קבלת השונה
מפגש עם מי ששונה מאתנו יכול להיות מאתגר ולהעלות חשש, אך טמונה בו אפשרות ללמידה, והזדמנות להתפתחות ולפיתוח סקרנות ורגישות. דרך ספרים וסיפורים על קבלת השונה אפשר לגעת בהתמודדויות אמיתיות מחיי הילדים ולטפח מיומנויות חברתיות חשובות.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ምክር
ይህ የጓደኛን ውስብስብ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ሁኔታ በጥንቃቄ የሚዳስስ ልዩ መጽሐፍ ነው። ንባቡንና ጭውውቱን ከታሪኩ ልዩ ይዘትና ከልጅዎ ልዩ ዓለም ጋር ለማስማማት እርስዎ ወላጆች መጽሐፉን ከጋራ ንባብ በፊት እንዲያነቡ እንመክርዎታለን።

“መንገድም አገኘሁ”
የዳዊት ጓደኛ በባህሪው ላይ የሆነ ነገር ሲቀየር ወዲያውኑ ያስተውላል። መወያየትና ማጋራት ይችላሉ፦ ለእርስዎ ቅርብና ውድ የሆነ ሰው ከተለመደው የተለየ ባህሪ እንዳለው አስተውለው ያውቃሉ? ምን አደረጋችሁ? የዳዊት ጓደኛ ስላደረገው ነገር ምን ታስባላችሁ?

የወረቀት አበቦች መልካም ቃልና ልምድ
የቤተሰቡን አባላት የሚያስደስት በመፅሃፍ ተመስጦ ያማረ የአበባ እቅፍ ልጆቻችሁን ጋብዟቸው። ልጆቹ የወረቀት አበቦችን እንዲቆርጡና እንዲያስጌጡ ያቅርቡና በእያንዳንዳቸው ላይ ስለ አንድ የቤተሰብ አባል ጥሩ ቃል ይጻፉ።

የ”ሲያስፈልግ” ሣጥን
በአስቸጋሪ ጊዜ ምን ሊያጽናናዎና ሊያስደስትዎ ይችላል? ጥሩ ቃል? አስደሳች መጽሐፍ? ወይም ምናልባት አሻንጉሊት? በፍላጎት ጊዜ የሃሳቦች ገንዳ ያለው ሳጥን ማዘጋጀት ይችላሉ። ደስታን የሚፈጥሩ እቃዎች፣ አበረታች መልእክቶችና ደጋግ ቃላት

የእቅፍ ደብዳቤ
ልጅዎ ውስብስብ የሆነ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ሁኔታን የሚይዝለት ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል አለው? የማበረታቻና የማጠናከሪያ ደብዳቤ እንዲጽፍ ሊጠቁሙት ይችላሉ? እንደዚህ ያሉ አበረታች ቃላትን ይጠቀሙ፦ እኔ ለአንተ ነኝ፣ ጠንካራ ነህ፣ ጓደኛሞች ነንና እንወድሃለን። ደስታ የተጎናጸፈን ስዕል ይጨምሩበት።

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ይህ አንድ ማየት የተሳነው ወይም ዓይነ ስውር ወንድም ስላለበት አንድ ልዩ ቤተሰብ የሚገልጽ ልዩ መጽሐፍ ነው። ተራኪው ወንድም በቤተሰቡ ውስጥ ያሉትን ችግሮችና በቤት ውስጥ የሚፈለግበትን ውስንነት ጠንቅቆ እያወቀ ነገርግን ዓለምን በአዎንታዊ መልኩ ይመለከታል። ንባቡንና ውይይቱን ከመጽሐፉ ልዩ ይዘት ጋር ለማስተካከል ለእናንተ ወላጆች ከጋራ ንባቡ በፊት መጽሐፉን እንድታነቡ እንመክራለን።

ውይይት
በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ እድለኛ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን? በምን እድለኛ ናችሁ? ወላጆችና ልጆች እርስ በርሳችሁ እንደ ቤተሰብ አብረው በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች በተመለከተ ማካፈል ትችላላችሁ። በሳምንት አንድ ጊዜ የቤተሰቡ አባላት ባለፈው ሳምንት ያጋጠሟቸውን አወንታዊ ነገሮች የሚያካፍሉበት መደበኛ ሥርዓት መፍጠር ትችላላችሁ።
ምን ታያላችሁ...?
ዓይነ ስውራን ልጆች ሕይወትን እንዴት ይለማመዳሉ? ኮዱን በማድረግ ከዓይነ ስውራን ልጆች ጋር “ለጥያቄው ይቅርታ” የሚለውን ክፍል ማየት ትችላላችሁ። ከቪዲዮው በኋላ መወያየት ጠቃሚ ነው፦ ሕይወታችን እንዴት ተመሳሳይ ነው እንዲሁም በቪዲዮው ውስጥ ካሉት ልጆች እንዴት ይለያሉ?

ድጋሜ በማንበብ ምን እናውቃለን?
በሁለተኛው ንባብ አዳዲስና አስገራሚ ነገሮችን ማግኘት ይቻላል። ምስሎችን በመመልከትና የሃጋይን የእይታ እክል ፍንጭ በመፈለግ መጽሐፉን ሁለት ጊዜ ማንበብ ተገቢ ነው፦ ቃላቱና ምስሎቹ ስለቤተሰብ ፈተና ምን ፍንጭ ይሰጣሉ? በመጀመሪያው ንባብ ይህን አስተውላችኋል?

ምናባዊ ጨዋታ
ሃጋይ ምናባዊ ታሪኮችን እንዴት እንደሚናገር ያውቃል። እናንተም ሞክሩት! ሁለት እቃዎችን በመምረጥ ምናባዊ ታሪክን ለመተረክ ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ -ብሩሽና ምንጣፍ፣ ጠርሙስና የድመት አሻንጉሊት፣ ኮፍያና መስኮት – እናንተ በጋራ ባሰባሰባችሁት ምናባዊ ታሪክ ውስጥ ምን ሊደርስባቸው ይችላል?

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚበጅ ምክር
አንድ መጽሐፍ ለአንድ ልዩ ዝግጅት ለመዘጋጀት ወይም ካለፈ ክስተት ላይ ትውስታዎችን ለመሰብሰብ ይረዳል። የበዓል ሰሞን ለምሳሌ ከበዓል ጋር የተያያዘ መጽሐፍ መምረጥና መወያየት ይችላሉ፦ በበዓል ቀን ምን ምን ዝግጅቶች ለእርስዎ ታቅደዋል? ሲቃረብስ ወላጆችና ልጆች አብረው እንዴት ማዘጋጀት ይችላሉ? ለፑሪም ዝግጅት አንድ ላይ ልብስን መላበስ ወይም ምግቦችን መላክ ይችላሉ። ከበዓል በኋላም መጽሐፉን እንደገና ማንበብና በእርሱ በመታገዝ አብረው ያጋጠሟችሁን መልካም ጊዜያት ያስታውሱ።

መላበሶች በምስሎች
“በመጽሐፉ ውስጥ የጠፈር ተመራማሪ አለባበስ የት ላይ ነው ያለው? ንግስት አስቴርን፣ የእሳት አደጋ ተዋጊዎችን፣ ፖሊሶችን ወይም አልበርት አንስታይንን በተመለከተስ? በምስሎቹ ውስጥ ልብሶችን መፈለግ ትችላላችሁ። በተለይ የትኛውን መላበስ ይወዳሉ?
አልበርት አንስታይን ማን ነበር?
አልበርት አንስታይን [1879-1955] የጀርመን ተወላጅ አይሁዳዊ ሳይንቲስት ነበር። እርሱ ባዘጋጀው “”የአንፃራዊነት ፅንሰ-ሀሳብ”” ባደረጋቸው ሌሎች ጥናቶች በመታገዝ በሳይንሱ ዓለምና በተፈጥሮ፣ በጊዜ ብሎም በዩኒቨርስ ህጎች ግንዛቤ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። አንስታይን በቀልድና ምናብ ተሰጥኦ የተካነ ነበር። ለሰላምና ለወንድማማችነት የሰራ ሲሆን ከመላው ዓለም ካሉ ልጆች ጋር መጻጻፍ ይወድ ነበር። አንስታይን በኢየሩሳሌምና በእስራኤል ግዛት ስር የዕብራይስጥ ዩኒቨርስቲ እንዲቋቋም ድጋፍ አድርጓል።”

የቤተሰባዊ ንባብ ምክር
በእያንዳንዱ መጽሐፍ ውስጥ የሚወደድ ነገር አለ፦ በታሪኩ ውስጥ ያለው ውጥረት፣ ገፀ ባህሪያቱና ምናልባትም ምስሎች ወይስ ልዩ ቃላቱ? በንባቡ መጨረሻ ላይ ልጆች ስለ ታሪኩ የወደዱትን መጠየቅና እናንተው ወላጆችም የወደዳችሁትን አካፍሉ። በተለይ የትኞቹን መጽሃፎች እንደምትወዱና ለምን እንደሆነ እርስ በርሳችሁ መተረክ ትችላላችሁ።

እኛና ጓደኞች
ፊትዝና እንጉዳዩ አንድ ላይ ናቸው። እርሷ አትክልቶቹን ታበቅላለች፤ እርሱ ይንከባከባል። እስከዚያው ድረስ ይጨዋወታሉ፤ ይዘምራሉ፤ እንዲሁ አብረው ይዝናናሉ። ልጆችን ከጓደኞቻቸው ጋር ምን ማድረግ እንደሚወዱ መነጋገርና መጠየቅ እንችላለን። አብረው ጊዜ የሚያሳልፉት እንዴት ነው? ይህ ለወላጆች የልጅነት ጓደኞቻችሁን የማስታወስና ልምዶችን ከልጆችዎ ጋር ለመካፈል እድል ነው።

አትክልቶችና ምስሎች
ጥቅል ጎመን? ብሮኮሊ? – በመጽሐፉ ውስጥ አሥራ ሦስት ዓይነት ለምግብነት የሚውሉ አትክልቶች ይገኛሉ፦ ልታገኟቸው ትችላላችሁ? ምናልባትም የሚወዱትን አትክልት መመገብ ወይም አዲስ አትክልቶችን መሞከርና መቅመስ ይፈልጋሉ?
አትክልቶችን ማሳደግ
ምንም እንኳን መሬት ባይኖራችሁም አትክልቶችን ማምረት ትችላላችሁ፦ የተቆረጠ የካሮት ራስ፣ የነጭ ሽንኩርት ወይም የሰላጣ ወይም የካርፓስ የታችኛው ክፍል ግልፅ አድርጎ በሚያሳይ መያዣ ውስጥ ውሃ ማጠጣት ይቻላል። በትዕግስት ይጠብቁ፤ አስፈላጊ ከሆነ ውሃ በመጨመር ቀስ በቀስ ሥሮችና ቅጠሎች እያደጉ ያገኙታል። መከርከምና መብላት ወይም በማሰሮ ውስጥ መትከል፣ ውሃ ማጠጣትና አዲሶቹን አትክልቶች እስኪያድጉ ድረስ መጠበቅ ይችላሉ።
ቪድዮ
እንጉዳይ አንተ ራስህ ማን ነህ? – ኮዱን ስካን በማድረግ በእስራኤል ውስጥ በየክረምቱ እንደ አዲስ ከሚታዩት እንጉዳዮች ጋር ያስተዋውቃል። የበለጠ መማር ይፈልጋሉ? አብረው ወደ ቤተ መፃህፍት በመሄድ ወይም በኢንተርኔት በማሰስ ስለ እንጉዳዩና ሌሎች እንጉዳዮች መረጃ ይፈልጉ።
የስሜት ቃላት
በታሪኩ ውስጥ ያሉት ፊደሎች ስሜቶችን ይገልጻሉ፦ አንድን ሰው ማጣት፣ አንድን ሰው መውደድ፣ ደስተኛ መሆን…
በስሜት ቃላቶች አንዳንድ ካርዶችን መስራት፣ እንዲሁም እነዚህን ስሜቶች የሚገልጹ ሐረጎችን መሥራት፣ እና እያንዳንዱን ቃል ከሚገልጸው ዓረፍተ ነገር ጋር እንዴት ማገናኘት ይቻላል?
አንድን ሰው መናፈቅ፦ እንደገና እንድንገናኝ እመኛለሁ
አንድን ሰው መውደድ፦ አብረን ስንሆን ጥሩ ስሜት ይሰማናል
የደስታ ስሜት፦ ይህ ዜማ ወደላይ መዝለልና መደነስ እንድፈልግ ያደርገኛል
የማመስገን ስሜት፦ በመገናኘታችን በጣም ደስ ብሎኛል! ወደዚህ ስለመጡ አመሰግናለሁ!