תפקיד הילדים, ולהפך.
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ማንበብ፣ መዘመር እና መንቀሳቀስ
ታዳጊው የሚደጋገመውን ዓረፍተ ነገር ያጠናቅቀው፦ “ወዴት፣ ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!”
እንቅስቃሴዎችን መጨመር፣ ማጨብጨብ ወይም የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ።
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
የጠዋት ስነ-ስርአታችን
ተደጋጋሚ የጠዋት ድርጊቶች ታዳጊዎች ቀኑን በጥሩ ሁኔታ እንዲጀምሩ ይረዳቸዋል፦
ልብሱን አብሮ ማዘጋጀት፣ አስደሳች መዝሙር መዘመር፣ በመንገድ ላይ ቅጠሎችን ወይም ቀንበጦችን መሰብሰብ፣ ወይም ቋሚ በሆነ የሚያበረታታ ሰላምታ ቻዎ ማለት።
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ስዕላዊ ማብራሪያዎች ተረትን ይናገራሉ
አንድ ላይ ይመልከቱና ታዳጊው እንዲያገኝ ያድርጉ፦ ወፏ የት አለች? በተጨማሪ ገጾች ላይ ነውን? ልጁን ወደ መዋዕለ ህፃናት የሚሸኘው ማነው? ወደ መዋዕለ ህፃናት እንዴት እንሄዳለን – በብስክሌት፣ በእግር ወይም በሌላ መንገድ? ኮፍያ የሚለብሰው ማን ነው እና ውሻው የት አለ?
የመጨረሻውን ገጽ ይመልከቱ እና ይጠይቁ፦ “በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ያሉ ልጆች ምን እያደረጉ ነው? በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ምን ማድረግ ትወዳለህ/ትወጃለሽ?
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ጨዋታ፦ ወዴት?
ይጠይቁ፦ ወዴት፣ ወዴት? እና በእያንዳንዱ ጊዜ የተለየ ቦታ ይምረጡ፦ ወደ… መታጠቢያው፣ በረንዳው ወይም ወደ… የመጫወቻ ስፍራው? ወደ መረጡት ቦታ አብራችሁ ሂዱ፣ እርስ በርሳችሁ ተቃቀፉ እና ከዚያም ጮክ ብላችሁ ተናገሩ፦ ወዴት? ወዴት? ወደ… የሚቀጥለው ቦታ!
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!
ወዴት? ወደ መዋዕለ ህፃናት!