סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ ሊሆን የሚችል ጠቃሚ ምክር
መጽሐፍን አንድ ላይ ማንበብ በልጆች ላይ የሕዋሳትና የስሜት አስተሳሰቦችን ሊፈጥር ይችላል፦ ልክ እንደ ጫጩት ትንሽነትና ደካማነት ሊሰማቸው ይችላል። እንደ ኤፍራት ሁሉ እነርሱ የማይረዷቸው ሆኖ ሊሰማቸው ወይም በዓይናቸው ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ ሊያደርጉ ይችላሉ። ተቀራርበን ተቀምጠን ንባቡን በሚያሳምንና በሚያረጋጋ ንክኪ ማጀብ ጥሩ ነው፦ መነካካቱ ልጆቹን ወደ ወላጆቻቸው ያቀራርባል፤ ልጆቹን የሚደግፋቸውና መጽሐፉ የሚያነሳሳቸውን ስሜቶች በትኩረት የሚከታተል ሰው በእነርሱ ውስጥ እንዳለ ያላቸውን እምነት ያጠናክራል።
ኮተን ቡታን
ማደግ
ኮተን ቡታን ያድጋል። ነፃነትንና ሃላፊነትን ያገኘቺው ኤፍራትም እንዲሁ። ልጆቹችከዚህ በፊት ከነበሩት የበለጠ ትልቅ እና ኃላፊነት የሚሰማቸው እንዴት እንደሆነ ማውራትና መጠየቅ ትችላላችሁ – ለምሳሌ እንስሳትን ይንከባከባሉ? ድርጊቶችን እራሳቸው ያከናውናሉ? ቤትንና ጓደኞችን ይረዳሉ? እናንተ ወላጆች ያደጋችሁበትንና አካባቢውን ልጆችን ማሳሰቡ ሁል ጊዜ ጠቃሚ ነው። በዚህም ለልጆች ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸውና የደህንነት ስሜታቸውን እንዲያጠናክሩ ያደርጋቸዋል።
ኮተን ቡታን
እንሥሳትን መርዳት
እናንተም በአካባቢያችሁ ያሉትን እንስሳት መርዳት ትችላላችሁ፦ በውስጡም ፍርፋሪ ያለበት የወፍ መኖ ጣቢያ ማዘጋጀት፣ ለድመቶች አንድ ሳህን ውሃ ማስቀመጥ፣ የጉንዳን ጎጆን የሚከላከል ምልክት ማድረግ ወይም በአካባቢው ላሉ እንሰሳት ስለምታደርጉላቸው እርዳታ ማሰብ ትችላላችሁ።
ኮተን ቡታን
እንሥሳቱ የት ነው ያሉት?
በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጹት ምሳሌዎች ውስጥ የተለያዩ እንስሳት ይታያሉ – አንዳንዶቹ አሻንጉሊቶች፣ ስዕሎችና ጨዋታዎች አንዳንዶቹ እውነተኛ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ በልጆች ሀሳቦች ውስጥ የሚታዩትን ልታገኟቸው ትችላላችሁ?
ኮተን ቡታን
መዝለል፣ ዱብ ዱብ ማለት፣ መብረር
መንቀሳቀስ ትወዳላችሁ? ኮተን ቡታን መብረርን የተማረበትን ገጽ ተመልከቱና ከታሪኩ ጋር ለመንቀሳቀስ ሞክሩ፦ ክንፍ ማውጣት፣ ዱብ ዱብ ማለት፣ መዝለልና ምናልባትም “በቢሆን” ለመብረር መሞከር ትችላላችሁ።
ኮተን ቡታን