סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ውይይት - ይህ በጣም ጥሩና በነፃ ነው
የሚያስደስቱዎና በነጻ የተሰጡዎ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? – ሊቁ በነጻ የተሰጡን በዓለማችን ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች የሚያቀርብበትን ምስል ማየትና እርስ በእርስ መጋራት ይችላሉ – እርስዎም ይደሰቱባቸዋል? ሌሎችስ የትኞቹ ነፃ ክፍያዎች ለእርስዎ ተወዳጆች ናቸው?
ደስታው የሁላችንም ነው
ደስታው የሁላችንም ነው
ስዕላዊ መግለጫዎች - ሴትና ወንድ ልጅ
በመጽሐፉ ውስጥ በተቀመጡት ስዕላዊ መግለጫዎች ላይ በብዛት አንዲት ልጃገረድና አንድ ወንድ ልጅ ይታያሉ። በመጽሃፉ ገፆች መካከል በመፈለግ አንድ ላይ ማሰብ ይችላሉ – ስዕላዊ መግለጫዎቹ ውስጥ ለመጨመር ለምን ሰዓሊዋ የመረጠች ይመስልዎታል?
ደስታው የሁላችንም ነው
ሐላና ጥሩ ሽታ
ሐላን ማዘጋጀት ይፈልጋሉ? – በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ እርስዎን የሚጠብቅ የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ አለ። መልካም ምግብ ይሁንልዎ፤ ቤቱን በሚሞላው ጥሩ መዓዛ ይደሰቱ።
ደስታው የሁላችንም ነው
ደስታው የሁላችንም ነው
መነጋገር
የሆነ ጊዜ የሆነ ነገር ለማድረግ ፈልጋችሁ የሆነ ሰው አስቸግሯችሁ ያውቃል? ምን ተሰማችሁ? ምን አደረጋችሁ ምንስ አላችሁ? – መጽሐፉ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎችን አንስቶ ለመወያየትና በጥሩም መንፈስ የመፍትሔ መንገዶችን የማግኛ እድል ነው።
መንገዱ ላይ የተኛው ዝሆን
የቤት ውስጥ የምላሾች ትንሽ ኩብ
ዘረፉኝ፣ ወሰዱብኝ፣ ረበሹኝ፣ አስቸገሩኝ – ምን ላድርግ? እንደ “እባክዎ” የሚልን ቃል በመጠቀም ስለ አዎንታዊ ግብረመልሶች አብራችሁ ማሰብ ትችላላችሁ፤ ወይም ምን እንደረበሻችሁ ማብራራት። ከወረቀት ትንሽ ኩብ መስራት ይቻላል፤ ሁሉንም አይነት አዎንታዊ አስተያየቶችን በጎኗ ጀርባ ላይ መጻፍና የተፃፈውን የሚገልጽ ምስል ማከል ይችላሉ። እንዲህ ባለ መልክ ችግር በሚያጋጥማችሁ ጊዜ ትንሿን ኩብ መጣልና እንዴት እንደምትመልስ ማየት ትችላለሁ።
መንገዱ ላይ የተኛው ዝሆን
ጨዋታ- እንስሳው ማን ነው?
በመጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ እንስሳት ይታያሉ- የትኛው እንስሳ ያለቅሳል? እንቁላል የሚጥለው የትኛው እንስሳ ነው? በጋጣ ውስጥ የሚኖረውስ እንስሳ የትኛው ነው? እስኪ እንወቅ፦ ከተሳታፊዎች አንዱ እንስሳን ይመርጣል። የተቀረው ቤተሰብ ደግሞ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የትኛውን እንስሳ እንደመረጠ ማወቅ ይኖርባቸዋል፤ መራጩም በሚሰጣቸው ፍንጮች ይታገዛሉ፦ የመረጥኩት እንስሳ ያለቅሳል፣ እንስሳዬ በበረት ይኖራል። የትኛው እንስሳ እንደተመረጠ እስኪያውቁ ድረስ ፍንጮችን ጨምር።
መንገዱ ላይ የተኛው ዝሆን
שיעור באיור - פיל!
למדו לצייר פיל יחד עם נעם נדב!
מגוון שיעורים באיור עם נעם נדב בעמוד היוטיוב שלנו, לצפייה לחצו >>
መንገዱ ላይ የተኛው ዝሆን
ክቡራትና ክቡራን - ተውኔቱ!
በልብሶች፣ በባርኔጣዎች፣ በመለዋወጫዎች ወይም በታሸጉ አሻንጉሊቶች በመታገዝ ታሪኩን መተወን ትችላላችሁ። የእንስሳቱን ድምጽ ማሰማት፣ እያንዳንዱ እንስሳ ከዝሆን ጋር ሲገናኝ እንዴት እንደሚሰማው ማሳየት ወይም በመንገዱ ላይ የተኛውን ዝሆን መሆን ይቻላል።
መንገዱ ላይ የተኛው ዝሆን
פינטרסט
פינטרסט – ጨዋታዎች፣ ፈጠራና ዝሆኖች በፒጃማ ቤተ መፃህፍት ፒንተረስት ውስጥ ባለው የመፅሃፍ ገጽ ላይ እርስዎን እየጠበቁ ነው
መንገዱ ላይ የተኛው ዝሆን