סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ስዕሎቹ የመጽሐፉ ዋና አካል ሲሆኑ በታሪኩ ውስጥ ሁልጊዜ ያልተጻፉ ዝርዝሮችን ያሟላሉ። ለምሳሌ፦ ቴይለር የሚገነባባቸው በስዕሉ ላይ ብቻ የሚታዩት ብሎኮች። በስዕሎቹ ውስጥ ምን ሌሎች ዝርዝሮችን አግኝተዋል? አንዳንድ ጊዜ በውስጡ ባሉት ስዕሎች አንድን ታሪክ “እንደገና” ለማንበብ መሞከር አለብዎት። ሌላም ምን ሊያገኙ እንደሚችሉ ያረጋግጡ።
ጥንቸሉ አዳምጧል
ነገሮች አልሳካ ሲሉ ላይ መወያየት
በማዳመጥ መልመጃዎች በመታገዝ የስሜት ህዋሳትን ንቁ በማድረግ አዳዲስ ነገሮችን ማስተዋል ይችላሉ፦ ከተቀመጡ በኋላ ጀርባ ለጀርባ ከዚያም ፊት ለፊት ለመነጋገር ይሞክሩና በእያንዳንዱ ጊዜ ምን እንደተሰማዎት ለማየት ይሞክሩ። ሌላ መልመጃ፦ ዓይኖችዎን ለአንድ ደቂቃ ይጨፍኑ። በፍፁም ፀጥታ በዙሪያዎ ያሉትን ድምፆች ለማዳመጥ ብቻ ይሞክሩ። በጊዜው መጨረሻ የሰሙትን ይናገሩ።
ጥንቸሉ አዳምጧል
እንሳሳትና ማስመሰሎች
ሰጎን ጭንቅላቷን አሸዋ ውስጥ ስትቀብር ምን ትመስላለች? ዝሆኑ ሲያስታውስ በኩምቢው ምን ያደርጋል? ድብስ ምን ያህል ይናደዳል? በእንቅስቃሴው፣ በድምጹና በሚሰጠው መፍትሔ መሰረት በመፅሃፉ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን እንስሳት ለማስመሰል ይሞክሩ።
ጥንቸሉ አዳምጧል
ውይይት፦ ቀዳዳዎች በመርከቧ ውስጥ
ልክ እንደ ሽላፍኖቼዎቹ መርከብ በቤት ውስጥም አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ወይም ‘ጥፋቶች’ አሉ። መፍትሔው የጋራ ጥረት ይጠይቃል። ታሪኩን በመከተል በጋራ መነጋገርና ማሰብ ይችላሉ፦ በየትኞቹ ሁኔታዎች በቤተሰብ ውስጥ አንድን ሀሳብ ወይም መፍትሔ ማሰብ አለብን? የጋራ ጥረት መቼ ያስፈልጋል? መቼ ነው ችግር እንዳለ ተረድተን ነገር ግን መፍትሔ ለማግኘት ጥረት ሳናደርግ ስለ ጉዳዩ ብቻ የምንነጋገርበት ሁኔታ መቼ ይከሠታል? በእነዚህ አጋጣሚዎችስ የትኛው ‘ወፍ’ ሊያድነን ይችላል?
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
ቤተሰባዊ የሆነ ፈታኝ ነገር
በታሪኩ መጨረሻ ላይ በቂ መፍትሔ በማይኖርበት ጊዜ “አራቱ ሽላፍኖቼዎች በአንድ ትንሽ ቁም ሳጥን ላይ” ይሰበሰባሉ። እንዲሁም ለመዝናናትና ለመፈተሽ መሞከር ይችላሉ – ስንት የቤተሰብ አባላት በአንድ ትንሽ ምንጣፍ ላይ መሰብሰብ ይችላሉ? በመጋሊቦሽ ላይስ? ወይም በመረጡት ሌላ ቦታ ላይ። አንድ ላይ ለማሰብ ይሞክሩና በዚህ ፈታኝ ነገር ውስጥ የሚረዱዎትን የፈጠራ ሀሳቦችንና መፍትሔዎችን ያቅርቡ።
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
አስቂኝ ስሞች ያሏቸውን ፍጡሮች መፍጠር
ሽላፍኖቼ ምን አይነት አስቂኝ ስም ነው? ለእንደዚህ አይነት ተጨማሪ አስቂኝ ስሞች ሀሳብ አለዎት?
ሃምቡልባሊኖስ? ሃሽቱቲፑሎች? የእራስዎን ምናባዊና አስቂኝ ፍጥረታትን አንድ ላይ መፍጠር የሚችሉ ሲሆን በዓይነ ሕሊናዎ በመሳል ቀለም ይስጧቸውና ለእነርሱ ረዥምና አስቂኝ ስም ይወስኑ።
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ
טיפ לקריאה משפחתית:
לאחר הקריאה כדאי לחזור אל הסיפור ולהקדיש זמן להתבוננות באיורים. להבחין בפרטים קטנים שלא קשורים ישירות לטקסט ולשתף זה את זה בתגליות שלנו.
አዞ ወደ ባቡሩ ገባ
מתחשבים אחד בשני
גם בבית כולם צריכים להסתדר יחד באותו ה”קרון”. תוכלו לשוחח עם הילדים ולחשוב: באֵילו מצבים בבית אנחנו צריכים להתחשב אחד בשני? למה חשוב שנִפנה ונדבר על מה שלא נעים או לא מתחשב בעינינו? כיצד כדאי לעשות זאת?
አዞ ወደ ባቡሩ ገባ
משחק תפקידים
תוכלו להמחיז את הסיפור – שְבוּ יחד ב”רכבת” – ההורה יהיה התנין המתפרש על כל הקרון, והילד או הילדה יהיו האפרוח. כיצד תבקשו מהתנין מקום? האם בסוף תשתוללו ותשתעשעו כמו חברים? עכשיו ניתן להחליף תפקידים.
አዞ ወደ ባቡሩ ገባ
חיות ותכונות
הצב איטי, הינשופה נבונה והארנב מהיר. תוכלו לחזור אל הסיפור ולבדוק – אֵילו חיות נוספות מופיעות בו? אֵילו תכונות ומאפיינים מיוחדים יש להן? האם גם במציאות הן בעלות אותן תכונות?
አዞ ወደ ባቡሩ ገባ
አዞ ወደ ባቡሩ ገባ
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር - ከመጽሃፉ ወደ ሕይዎት
መጽሃፍት ፈታኝ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ይረዳሉ። ታዳጊዎች በመጽሃፍቱ ውስጥ ካሉ ገፀ-ባህሪያት ጋር ይተዋወቃሉ። በውጤቱም በመጽሃፍቱ ውስጥ እንዲሁም በሕይወታቸው ውስጥ ስላሉት ስሜቶች፣ ባህሪዎችና ተግዳሮቶች ይማራሉ። በመጽሐፉ ውስጥ ከቀረቡት ጋር በሚመሳሰሉ ሁኔታዎች ውስጥ ታዳጊዎችን የመጽሐፉን ጀግኖች ለማስታወስና መነሳሻን እንዲስሉ በተመሳሳይ መንገድ እንዲሠሩ ሀሳብ መስጠት ትችላላችሁ – “ምናልባት አግዳሚ ወንበር ላይ ትንሽ ልንንቀሳቀስና ከመጽሐፉ ውስጥ እንዳሉት ድቦች ለጓደኛ ቦታ እንሰጥ ይሆናል።”
ድቦች በመቀመጫዎች ላይ
ታሪኩ ላይ ምን እየሆነ ነው?
በመጽሐፉ ውስጥ ስላለው ክስተት ከታዳጊዎች ጋር መነጋገር ትችላላችሁ – ድቦች ምን ችግር አጋጥሟቸዋል? ለምን ድቡ የሚቀመጥበት ቦታ አልነበረውም? ሌሎቹ ድቦች ምን አደረጉ? እንዲሁም ከታሪኩ የሚነሱትን ስሜቶች መጥቀስ ትችላላችሁ -ቴዲ ድብ ቦታ በሌለው ጊዜ ምን ተሰማው? ተደስቶ፣ አዝኖ ወይም ምናልባት ተገርሞ ወይስ ግራ ተጋብቶ ነበር?
ድቦች በመቀመጫዎች ላይ
QR ኮድ - በድቦች ጨዋታ
ታሪኩን ማቅረብ ትፈልጋላችሁ? – ኮዱን ስካን በማድረግ የድብ ገጸ ባህሪዎችን ማተም፣ ቀለም መቀባትና አንድ ላይ ማሳየት ትችላላችሁ!
ድቦች በመቀመጫዎች ላይ
በምስሎች ማንበብ
“በምስሎቹ አማካኝነት መማር፣ መጫወትና መደሰት ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ጊዜ በምስሎቹ ውስጥ የተለያዩ ዝርዝሮችን መፈለግ ትችላላችሁ – ሮዝ ቴዲ ድብ የት አለ? ባለነጠብጣቡ ድብ የት አለ? ትልቁ ድብና ትንሽ ድብ የት አሉ?
ሚናዎችን በመቀያየር ታዳጊዎቹ በምስሉ ላይ እቃዎችን እንድትፈልጉ እንዲጋብዙ ማድረግ ትችላላችሁ።
“
ድቦች በመቀመጫዎች ላይ
ድቦች በመቀመጫዎች ላይ
እንደ ድብ
መጽሐፉን በማገላበጥ ልክ በምስሉ ላይ እንዳለው በእያንዳንዱ ጊዜ በተለያየ ገጽ ላይ በማቆም ድቦችን መመልከትና እንቅስቃሴያቸውን፣ የተቀመጡበትን መንገድ ብሎም የፊት ገጽታን ለመምሰል መሞከር ትችላላችሁ።
ድቦች በመቀመጫዎች ላይ
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ታዳጊዎቹ አንድ ላይ ሲያነቡ ይደሰታሉ። በታሪኩ ላይ ሲያተኩሩ ደግሞ የመማር፣ የማተኮርና የማሰብ ችሎታዎችን ይጠቀማሉ። ወደ ታሪኩ ውስጥ “ለመግባት” እና ትኩረታቸው እንዲሰበስብ ለደቂቃዎች ያህል ከዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥ፣ የተረጋጋ ቦታ ላይ ተቀምጦ ያለ የጀርባ ጫጫታ፣ ስክሪን ወይም ሞባይል በታሪኩ ክንፍ ላይ አብሮ መብረር ይጠቅማል።
ድመቷም
አንዴ ወንድ አንዴ ደግሞ ሴት ድመት ነኝ
አጭሩ መፅሃፍ ከህፃናት የእለት ተእለት ህይወት ልምዶች የተሞላ ነው፦ ለመሳተፍ ይፈልጋሉ፣ አንዳንድ ጊዜ ውድቅ ያደርጉታል፣ እራሳቸውን ችለው ለመኖር ይጥራሉ ብሎም መፍትሔዎችን በማግኘት ይጠመዳሉ። በታሪኩ ውስጥ እንደዚህ ባሉ ጊዜያት ከልጆች ጋር መነጋገርና ከዓለማቸው ጋር ማዛመድ ትችላላችሁ – ድመቷ ምን ፈለገች? ድመቷ ከእርሷ ጋር መቀላቀል በማይፈልግበት ጊዜ ምን ተሰማት? ምን ለማድረግ ወሰነች? እንዲሁም ጉዞ ላይ መሄድ ትወዳለህ? አንቺን ምን ማድረግ ትወጃለሽ?
ድመቷም
ለጉብኝት እንውጣ
ታዳጊዎች ትንሽ ቦርሳ እንዲይዙና ልክ እንደ ድመቷ በቤት ውስጥ ወይም በአካባቢው በእግር መራመድ ይችላሉ። በጉዞው ላይ ምን መወሰድ እንዳለበት አንድ ላይ ማሰብ እንችላለን – የውሃ ጠርሙስ? ኮፍያ? ምናልባት አሻንጉሊት?
ድመቷም
ምስሎቹ ምን ይናገራሉ?
ስዕሎቹን አንድ ላይ ስትመለከቱ በእያንዳንዱ ጊዜ ትኩረታችሁን ወደ ሌላ ነገር ማዞር ትችላላችሁ – ድመቱ የት አለ? ድመቷስ የት አለች? ምን እየሰሩ ነው? በሥዕሉ ላይ የትኞቹን ነገሮች ታውቃላችሁ?
ድመቷም
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር- ልምድን ማጋራት
“ብዙ መጻህፍት የህፃናትን የእለት ተእለት ሕይወት ላይ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ይገልፃሉ፦ የማካፈል ችግር፣ የመሰናበት ችግር፣ ከቀን ወደ ማታ የመሸጋገር ፈተናና ሌሎች ብዙ። ታዳጊው ፈተና እየገጠመው መሆኑን ስትረዱ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ መጽሐፍ መርጣችሁ አብራችሁ አንብቡ። መጽሐፉ ስሜትንና ልምዶችን እንድታካፍሉ ይጋብዛል።
የመለ
ያ፣ የማበረታቻና የመቋቋሚያ ሃሳቦችን ማቅረብ ይችላል።
ሊያ ናኦር – በ1935 በሄርጼሊያ ተወለደች። ለህፃናት መጽሃፎችን፣ ድራማዎችን፣ ስክሪፕቶችንና መዝሙሮችን የጻፈች ሲሆን ብዙ መጽሃፎችን ወደ ዕብራይስጥም ተርጉማለች። ከእነርሱም መካከል ተከታታዩ “”ዶክተር ሱስ”” ይገኝበታል። መጽሐፎቿና ትርጉሞቿ ብዙ ሽልማቶችን አሸንፈዋል።”
ዓጋሮች
የእኔ ምንድን ነው የእኛስ ምንድን ነው?
ለእያንዳንዱ የየራሳቸው ከሆኑት ነገሮች በተቃራኒ ለሁሉም የቤቱ አባላት የተለመዱትን የጋራ ነገሮች ላይ መወያየት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፦ “ሁሉም ሰው የራሱ የጥርስ ብሩሽ አለው – የእርስዎ የጥርስ ብሩሽ ምን ይመስላል?” “ቤቱ አንድ ላይ የሁላችንም ነው፤ በእኛ ቤት ውስጥ ማን ማን ይኖራል?
ዓጋሮች
መተወንና መቀያየር
በእንስሳት አሻንጉሊቶች እርዳታ መጽሐፉን መተወንና አንድ ላይ መዝናናት ትችላላችሁ፦ በመዝሙሩ መሰረት አሻንጉሊቶችን በመካከላችሁ ቀያይሩ፣ በተደጋገመው ዓረፍተ ነገር ውስጥም “ከዚያም በቅርብ ጊዜ በሁሉም ውብ ነገሮች ላይ ዓጋሮች እንሆናለን” የሚለው ላይ አሻንጉሊቱን አንድ ላይ በማያያዝ አጋርነት ምን እንደሆነ አሳዩ።
ዓጋሮች
ምስሎችና እንስሳት
ድመት፣ እርግብ፣ ኤሊ፣ ቡችላና ጫጩት – ሁሉም በአንድ መጽሐፍ! ምስሎችን መመልከት፣ አንድ ላይ አንድን እንስሳ መምረጥ፣ ድምፁን ማስመሰልና በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ማስመሰል ይቻላል። ለምሳሌ፦ ኤሊ ከመረጡ “ሙሉ ቤት በጀርባ ላይ” – ትራስ በጀርባዎ ላይ በማስቀመጥ በአራት እግሮች መሄድ ይችላሉ። በጅራቱ ላይ ጭራ ያለው ቡችላ እንዴት ያወዛውዛል?
ዓጋሮች
የቤተሰባዊ ንባብ ምክር
ምስሉ ለጋ አንባቢዎች ለሥነ-ጽሑፍ እንዲጋለጡና በተጻፈው ታሪክ ላይ አንዳንድ ጊዜም በቃላት ከተነገረ በኋላ ተጨማሪ ታሪክ የሚናገሩ አዳዲስ ዓለሞችን እንዲያውቁ ያስችላቸዋል። በመጽሐፍ ንባብ ጊዜ ምስሎችን አንድ ላይ ማየ፣ የንባብ ፍሰቱን ቆም ማድረግ፣ አንድ ተጨማሪ ጊዜ መመልከትና ልጆቹ የልባቸውን ለመናገር ልዩ ዝርዝሮችን እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል።
ለምን አታብብም?
መንከባከብና መሞከር
ቴዲ ድብ ተክሉን ለመርዳት ይሞክራል፣ ያስብለታልና ይንከባከበዋል። አብሮ በመወያየት ማካፈል ይቻላል፦ ለማን ታስባላችሁ? ማንን ነው የምትንከባከቡት? – የቤት እንስሳን? አሻንጉሊትን? ተወዳጅ አበባን ወይስ ምናልባት ትንሽ ወንድምን? – እነርሱን ለመንከባከብ ምን ታደርጋላችሁ? እንክብካቤው እንዳቀዳችሁት ባይረዳም ነገር ግን ባላሰባችሁት መንገድ የተከናዎነበት እድል ነበር?
ለምን አታብብም?
QR ኮድ - በካሮት ምን ይደረጋል?
ለመትከልና ለመመገብ ካሮትን ማዘጋጀት ይፈልጋሉ? – ኮዱን ስካን ያድርጉና ከትንሽ ካሮት ቁራጭ ምን ሊወጣ እንደሚችል ይመልከቱ።
ለምን አታብብም?
ምስሎች ይናገራሉ
ጥንቸሎች ምን ሆኑ? አስቂኝ ምስሎች ከመሬት በታች ያለውን መላውን ዓለም ያሳያሉ። ምስሎችን መመልከትና ጥንቸሎች ሲደሰቱ፣ ሲያዝኑ፣ ሲጠግቡ ወይም ሲጨናነቁ ምን እንደሚሰሩ በጋራ መተረክ ይችላሉ።
ለምን አታብብም?
እዚህና እዚያ ላይ ምን ታያላችሁ?
ሶፋው ላይ ስትቀመጡ ምን ታያላችሁ? በክፍሉ መሃል ስትቆሙስ? ወይም በጠረጴዛው ስር ሲሳቡ? – በእያንዳንዱ ዙር አንድ የቤተሰብ አባል አንድ ቦታ ይመርጥና ክፍሉን ከዚያው ያያል፦ ትኩረቱን የሚስበው ምንድን ነው? እርሱ ሌሎች ማየት የማይችሏቸውን ዝርዝሮች ይመለከታል?
ለምን አታብብም?