עלייה
אספנו עבורכם סיפורים שונים על עלייה לארץ. כל סיפור מזמין את הקוראים למסע מרגש של צבעים, ריחות וטעמים של ארץ אחרת, וחושף אותם לתרבויות, לשפות, למאכלים ולמנהגים שונים המחוברים כולם בחוט אחד של הזהות היהודית הישראלית. סיפורי עלייה מאפשרים לנו להכיר את החוויה המטלטלת ואת ההתמודדויות הכרוכות בה, להבין את תחושותיהם של ילדות וילדים שעלו לארץ ולהתחבר לשורשיהם ולסיפורם המשפחתי.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
“ታላቁ የሲማቺ ቀን” ረዘም ያለ መጽሐፍ ነው። ለዚያም ነው በሁለት ክፍሎች ለማንበብ የሚመከረው፦ ሲማቺ ወንድሟ አብራም ለምን የበዓል ልብስ እንደለበሰ ከተገረመች በኋላ ማንበብ ያቁሙና በሚቀጥለው ቀን ማንበብዎን ይቀጥሉ።
ትዝታዎች
በመጽሐፉ ውስጥ አያቱ የልጅነት ጊዜዋን ትዝታ ትተርካለች። ይህ ለእናንተ ለወላጆች ከልጅነታችሁ ጀምሮ ልዩ ጊዜዎችን እንድታካፍሉ እድል ነው። ስላደረጋችኋቸው ነገሮች፣ ከዚህ በፊት ማድረግ እችላለሁ ብላችሁ ያላሰባችሁትን ወይም በእናንተና በወንድሞቻችሁ መካከል ስላለው ግንኙነት ተርኩ። እንዲሁም ልጆቹን ጠይቋቸው፦ ወደ ኋላ በመመልከት በራሳቸው ባገኙት ችሎታ ያስደነቋቸውን ያደረጓቸውን ልዩ ድርጊቶች ማስታወስ ይችላሉ?
አናናስ በራስ ላይ
አብራምና ኔሚ አናናስ ራሳቸው ላይ በማድረግ የመራመድ ጨዋታ ይጫወታሉ። ማን እንደማይጥልም ለማየት ይወዳደራሉ። ተመሳሳይ ጨዋታም መጫወት ትችላላችሁ፦ በራሳችሁ ላይ የምታስቀምጧቸውን ዕቃዎች – ትራስ፣ አሻንጉሊት ወይም ሳጥን ምረጡና፦ ከመካከላችሁ በመራመድ ራሱ ላይ መሸከም የሚችለው ማነው? እስከ ምን ርቀት? የሚለውን አረጋግጡ።
ባህሩን ተከትሎ
ታሪኩ ከባህር ጋር የተያያዙ ብዙ ተግባራትን ይገልፃል፦ የዓሳ እንቅስቃሴ፣ ጀልባ መቅዘፍ፣ ዋና፣ የዓሣ ማጥመጃ መረቦችን መሰብሰብ፣ በመርከብ ምሰሶ ላይ ባንዲራ ማውለብለብ ወይም መስቀል። ከድርጊቶቹ ውስጥ አንዱን በመምረጥ በእንቅስቃሴ ማሳየት ትችላላችሁ። የቤተሰቡ አባላት የትኛውን ድርጊት እንደፈለጉ መገመት የሚኖርባቸው ሲሆን በመጽሐፉ ውስጥ ካሉት ምስሎች ውስጥ የሚፈልጉት ይሆናል። መልካም እድል!