משחק
ילדים אוהבים לשחק והם עוסקים בכך בחלק משמעותי מהיום. דגדוגים או מחבואים או כל משחק אחר הם לא רק דרך ליהנות או להשתעשע, אלא גם אמצעי לחקור וללמוד את העולם, לגבש את הזהות ואת תחומי העניין, לתרגל מיומנויות רבות בכל היבט התפתחותי ולעבד חוויות שונות. לפניכם ספרים "משחקיים" וספרים על משחק, שיעוררו עניין והשראה לזמנים משותפים של הזדהות, של הנאה ושל היכרות עם העולם.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

የፋሲካ ልምዶች
ታሪኩ ለእናንተ ለወላጆች ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ስለምታስታውሷቸው ስለ ሴደር የምሽት ልማዶች ለልጆቻችሁ ለመንገር እድል ይሰጣል፦ አፊኮማን ከእናንተ በኩል ደብቀውባችሁ ነበር? ማንስ አገኘው? በልጅነት ጊዜ ስለ ፋሲካ ምን ትወዳላችሁ? ዛሬስ ምን ትወዳላችሁ – ወላጆችና ልጆች?
ፋሲካ ማን ያውቃል?
ከግብፅ ስትወጡ ከእናንተ ጋር የምትወስዷቸው ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? ከእንቁራሪቶች መቅሠፍት ላይ እንደ እንቁራሪት ማን ሊዘል ይችላል? ኮዱን ስካን ያድርጉና አዝናኝ የካርድ ጨዋታን ማተም ትችላላችሁ። ይህም ወደ ሴደር የምሽት ተሞክሯችሁ የሚጨምር ይሆናል።
አፊኮማንንና ትንሽን ነገር በመደበቅ የቤተሰብ አባላት እንዲፈልጉት መጠየቅ ትችላላችሁ። ወጥ ቤት ውስጥ ነው? ከሶፋው በታች? ወይስ ምናልባት በቁም ሳጥኑ ውስጥ? በሚቀጥለው ዙር እድለኛው አግኚ የመረጠውን ዕቃ ይደብቅና ሌሎቹ ደግሞ እንደገና ፍለጋ ይወጣሉ… መልካም እድል!

እንቁራሪቱ የት አለ?
በሴደር ምሽት አንድ ትንሽ እንቁራሪት ለመጎብኘት መጣች። ራሷም ላይ ጥንታዊ የግብፅ የራስ ሻሽ ነበር። በምስሎቹ ውስጥ ማሸብለልና ማግኘት ትችላላችሁ? በእናንተ አስተያየት በምስሎቹ ላይ የምትታየው ለምንድን ነው?

ለንባብ የሚሆን አጋዥ ሌንስ
ታዳጊዎች አካላዊ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ በንባብ ጊዜ ተቀራርቦ መቀመጥ፣ መተቃቀፍ፣ መነካካትና አልፎ አልፎ አንዳችሁ የሌላውን ዓይን መመልከት ይኖርባችኋል። በዚህ መንገድ ታዳጊዎቹ ፍቅርና ደህንነት እንዲሰማቸው ሲደረግ ታሪኩን ሞቅ ያለና ዘና የሚያደርግ ልምድ አድርገው ይወስዱታል።

መኮርኮርና ጨዋታዎች
ታዳጊዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ – የመኮርኮር ጨዋታዎችን ትወዳላችሁ? ምን አይነት ጨዋታዎችን አብረን እንድንጫወት ትወዳላችሁ? ምን እንድንጫወት ትፈልጋላችሁ? እንዲሁም በመፅሃፉ ውስጥ የእናትን የስልክ ጥሪ ማየት ትችላላችሁ – እናትየው ስልኩን ለመቀበል ስትሄድ ጋን-ያ ምን ተሰማት? መጠበቅ ሲኖርባችሁ ምን ይሰማችኋል?

ቤት ውስጥ ተራራ አለ
“ልክ በመጽሐፉ ውስጥ እንዳለው መጫወት ትችላላችሁ፦ ታዳጊው ወይም ከቤተሰቡ አባላት አንዱ እራሱን በብርድ ልብስ ሸፍኖ ወደ ተራራ ይለወጣል። ተራራውን መኮርኮር፣ መዳሰስና ማሠሥ ይቻላል፦ የተራራው እግር የት ነው? ራሱስ የት ነው?
* ለመነካት ወይም ለመኮርኮር የሚቸገሩ ልጆች ሊኖሩ ስለሚችሉ ከጨዋታው በፊት ማንም ሰው በማንኛውም ጊዜ “”በቃ”” ሊል እንደሚችል ማስታወሱ አስፈላጊ ነው ልክ እንደ መጽሐፉ።”

አንድ ላይ መንቀሳቀስ
በመጽሐፉ ውስጥ ብዙ የሰውነት እንቅስቃሴዎች አሉ፦ መዝለል፣ መደነስ፣ መንከባለል ወይም እግሮችን በአየር ላይ ማንሳት። ልክ እንደ ተራራው እንዲሁ ምስሎችን ማየትና የጋን-ያን እንቅስቃሴ ማስመሰል ይቻላል።
በድብብቆሽ መጫወት
ኑ ድብብቆሽ እንጫወት! ጣቶቻችንን በእጅ መዳፍ ውስጥ መደበቅ፣ አፍንጫችንን ሸፍነን መግለጥ፣ በብርድ ልብስ መደበቅ፣ ከሶፋው ጀርባ መደበቅ ወይም አሻንጉሊትን ከጀርባ መደበቅ እንችላለን።
መጀመሪያ መደበቅ የሚፈልገው ማነው?

ድመቱን ፈልጉ
ሜያው! ግራጫው ድመት የድብብቆሽ ጨዋታውን ተቀላቅሏል። በእያንዳንዱ ስዕላዊ መግለጫ ላይ እርሱን መፈለግ ይቻላል፤ ጅራቱን እንዳትረግጡ ብቻ ተጠንቀቁ …

ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ መጽሐፉን ወደ ጓደኛ እንዴት ይለውጡታል?
ከትንሽነታቸው ጀምሮ መጻሕፍትን ማንበብ ለታዳጊ ህፃናት እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። ነገር ግን በሁሉም አዲስ ነገር ላይ ጥያቄ እንደሚነሳው ሁሉ – መንገዱን እንዴት እናገኘዋለን? የእኛ ሀሳብ በዝግታና ቀስ በቀስ መተዋወቅ ነው – ታዳጊው በራሱ መንገድ ከመጽሐፉ ጋር መገናኘት ይችላል፦ በመንካት፣ በመክፈትና በመዝጋት እና በአፍ ውስጥ እንኳን “መቅመስ” ሳይቀር። ከዚያ ማንበብ ይችላሉ፦ በየቀኑ ትንሽ በትዕግስትና በደስታ እናነባለን። መጀመሪያ ላይ አንድ ገጽ እንኳን ማንበብ፣ መተዋወቅና መለማመድ ይችላሉ። እነሆ – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል!
התוכנית שלנו!
הִזְדַּמְּנוּת לִקְרִיאָה, לַחֲוָיָה וְלַהֲנָאָה – למדו עוד על התוכנית!

ውይይት - በአንድ ላይና በተናጠል
ብቻን ምን ማድረግ ይቻላል? አንድ ላይስ ምን ቢያደርጉ ይመረጣል? ከሌሎች ጋር መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ከልጆች ጋር መወያየትና ለራሳቸውም ምን ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስቡ አድርጉ። ከማን ጋር ነገሮችን በአንድ ላይ ማድረግ ይወዳሉ? የቤተሰብ አባላት? ጓደኞች? ምናልባትም የቤት እንስሳ?

ጨዋታ - በአንድ እግር
እናንተም በአንድ እግር ላይ መቆም ትችላላችሁ? ኑ እንሞክረው!
የጨዋታ ሳጥንን ይጣሉ፣ በአንድ እግር ላይ ይቁሙና ከሳጥኑ በወጣው ቁጥር መሠረት መቁጠር ይጀምሩ፦ አንድ፣ ሁለት፣ እ … ሊወድቁ ነው? አጠገብዎ ከሚገኝ ሰው እጅዎትን በመዘርጋት እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

የስራ ተሳትፎ
በቤት ውስጥ በመተባበር ደስ የሚያሰኙና ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን ዝርዝር ማዘጋጀት ይችላሉ፦ ክፍሉን ማስተካከል፣ ምግብ ማዘጋጀት ወይም የሚወዱትን መጽሐፍ ማንበብ። ከዚያም እያንዳንዱን ድርጊት በተለየ ካርድ ላይ ይቅረጹና ያስጊጡት። ካርዶቹን በልዩ ሳጥን ውስጥ ማቆየትና በየቀኑ አንድ ካርድ በማውጣት መመርመር፦ ዛሬ ቤቱን በመጥረግ መተባበር እንፈልጋለን? ወይስ በሚስብ የቤተሰብ ጨዋታ? ምናልባት በአዲስ ነገር ላይ መተባበር እንፈልጋለን?
እንቅስቃሴ - በአንድ ወይም በሁለት እግሮች ላይ
በቤት ውስጥ የእንቅስቃሴ መስመር ማዘጋጀትና በአንድ እግር፣ በሁለት እግሮች መገስገስና በአራትና በሦስት ላይ ራሱ … መሳብ ይችላሉ። ገመድ በመጠቀም ወለሉ ላይ መስመር ይፍጠሩና በእያንዳንዱ ጊዜ መስመሩን እያስረዘሙ ይራመዱ፦ አንድ ጊዜ በአንድ እግር ላይ በመዝለል፣ አንድ ጊዜ ትራስን ጭንቅላት ላይ በማድረግ ሚዛንን በመጠበቅ፣ አንድ ጊዜ በመሳብና አንድ ጊዜ ጥንድ በመሆን፣ እጆችን በማጣመር፤ ምክንያቱም በአንድ እግር ላይ ለሁለት መዝለል ስለሚቀልል ነው።

פינטרסט
פינטרסט – የእንቅስቃሴ ጨዋታዎች፣ የተሳትፎ ስራዎች፣ ፈጠራና መዝሙሮች በፒጃማ ቤተ መፃህፍት ፒንተረስት ውስጥ ባለው የመፅሃፍ ገጽ ላይ