יום המשפחה
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር - መጻህፍት በሁሉም ቦታ
ልክ እንደ ብዙ ታዳጊዎች ባርላ አያቷን – “አሁን ምን እናደርጋለን?” ብሎ ይጠይቃል። አያት በቅርጫት ውስጥ ካሉት ሰርፕራይዞች መካከል በፈለጉት ጊዜ ሊያነቡት የሚችሉበት መጽሐፍም አለ። መጽሐፍ በየትኛውም ቦታ ለመውሰድ ቀላል የሆነ ራሱን የቻለ ዓለም ነው። ዶክተሩን ስትጠብቁ፣ በመጫወቻ ስፍራው ላይ ዘና ማለት በምትፈልጉበት ጊዜ ወይም በረዥም ጉዞ ውስጥ ስትሆኑ እናንተም መፅሃፍ በቦርሳችሁ በመያዝ መዝናናት ትችላላችሁ።

ውይይት - ከዘመዶች ጋር የሚኖሩ ጥሩ ጊዜያት
ስለ ታዳጊዎች ግንኙነት ከአያቶች ወይም ከሌሎች ጉልህ የቤተሰብ አባላት ጋር መነጋገርና መጠየቅ ትችላላችሁ – ምን አንድ ላይ ማድረግ ትወዳላችሁ? ከአያቶችህ ወይም ከአጎቶችህ ጋር ብቻ የምታደርጋቸው ልዩ ነገሮች አሉ? በቤታቸው ውስጥ ብቻ ያሉ ልዩ እቃዎችስ አሉ?


ምናብ የወለደው ተረት
የአያቴ ታሪኮች ባርላን ያስቁታል። ምክንያቱም ምናባዊ ስለሆኑና ያልተለመዱ ነገሮችም በምናብ ውስጥ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ነው። እንደ ‘በሾርባ ሳህን ውስጥ የወደቀው ጉማሬ’ ወይም ‘በሌሊት ብቻውን መሆንን የሚፈራ አንበሳ’ ወይም ሌላ ሐሳብን የመሰለ ታሪክ አብራችሁ ለመምጣት ሞክሩ። በአካባቢያችሁ ካለ ነገር ጀምሮ ታሪኩ የት እንደሚደርስ ማየት ትችላላችሁ።

አያት ኬክ ጋግራለች ...
አያት ገንፎ አብስላለች’ የሚለውን የጣት ጨዋታ ታውቃላችሁ? ተመሳሳይ ጨዋታ መጫወት ትችላላችሁ – ጣቶቻችሁን ወደ ውስጥ በማጣጠፍ አውራ ጣትን አውጡ፤ እነሆ – ‘ቀንድ አውጣ’ ኖራችሁ ማለት ነው። የሕፃኑ መዳፍ በትንሽ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ሊኖር ይችላል፦ ከዚያ እናንተ እንዲህ ትላላችሁ -“አያትና ባርላ ኬክ ጋገሩ፣ ዱቄት ጨመሩ፣ ስኳር ጨምሩ፣ እንቁላል ጨምረዋል…” ከእያንዳንዱ ምርት ጋር የህፃኑን መዳፍ በአውራ ጣት መንካት። ሚናዎችን መቀያየርም ይቻላል።

ለንባብ የሚሆን አጋዥ ሌንስ
ታዳጊዎች አካላዊ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ በንባብ ጊዜ ተቀራርቦ መቀመጥ፣ መተቃቀፍ፣ መነካካትና አልፎ አልፎ አንዳችሁ የሌላውን ዓይን መመልከት ይኖርባችኋል። በዚህ መንገድ ታዳጊዎቹ ፍቅርና ደህንነት እንዲሰማቸው ሲደረግ ታሪኩን ሞቅ ያለና ዘና የሚያደርግ ልምድ አድርገው ይወስዱታል።

መኮርኮርና ጨዋታዎች
ታዳጊዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ – የመኮርኮር ጨዋታዎችን ትወዳላችሁ? ምን አይነት ጨዋታዎችን አብረን እንድንጫወት ትወዳላችሁ? ምን እንድንጫወት ትፈልጋላችሁ? እንዲሁም በመፅሃፉ ውስጥ የእናትን የስልክ ጥሪ ማየት ትችላላችሁ – እናትየው ስልኩን ለመቀበል ስትሄድ ጋን-ያ ምን ተሰማት? መጠበቅ ሲኖርባችሁ ምን ይሰማችኋል?

ቤት ውስጥ ተራራ አለ
“ልክ በመጽሐፉ ውስጥ እንዳለው መጫወት ትችላላችሁ፦ ታዳጊው ወይም ከቤተሰቡ አባላት አንዱ እራሱን በብርድ ልብስ ሸፍኖ ወደ ተራራ ይለወጣል። ተራራውን መኮርኮር፣ መዳሰስና ማሠሥ ይቻላል፦ የተራራው እግር የት ነው? ራሱስ የት ነው?
* ለመነካት ወይም ለመኮርኮር የሚቸገሩ ልጆች ሊኖሩ ስለሚችሉ ከጨዋታው በፊት ማንም ሰው በማንኛውም ጊዜ “”በቃ”” ሊል እንደሚችል ማስታወሱ አስፈላጊ ነው ልክ እንደ መጽሐፉ።”

አንድ ላይ መንቀሳቀስ
በመጽሐፉ ውስጥ ብዙ የሰውነት እንቅስቃሴዎች አሉ፦ መዝለል፣ መደነስ፣ መንከባለል ወይም እግሮችን በአየር ላይ ማንሳት። ልክ እንደ ተራራው እንዲሁ ምስሎችን ማየትና የጋን-ያን እንቅስቃሴ ማስመሰል ይቻላል።
በድብብቆሽ መጫወት
ኑ ድብብቆሽ እንጫወት! ጣቶቻችንን በእጅ መዳፍ ውስጥ መደበቅ፣ አፍንጫችንን ሸፍነን መግለጥ፣ በብርድ ልብስ መደበቅ፣ ከሶፋው ጀርባ መደበቅ ወይም አሻንጉሊትን ከጀርባ መደበቅ እንችላለን።
መጀመሪያ መደበቅ የሚፈልገው ማነው?

ድመቱን ፈልጉ
ሜያው! ግራጫው ድመት የድብብቆሽ ጨዋታውን ተቀላቅሏል። በእያንዳንዱ ስዕላዊ መግለጫ ላይ እርሱን መፈለግ ይቻላል፤ ጅራቱን እንዳትረግጡ ብቻ ተጠንቀቁ …

ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ መጽሐፉን ወደ ጓደኛ እንዴት ይለውጡታል?
ከትንሽነታቸው ጀምሮ መጻሕፍትን ማንበብ ለታዳጊ ህፃናት እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። ነገር ግን በሁሉም አዲስ ነገር ላይ ጥያቄ እንደሚነሳው ሁሉ – መንገዱን እንዴት እናገኘዋለን? የእኛ ሀሳብ በዝግታና ቀስ በቀስ መተዋወቅ ነው – ታዳጊው በራሱ መንገድ ከመጽሐፉ ጋር መገናኘት ይችላል፦ በመንካት፣ በመክፈትና በመዝጋት እና በአፍ ውስጥ እንኳን “መቅመስ” ሳይቀር። ከዚያ ማንበብ ይችላሉ፦ በየቀኑ ትንሽ በትዕግስትና በደስታ እናነባለን። መጀመሪያ ላይ አንድ ገጽ እንኳን ማንበብ፣ መተዋወቅና መለማመድ ይችላሉ። እነሆ – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል!
התוכנית שלנו!
הִזְדַּמְּנוּת לִקְרִיאָה, לַחֲוָיָה וְלַהֲנָאָה – למדו עוד על התוכנית!
ውይይት
በቤትዎ ውስጥ ምን ይወዳሉ? በቤት ውስጥ የሚኖረውስ ማነው? ታሪኩን ተከትለው ከልጆች ጋር ስለ ቤትዎ ማውራት ይችላሉ፤ ምንና ማን በውስጡ እንዳለ፦ የቤተሰብ አባላት፣ የቤት እንስሳት፣ ተወዳጅ አሻንጉሊቶችና ሌላስ ማን? (በአንቀጹ መጀመርያ ላይ የታየ ነው)

ሌላ ተጨማሪ ሳይሆን ሳጥን
“ይሄ ቤት ማለት በጠቅላላው የሚኖሩበት ሳጥን ነው…” ኮዱን ስካን ያድርጉና በዳቲያ ቤን ዶር የተጻፈውንና የተቀናበረውን ዘፈን ይቀላቀሉ።
ጨዋታ - ድብብቆሽ
የት መደበቅ ይገባል? – እንደ ያስሚንና እናቷ ታዳጊው ሕጻን ሲደበቅና ወላጁ ሲፈልገው እርስዎም ድብብቆሽ መጫወት ይችላሉ። ተሳካ? – ተጨማሪ ዙር መጀመርና ቤተሰብ አባላትን ማሳተፍ ይችላሉ።
እኛም እየገነባን ነው
እርስዎም ከሣጥን ቤት መሥራት ይችላሉ። የሚያስፈልገው ትልቅ የካርቶን ሳጥን፣ ነፃ ጊዜና ጥሩ ስሜት ብቻ ነው። አሁን እርስዎ በገነቡት ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ጓደኞችን መጋበዝ ይችላሉ። ትንሽ ሳጥን ብቻ ነው ያገኙት? – ወደ አሻንጉሊቶች ቤት መቀየር ይችላሉ።
መነጋገር - ማን ሊያግዝ ይችላል?
ሁሉም ሰው ሌሎችን ታዳጊ ሕጻናትን እንኳን ሳይቀር ሊያግዝ ይችላል። ታዳጊ ሕጻናቱን ሌሎችን በምን እንደሚያግዙ መጠየቅ ወይም በሚከሰትበት ጊዜ እንደሚረዷቸው መንገር ይችላሉ፦ “ጠረጴዛውን ለማዘጋጀት እንደረዳኸኝ አስታውስ?”፣ “መጫዎቻዎቹን ለማዘጋጀት እንዴት እንደረዳሽኝ ተመልከቺ!”
ታሪኩን ማዳመጥ
“ኖኒና እናቱ” የሚለውን ታሪክ ማዳመጥ ይፈልጋሉ? – የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና የታሪኩ የድምጽ ቅጂ ላይ ይደርሳሉ። በሚያሽከረክሩበት ጊዜ፣ በሚጫወቱበት ወይም አብረው ተቀምጠው መጽሐፍ በሚያገላብጡበት ጊዜ ማዳመጥ ይችላሉ።
ታሪኩ በምስል
ስዕሎቹ የታሪኩ አካል ሲሆኑ በእነርሱ አማካኝነት ታዳጊ ሕጻናቱ የታሪኩን ሂደትና ዝርዝሮቹን ያውቃሉ፤ ያስታውሳሉም። ስዕላዊ መግለጫዎቹን አንድ ላይ በማየት ኖኒ ለእናቱ የሰጣትን ዕቃዎች መፈለግ ይቻላል። ‘ቦርሳ የተሳለበት ቦታ የት ነው?’ እና ‘የኮት ምስል የት አለ?’
ጨዋታ - የእቃዎች ግንብ
በእናት ላይ በተቆለሉ ነገሮች በመጠቀም በተራ የእቃዎችን ግንብ መገንባት ይችላሉ፦ በጥንቃቄ አንዱን በሌላው ላይ በማድረግ ኩቦችን፣ መጫወቻዎችን፣ ኮፍያዎችን፣ ቦርሳዎችንና ማከል የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ማስቀመጥ ይችላሉ።
እኛም መርዳት እንችላለን!
ታዳጊዎች በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይችላሉ? ብዙ ነገሮችን! በመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ ብርጭቆዎችን ማስቀመጥ፣ በትንሽ መጥረጊያ መጥረግ፣ የቤት እንስሳቱን መመገብ እናም ኩኪዎችን ማቅረብ ይችላሉ። ታዳጊው በቤት ውስጥ እንዴት መርዳት እንደሚችል እና በምን መሳተፍ እንደሚችሉ ወይም ምን እንደሚፈልጉ ማውራት እና ማቅረብ ጥሩ ሀሳብ ነው።
በቤተሰቡ ውስጥ ያለው ማነው?
በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ ኩኪዎችን ለሌሎች የቤተሰብ አባላት፦ ለአያት፣ አጎት፣ እህት፣ የአጎት ልጅ ይሰጣል። እና የእርስዎ ቤተሰብ አባላት እነማን ናቸው? ስለቤተሰብ አባላት መንገር፣ ስሞቻቸውን እና የያዙትን ሚናዎች መናገር ይችላሉ፣ ለምሳሌ፦ “ሴት አያቴ ብራሃ”፣ “አጎት ባሮክ” እና የቤተሰብ ፎቶዎችን መጠቀም ይችላሉ። እና ያሰራጩ–ኩኪዎች ነበሩዎት…
ባንድነት አንዳንድ ቀላል ያለ ምግብና መጠጥ እናዘጋጅ!
እንደ ቸኮሌት ኳሶች፣ የፍራፍሬ ሳህን ወይም የተቆረጠ ኪያር የመሳሰሉ ምግቦችን አብረው ማዘጋጀት ይችላሉ። የጨዋታ ሊጥ በመጠቀም “የማስመሰል” ምግቦችን ማዘጋጀት እና በቤት ውስጥ ላሉ አሻንጉሊቶች ማቅረብ ይችላሉ።
ጨዋታ፦ አያቴ ኩኪዎች ነበሯት…
“ሴት አያቴ ገንፎ ሰሩ (Grandma made porridge)” የሚለውን ጨዋታ ያውቃሉ? “ልጁ ኩኪዎች ነበረው (The child had cookies)” በተመሳሳይ መንገድ መጫወት ይቻላል፣ ህፃኑ እጇን ወይም እጁን ከፍቶ ወላጁ መቁጠር ይጀምራል፦ “ትንሹ ወንድ ልጅ/ልጃገረዷ ኩኪዎች ነበራት እና አንዱን ለሴት አያቴ (አውራ ጣት በመያዝ)፣ እና አንዱን ለአጎቴ (ጠቋሚ ጣትን በመያዝ) ወዘተ ሰጠ/ች። እና ስለዚህ አንድን የቤተሰብ አባል ለእያንዳንዱ ሰው በመመደብ ጣቶቹን ይቆጥራሉ። የመጨረሻውን ኩኪ ለማን ይሰጣሉ?