עזרה הדדית
כוחה של קבוצה או קהילה וכוחו של כל קשר טמונים בהדדיות. ביכולת לתמוך ולהיתמך, לתת ולקבל. עזרה הדדית מחזקת את האמון בין חברי הקבוצה, מעניקה בטחון ומשמעות ותורמת לתחושת השייכות. אמנם לא לכולם פשוט לבקש או להושיט עזרה - מגוון של סיפורים משעשעים, מרגשים ומופלאים על עזרה הדדית יכולים לסייע להטמיע את ערך ההדדיות, לעורר השראה ולמלא את הלב ברצון טוב.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

ውይይት፦ ቀዳዳዎች በመርከቧ ውስጥ
ልክ እንደ ሽላፍኖቼዎቹ መርከብ በቤት ውስጥም አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ወይም ‘ጥፋቶች’ አሉ። መፍትሔው የጋራ ጥረት ይጠይቃል። ታሪኩን በመከተል በጋራ መነጋገርና ማሰብ ይችላሉ፦ በየትኞቹ ሁኔታዎች በቤተሰብ ውስጥ አንድን ሀሳብ ወይም መፍትሔ ማሰብ አለብን? የጋራ ጥረት መቼ ያስፈልጋል? መቼ ነው ችግር እንዳለ ተረድተን ነገር ግን መፍትሔ ለማግኘት ጥረት ሳናደርግ ስለ ጉዳዩ ብቻ የምንነጋገርበት ሁኔታ መቼ ይከሠታል? በእነዚህ አጋጣሚዎችስ የትኛው ‘ወፍ’ ሊያድነን ይችላል?

ቤተሰባዊ የሆነ ፈታኝ ነገር
በታሪኩ መጨረሻ ላይ በቂ መፍትሔ በማይኖርበት ጊዜ “አራቱ ሽላፍኖቼዎች በአንድ ትንሽ ቁም ሳጥን ላይ” ይሰበሰባሉ። እንዲሁም ለመዝናናትና ለመፈተሽ መሞከር ይችላሉ – ስንት የቤተሰብ አባላት በአንድ ትንሽ ምንጣፍ ላይ መሰብሰብ ይችላሉ? በመጋሊቦሽ ላይስ? ወይም በመረጡት ሌላ ቦታ ላይ። አንድ ላይ ለማሰብ ይሞክሩና በዚህ ፈታኝ ነገር ውስጥ የሚረዱዎትን የፈጠራ ሀሳቦችንና መፍትሔዎችን ያቅርቡ።

አስቂኝ ስሞች ያሏቸውን ፍጡሮች መፍጠር
ሽላፍኖቼ ምን አይነት አስቂኝ ስም ነው? ለእንደዚህ አይነት ተጨማሪ አስቂኝ ስሞች ሀሳብ አለዎት?
ሃምቡልባሊኖስ? ሃሽቱቲፑሎች? የእራስዎን ምናባዊና አስቂኝ ፍጥረታትን አንድ ላይ መፍጠር የሚችሉ ሲሆን በዓይነ ሕሊናዎ በመሳል ቀለም ይስጧቸውና ለእነርሱ ረዥምና አስቂኝ ስም ይወስኑ።

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር የዓረፍተ ነገር ድግግሞሽ
ብዙዎቹ የህፃናት መፃህፍት ታዳጊዎቹ ታሪኩን እንዲከታተሉና በንባብ እንዲቀላቀሉ የሚረዳ ተደጋጋሚ ዓረፍተ ነገር አላቸው። በልዩ ድምጽ በመታገዝ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ወይም የንባብ ፍጥነትን በመቀየር በማንበብ ጊዜ የተደጋገመው ዓረፍተ ነገር አጽንዖት ሊሰጠው ይችላል። ለምሳሌ፡- “ከእኛ ጋር ና” ሲል የሚጋብዝ የእጅ ምልክት ማከል ወይም የዓረፍተ ነገሩን መጨረሻ ማራዘም ይችላሉ፦ “እኛም ዘንድ ቦ-ታ አለን”።

ጓደኞችን ማስተናገድ
በመጽሐፉ ውስጥ ያለችው ልጅ ልጆቹን ወደ ዣንጥላ እንዲመጡና ከእርሷ ዘንድ “እንዲስተናገዱ” ትጋብዛለች። ልጆቹን በቤታቸው ማስተናገድ እንደሚፈልጉና ማንን ማስተናገድ እንደሚፈልጉ መጠየቅ ይችላሉ።
ታዳጊዎች እቤት ውስጥ ሲያስተናግዱ አንዳንድ ጊዜ ጨዋታቸውን ማካፈል ይከብዳቸዋል። በዚህ ላይ ተወያይተው በመጽሐፉ ውስጥ እንዳለው ዣንጥላ ልጅቷ ወደ መጽሐፉ እንዲገቡ ስትጋብዝ የልጅቷ ሆኖ እንደሚቀረው ሁሉ የግል ንብረታቸውም የእነርሱ እንደሆነ ማስረዳት ይችላሉ።
የQR ኮድ
ከ”ደስ የሚል ቢራቢሮ” ፕሮግራም ላይ ዘፈኑን በካን ሒኖኺት ማዳመጥ ይችላሉ። ዘፈኑን በድምጽና በእንቅስቃሴ መቀላቀል ይችላሉ። ግጥምና ዜማ፦ ዳቲያ ቤን ዶር ኦፕሬተር፦ አስቴር ራዳ፣ ኡሪ ባናይ፣ ሜታል ራዝ፣ አሚ ዌይንበርግ።”

ቤተሰብና ዣንጥላ
በአንድ ዣንጥላ ስር ስንት የቤተሰብ አባላት ሊገቡ ይችላሉ? በብርድ ልብስስ ስር ምን ያህል? በመመገቢያ ጠረጴዛው ስርስ? በመፅሃፉ ተነሳሽነት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በደስታና በሳቅ እንዴት ሁላችሁ በጋራ መሰባሰብ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይችላሉ።

የዝናብ ላይ የእግር ጉዞ
ዝናባማ በሆነ ቀን ራስዎን በቦት ጫማዎች፣ ኮትና ዣንጥላ ያስታጥቁና በዝናብ ውስጥ ለመራመድ ይውጡ! ወደ ኩሬዎቹ ውስጥ ገብተህ በዝናብ ጊዜ በአካባቢው የሚለዋወጡትን ልዩ ነገሮች መመልከት ትችላለህ – ምን ያህል ሰዎች ውጪ አሉ? ሰማዩ ምን ይመስላል? ዝናቡ መሬት ወይም ንጣፍ ጋር ሲገናኝ ምን ይሆናል? በአየር ውስጥ ምን ሽታ አለ?


"ጌታዬ ንጉስ ሆይ ሰላም"
አሚራ በአንድ ወቅት የተጫወተችውን ጨዋታ ለመጫወት አስባለች – እናንተም ትችላላችሁ! እንዴት ነው የምንጫወተው? ከተሳታፊዎቹ አንዱ “ንጉሱ” ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በፊቱ መጥተው “ሰላም ጌታዬ ንጉስ ሆይ!” የሚሉ “ልጆቹ” ናቸው። ንጉሱም መልሶ “ሰላም ውድ ልጆቼ! የት ነበራችሁ? ምንስ እያደረጋችሁ ነበር?” ልጆቹ የት እንደነበሩና ምን እንዳደረጉ ያለ ቃላት የሰውነት እንቅስቃሴዎችንና የፊት ገጽታዎችን በመጠቀም ማብራራት አለባቸው። ንጉሱም መገመት አለበት። ሚናዎችን መቀየር ይቻላል፤ የሚፈለግም ነው።
ለቤተሰብ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
በጋራ ማንበብ ሴቶችና ወንዶች ልጆች በታሪኩ ውስጥ የተለያዩ ገጸ-ባህርያት ያላቸውን እንዲለዩ ያስችላቸዋል። መለየቱ ሲመሰረት ለሌላው እንደ መራራትና መተሳሰብ ያሉ ውስብስብ ስሜቶች ላይ መወያየት ይችላሉ።
ውይይት - ለእርሱ ... እናት ብሆን
በቤተሰብዎ ውስጥ የእያንዳንዷና የእያንዳንዱ ሚናዎች ምንድን ናቸው? ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጋሉ? በመጽሐፉ መንፈስ ውስጥ በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሚናዎችን መቀየር ላይ አብረው መገመት ይችላሉ – ልጆቹ ከአያት ጋር ቢቀያየሩ ምን ያደርጋሉ? አያትስ ከእናት ጋር ቢቀያየር ምን ያደርጋል? እንዴትስ እርስ በርሳችሁ መረዳዳት ትችላላችሁ?
ታሪኩን ማዳመጥ
በሰልፉ ውስጥ ምን መጫዎት ይቻላል? በኦርኬስትራ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች እንዴት ይሰማሉ? – እነዚህ ሁሉና ሌሎችም ኮዱን ስካን በማድረግ ታሪኩን ሲያዳምጡ ይጠብቁዎታል።
ጨዋታ – ሙያዬ ነው
ገጸ ባህርይው ማን ነው፦ ዶክተር ወይስ ምናልባት ቀልደኛ? – በእያንዳንዱ ዙር ተሳታፊዎች አንድ ባለሙያን ይመርጡና በትወና አቅርበው ተሳታፊዎቹ ገጸ ባህርይው ማን እንደሆነ መገመት አለባቸው። ለመገመት ትንሽ ይከብዳል? – ፍንጭ መስጠት ይቻላል።
ወደ ሥዕላዊ መግለጫዎች መግባት
በታሪኩ ውስጥ ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጉ ነበር? መጽሐፉን ማገላበጥ፣ መቀየር የሚፈልጉትን ሰው መምረጥና እርስ በርስ መጋራት ይችላሉ፦ ጋጋሪውን መቀየር ይፈልጋሉ? በሰልፍ ውስጥ የሚጫወተውን?
ውይይት
ታሪኩ ስለ ጎረቤቶችና ግንኙነቶች ውይይትን ይጋብዛል፦ እናንተ የምታውቋቸው ጎረቤቶች እነማን እንደሆኑ በጋራ መወያየትና በአካባቢው ከሚኖረው ጉርብትና ጋር ለመተዋወቅ ስለ አንድ እንቅስቃሴ ማሰብ ትችላላችሁ። እናንተ ወላጆች ከልጅነታችሁ ጀምሮ የጎረቤቶች ታሪኮችን እንድታካፍሉ ተጋብዛችኋል፦ ጎረቤቶቻችሁ እነማን እንደነበሩና አብራችሁ ስላደረጋችሁት ነገር።
"በጣም ደስ የሚል - "ጎረቤቶችን መተዋወቅ
አንድ የሆነ ነገር አንድ ላይ ሠርታችሁ ለጎረቤቶች መስጠት ትችላላችሁ፦ ምግብ፣ ሥዕል ምናልባትም በር ላይ የምታስቀምጡት ደብዳቤ ሊሆን ይችላል። ወይም በቀላሉ ስለሰላማቸው እንዴት እንደሆኑ መጠየቅ ትችላላችሁ። በጣም ቀላሉ ደግሞ፦ ከጎረቤቶች ጋር ሲገናኙ በፈገግታ “ሰላም”፣ “እንዴት ናችሁ?” እና “መልካም ቀን!” ማለት።
በቤት ውስጥ አስደሳች ነው
በያዔል ቤት የሚደረጉ ብዙ አስደሳች ነገሮች አሉ! ሥዕሎችን ለማየት የተጋበዛችሁ ሲሆን የምትወዱትን ተግባር በመምረጥ በራሳችሁ ወይም ከተቀረው ቤተሰብ ጋር ለማድረግ ሞክሩ።
ከራሳችሁ የሆነ ቤት
በታሪኩ ውስጥ ያሉት ልጆች የሳጥኖች ሕንፃ ይገነባሉ፦ እናንተም ትችላላችሁ! የተለያየ መጠን ያላቸውን ሳጥኖች በመሰብሰብ ለእናንተ ወይም ለአሻንጉሊቶቹ ቤት ትገነባላችሁ። እናም ጎረቤቶችን እንዲጎበኙ መጋበዛችሁን እንዳትረሱ።