חַגִּים וְיָמִים מְיֻחָדִים
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

טיפ לקריאה
ከልማዶች፣ ምልክቶችና የበዓል ምግቦች ጋር የተያያዙ መፃህፍት የበዓሉን ልምድ የሚያበለጽጉት ሲሆን ለእርሱም መጠባበቅንና ጉጉትን ለማዳበር ይረዳሉ። በበዓል ወቅት ከልጆችዎ ጋር መጽሐፉን ማንበብ አለብዎት። ከዚያም በኋላ እንኳን – ውብ የሆኑትን ጊዜያት አንድ ላይ የሚያስታውሱ ዜማዎች፣ ቀለሞች፤ ጣዕምና ሽታዎች ይኖራሉ።
ልያ ናኦር በ1935 በሄርጼሊያ ተወለደች። ለህፃናት መጽሃፎችን፣ ድራማዎችን፣ ስክሪፕቶችንና መዝሙሮችን የደረሰች ሲሆን በርካታ መጽሃፎችን ወደ ዕብራይስጥ ተርጉማለች። ተከታታይ የሆነው “ዶክተር ሴውስ” ከእነርሱ ውስጥ ይጠቀሳል። መጻህፍቶቿና የትርጉም ስራዎቿ ብዙ ሽልማቶችን አሸንፈዋል።

ውይይት - በጋራ ማብሰልና መርካት
በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት ስለሚወዷቸው ምግቦችና ስለ ዝግጅቱ ሂደት ማውራት ይችላሉ – ምን ዓይነት ንጥረ ነገሮች ጥቅም ላይ ይውላሉ? በምን መሳሪያዎች? በእያንዳንዱ ደረጃ ምን እናደርጋለን?


ምስሎቹ ምንድን ናቸው?
በእያንዳንዱ ንባብ በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጹት ምስሎች ውስጥ አዲስ አስደሳች ዝርዝሮችን ይፈልጉ – በቀቀኑ የት አለ? በእያንዳንዱ ምስል ላይ ምን እያደረገ ነው? አባትየውና ልጆቹ ምን እያደረጉ ነው? በጠረጴዛው ላይ ምን ምን ዕቃዎችና ቁሳቁሶች አሉ? በኩሽና ውስጥ ምን ዓይነት ዕቃዎችን ያውቃሉ? ምናልባትም በቤትዎና በኩሽናዎ ውስጥ ሊያገኟቸው ይችሉ ይሆናል።

የፓን ኬክን የምግብ
የፓን ኬክን የምግብ አዘገጃጀት
ግብዓቶች፡-
5 ድንች
አንድ ትልቅ ቀይ ሽንኩርት
2 እንቁላል
ግማሽ ኩባያ ዱቄት
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ስኳር
አንድ የሻይ ማንኪያ ጨው
ለመጥበሻ የሚሆን ዘይት
የዝግጅት መመሪያዎች፡-
1. ቀይ ሽንኩርቱንና ድንቹን በድስት ውስጥ በመፈቅፈቅ ይላጡ። ፈሳሾቹን በደንብ በማሸት በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ያስቀምጡ
።
2. ሁሉንም ሌሎች ንጥረ ነገሮች ወደ ሳህኑ ውስጥ ይጨምሩ – እንቁላል፣ ዱቄት፣ ስኳርና ጨው (ከፈለጉም ተጨማሪ ቅመሞች) እና በደንብ ይደባልቁ።
3. በሁለቱም በኩል ወርቃማ እስኪሆን ድረስ ፓን ኬኩን ሞቅ ባለ ዘይት (አንድ ጭልፋ ወይም ጭልፋ ተኩል ለእያንዳንዱ ፍሬ) በጥንቃቄ ይጥበሱት።
4. በሚመጥ ወረቀት ላይ ያስቀምጡና መልካም ምግብ ይሁንልዎ!

ደረጃ በደረጃ
ፓን ኬክን ወይም ሌላ ተወዳጅ ምግብ በሚዘጋጅበት ጊዜ የዝግጅቱን ሂደት ፎቶግራፎች ማንሳት ይችላሉ። ከፎቶዎቹ ውስጥ ደረጃዎችንና የእርምጃዎችንና የንጥረ ነገሮችን ስም ለመድገም የሚረዳ ትንሽ አልበም መስራት ይችላሉ፦

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚበጅ ምክር
አንድ መጽሐፍ ለአንድ ልዩ ዝግጅት ለመዘጋጀት ወይም ካለፈ ክስተት ላይ ትውስታዎችን ለመሰብሰብ ይረዳል። የበዓል ሰሞን ለምሳሌ ከበዓል ጋር የተያያዘ መጽሐፍ መምረጥና መወያየት ይችላሉ፦ በበዓል ቀን ምን ምን ዝግጅቶች ለእርስዎ ታቅደዋል? ሲቃረብስ ወላጆችና ልጆች አብረው እንዴት ማዘጋጀት ይችላሉ? ለፑሪም ዝግጅት አንድ ላይ ልብስን መላበስ ወይም ምግቦችን መላክ ይችላሉ። ከበዓል በኋላም መጽሐፉን እንደገና ማንበብና በእርሱ በመታገዝ አብረው ያጋጠሟችሁን መልካም ጊዜያት ያስታውሱ።

መላበሶች በምስሎች
“በመጽሐፉ ውስጥ የጠፈር ተመራማሪ አለባበስ የት ላይ ነው ያለው? ንግስት አስቴርን፣ የእሳት አደጋ ተዋጊዎችን፣ ፖሊሶችን ወይም አልበርት አንስታይንን በተመለከተስ? በምስሎቹ ውስጥ ልብሶችን መፈለግ ትችላላችሁ። በተለይ የትኛውን መላበስ ይወዳሉ?
አልበርት አንስታይን ማን ነበር?
አልበርት አንስታይን [1879-1955] የጀርመን ተወላጅ አይሁዳዊ ሳይንቲስት ነበር። እርሱ ባዘጋጀው “”የአንፃራዊነት ፅንሰ-ሀሳብ”” ባደረጋቸው ሌሎች ጥናቶች በመታገዝ በሳይንሱ ዓለምና በተፈጥሮ፣ በጊዜ ብሎም በዩኒቨርስ ህጎች ግንዛቤ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። አንስታይን በቀልድና ምናብ ተሰጥኦ የተካነ ነበር። ለሰላምና ለወንድማማችነት የሰራ ሲሆን ከመላው ዓለም ካሉ ልጆች ጋር መጻጻፍ ይወድ ነበር። አንስታይን በኢየሩሳሌምና በእስራኤል ግዛት ስር የዕብራይስጥ ዩኒቨርስቲ እንዲቋቋም ድጋፍ አድርጓል።”

የፋሲካ ልምዶች
ታሪኩ ለእናንተ ለወላጆች ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ስለምታስታውሷቸው ስለ ሴደር የምሽት ልማዶች ለልጆቻችሁ ለመንገር እድል ይሰጣል፦ አፊኮማን ከእናንተ በኩል ደብቀውባችሁ ነበር? ማንስ አገኘው? በልጅነት ጊዜ ስለ ፋሲካ ምን ትወዳላችሁ? ዛሬስ ምን ትወዳላችሁ – ወላጆችና ልጆች?
ፋሲካ ማን ያውቃል?
ከግብፅ ስትወጡ ከእናንተ ጋር የምትወስዷቸው ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? ከእንቁራሪቶች መቅሠፍት ላይ እንደ እንቁራሪት ማን ሊዘል ይችላል? ኮዱን ስካን ያድርጉና አዝናኝ የካርድ ጨዋታን ማተም ትችላላችሁ። ይህም ወደ ሴደር የምሽት ተሞክሯችሁ የሚጨምር ይሆናል።
አፊኮማንንና ትንሽን ነገር በመደበቅ የቤተሰብ አባላት እንዲፈልጉት መጠየቅ ትችላላችሁ። ወጥ ቤት ውስጥ ነው? ከሶፋው በታች? ወይስ ምናልባት በቁም ሳጥኑ ውስጥ? በሚቀጥለው ዙር እድለኛው አግኚ የመረጠውን ዕቃ ይደብቅና ሌሎቹ ደግሞ እንደገና ፍለጋ ይወጣሉ… መልካም እድል!

እንቁራሪቱ የት አለ?
በሴደር ምሽት አንድ ትንሽ እንቁራሪት ለመጎብኘት መጣች። ራሷም ላይ ጥንታዊ የግብፅ የራስ ሻሽ ነበር። በምስሎቹ ውስጥ ማሸብለልና ማግኘት ትችላላችሁ? በእናንተ አስተያየት በምስሎቹ ላይ የምትታየው ለምንድን ነው?

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር - መጻህፍት በሁሉም ቦታ
ልክ እንደ ብዙ ታዳጊዎች ባርላ አያቷን – “አሁን ምን እናደርጋለን?” ብሎ ይጠይቃል። አያት በቅርጫት ውስጥ ካሉት ሰርፕራይዞች መካከል በፈለጉት ጊዜ ሊያነቡት የሚችሉበት መጽሐፍም አለ። መጽሐፍ በየትኛውም ቦታ ለመውሰድ ቀላል የሆነ ራሱን የቻለ ዓለም ነው። ዶክተሩን ስትጠብቁ፣ በመጫወቻ ስፍራው ላይ ዘና ማለት በምትፈልጉበት ጊዜ ወይም በረዥም ጉዞ ውስጥ ስትሆኑ እናንተም መፅሃፍ በቦርሳችሁ በመያዝ መዝናናት ትችላላችሁ።

ውይይት - ከዘመዶች ጋር የሚኖሩ ጥሩ ጊዜያት
ስለ ታዳጊዎች ግንኙነት ከአያቶች ወይም ከሌሎች ጉልህ የቤተሰብ አባላት ጋር መነጋገርና መጠየቅ ትችላላችሁ – ምን አንድ ላይ ማድረግ ትወዳላችሁ? ከአያቶችህ ወይም ከአጎቶችህ ጋር ብቻ የምታደርጋቸው ልዩ ነገሮች አሉ? በቤታቸው ውስጥ ብቻ ያሉ ልዩ እቃዎችስ አሉ?


ምናብ የወለደው ተረት
የአያቴ ታሪኮች ባርላን ያስቁታል። ምክንያቱም ምናባዊ ስለሆኑና ያልተለመዱ ነገሮችም በምናብ ውስጥ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ነው። እንደ ‘በሾርባ ሳህን ውስጥ የወደቀው ጉማሬ’ ወይም ‘በሌሊት ብቻውን መሆንን የሚፈራ አንበሳ’ ወይም ሌላ ሐሳብን የመሰለ ታሪክ አብራችሁ ለመምጣት ሞክሩ። በአካባቢያችሁ ካለ ነገር ጀምሮ ታሪኩ የት እንደሚደርስ ማየት ትችላላችሁ።

አያት ኬክ ጋግራለች ...
አያት ገንፎ አብስላለች’ የሚለውን የጣት ጨዋታ ታውቃላችሁ? ተመሳሳይ ጨዋታ መጫወት ትችላላችሁ – ጣቶቻችሁን ወደ ውስጥ በማጣጠፍ አውራ ጣትን አውጡ፤ እነሆ – ‘ቀንድ አውጣ’ ኖራችሁ ማለት ነው። የሕፃኑ መዳፍ በትንሽ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ሊኖር ይችላል፦ ከዚያ እናንተ እንዲህ ትላላችሁ -“አያትና ባርላ ኬክ ጋገሩ፣ ዱቄት ጨመሩ፣ ስኳር ጨምሩ፣ እንቁላል ጨምረዋል…” ከእያንዳንዱ ምርት ጋር የህፃኑን መዳፍ በአውራ ጣት መንካት። ሚናዎችን መቀያየርም ይቻላል።

ለንባብ የሚሆን አጋዥ ሌንስ
ታዳጊዎች አካላዊ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ በንባብ ጊዜ ተቀራርቦ መቀመጥ፣ መተቃቀፍ፣ መነካካትና አልፎ አልፎ አንዳችሁ የሌላውን ዓይን መመልከት ይኖርባችኋል። በዚህ መንገድ ታዳጊዎቹ ፍቅርና ደህንነት እንዲሰማቸው ሲደረግ ታሪኩን ሞቅ ያለና ዘና የሚያደርግ ልምድ አድርገው ይወስዱታል።

መኮርኮርና ጨዋታዎች
ታዳጊዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ – የመኮርኮር ጨዋታዎችን ትወዳላችሁ? ምን አይነት ጨዋታዎችን አብረን እንድንጫወት ትወዳላችሁ? ምን እንድንጫወት ትፈልጋላችሁ? እንዲሁም በመፅሃፉ ውስጥ የእናትን የስልክ ጥሪ ማየት ትችላላችሁ – እናትየው ስልኩን ለመቀበል ስትሄድ ጋን-ያ ምን ተሰማት? መጠበቅ ሲኖርባችሁ ምን ይሰማችኋል?

ቤት ውስጥ ተራራ አለ
“ልክ በመጽሐፉ ውስጥ እንዳለው መጫወት ትችላላችሁ፦ ታዳጊው ወይም ከቤተሰቡ አባላት አንዱ እራሱን በብርድ ልብስ ሸፍኖ ወደ ተራራ ይለወጣል። ተራራውን መኮርኮር፣ መዳሰስና ማሠሥ ይቻላል፦ የተራራው እግር የት ነው? ራሱስ የት ነው?
* ለመነካት ወይም ለመኮርኮር የሚቸገሩ ልጆች ሊኖሩ ስለሚችሉ ከጨዋታው በፊት ማንም ሰው በማንኛውም ጊዜ “”በቃ”” ሊል እንደሚችል ማስታወሱ አስፈላጊ ነው ልክ እንደ መጽሐፉ።”

አንድ ላይ መንቀሳቀስ
በመጽሐፉ ውስጥ ብዙ የሰውነት እንቅስቃሴዎች አሉ፦ መዝለል፣ መደነስ፣ መንከባለል ወይም እግሮችን በአየር ላይ ማንሳት። ልክ እንደ ተራራው እንዲሁ ምስሎችን ማየትና የጋን-ያን እንቅስቃሴ ማስመሰል ይቻላል።
ለቤተሰብ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
በጋራ ማንበብ ሴቶችና ወንዶች ልጆች በታሪኩ ውስጥ የተለያዩ ገጸ-ባህርያት ያላቸውን እንዲለዩ ያስችላቸዋል። መለየቱ ሲመሰረት ለሌላው እንደ መራራትና መተሳሰብ ያሉ ውስብስብ ስሜቶች ላይ መወያየት ይችላሉ።
ውይይት - ለእርሱ ... እናት ብሆን
በቤተሰብዎ ውስጥ የእያንዳንዷና የእያንዳንዱ ሚናዎች ምንድን ናቸው? ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጋሉ? በመጽሐፉ መንፈስ ውስጥ በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሚናዎችን መቀየር ላይ አብረው መገመት ይችላሉ – ልጆቹ ከአያት ጋር ቢቀያየሩ ምን ያደርጋሉ? አያትስ ከእናት ጋር ቢቀያየር ምን ያደርጋል? እንዴትስ እርስ በርሳችሁ መረዳዳት ትችላላችሁ?
ታሪኩን ማዳመጥ
በሰልፉ ውስጥ ምን መጫዎት ይቻላል? በኦርኬስትራ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች እንዴት ይሰማሉ? – እነዚህ ሁሉና ሌሎችም ኮዱን ስካን በማድረግ ታሪኩን ሲያዳምጡ ይጠብቁዎታል።
ጨዋታ – ሙያዬ ነው
ገጸ ባህርይው ማን ነው፦ ዶክተር ወይስ ምናልባት ቀልደኛ? – በእያንዳንዱ ዙር ተሳታፊዎች አንድ ባለሙያን ይመርጡና በትወና አቅርበው ተሳታፊዎቹ ገጸ ባህርይው ማን እንደሆነ መገመት አለባቸው። ለመገመት ትንሽ ይከብዳል? – ፍንጭ መስጠት ይቻላል።
ወደ ሥዕላዊ መግለጫዎች መግባት
በታሪኩ ውስጥ ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጉ ነበር? መጽሐፉን ማገላበጥ፣ መቀየር የሚፈልጉትን ሰው መምረጥና እርስ በርስ መጋራት ይችላሉ፦ ጋጋሪውን መቀየር ይፈልጋሉ? በሰልፍ ውስጥ የሚጫወተውን?

የጨዋታዎች ጨዋታ
በመጽሐፉ ውስጥ ባሉት ሥዕሎች በመታገዝ የሰንበቱን ዳቦ የማዘጋጀት ሂደቱን ማየትና በውስጡ ያሉትን የተለያዩ ደረጃዎች መረዳት ይችላሉ። አንድ ላይ አንድን ምግብ ማዘጋጀትና የዝግጅት ሂደቱን ፎቶግራፍ ማንሳት ይችላሉ። በዚህ መንገድ ዝግጅቱን ማስታወስ፣ በፎቶዎች ላይ አንድ ላይ መመልከትና በሚያምር ጣፋጭ ምርት መኩራት ይችላሉ። የሰንበት ዳቦ የምግብ አሰራር ለሊጡ፡- 1 ኪሎ ግራም ዱቄት ½ ኩባያ ስኳር 2 የሾርባ ማንኪያ እርሾ 2 ኩባያ የሞቀ ውሃ ½ ኩባያ ዘይት 2 እንቁላሎች (አማራጭ፤ ያለ እንቁላል ይችላሉ) 1 የሾርባ ማንኪያ ጨው መቀቢያ እንቁላል ወይም ትንሽ ዘይት የዝግጅት ደረጃዎች፡- 1. ዱቄት፣ ስኳርና እርሾ በአንድ ትልቅ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ መቀላቀል። 2. የተቀሩትን ንጥረ ነገሮች በመጨመር ዱቄቱ ጉትትና ልስልስ እስኪል ድረስ ለ10 ደቂቃ ያህል በደንብ ማስቀመጥ። 3. ጎድጓዳ ሳህኑን በፎጣ ወይም በፕላስቲክ ከረጢት በመሸፈን ዱቄቱ መጠኑ በእጥፍ እስኪያድግ ድረስ እንዲነሳ ማድረግ። 4. ከሊጡ የሰንበትን ዳቦ ማዘጋጀት – ትንሽ ወይም ትልቅ የሰንበት ዳቦ ማዘጋጀት ይችላሉ። የሰንበት ዳቦውን በእንቁላል ወይም በዘይት መቀባት ይችላሉ። 5. ወርቃማ መሆን እስኪጀምር ድረስ ለግማሽ ሰዓት ያህል በምድጃ ውስጥ በአማካይ ሙቀት መጋገር። መልካም ምግብ!
ውይይት - የእኛ ሰንበት
“መልካሙ የሰንበት ቀን ጥቂት ቆይቶ ወደ እኛ ይወርዳል”
[ሰንበት፣ ሽሙኤል ባስ]
የሜዳ አህያዋ ታሪክ ሰንበት ስለሚያመጣው ልዩ ነገር ለመናገር እድል ይሰጣል። ታዳጊዎቹን በሰንበት ቀን ምን ማድረግ እንደሚወዱ መጠየቅና እናንተው ወላጆች የምትወዷቸውን ነገሮች አካፍላቸው።
በልብሶቹ የቁም ሳጥን ውስጥ
ሸሚዝ? የዋና ልብስ? ምናልባት ቀሚስ? – ወደ ቁም ሣጥኑ ውስጥ በመመልከት የሚወዷቸውን ልብሶች ይፈልጉና አብዛኛውን ጊዜ መቼ እንደሚለብሷቸው መተረክ ይኖርብዎታል፦ የክረምት ወይስ የበጋ ልብስ፣ የበዓል ዝግጅት ልብስና በተለዬ መልኩ የሚወዱት ልብስ።
ከሜዳ አህያዋ ጋር መዘመርና መደነስ
የ”የሜዳ አህያዋ ፒጃማ የምትለብሰው ለምንድን ነው?” ስንኞች የተዘጋጁ ሲሆን የልጆች ተወዳጅ ዘፈኖች ናቸው። አብራችሁ ለመዝፈንና ለመደነስ የQR ኮዱን ስካን ማድረግ አለባችሁ።
ስዕላዊ መግለጫዎች - የሜዳ አህያና ጓደኞች
የሜዳ አህያዋ ጓደኞች በመጽሃፉ ውስጥ በተገለጹት ስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ይታያሉ፦ አብረው ማሰስ፣ ጓደኞችን ማግኘት፣ የእንስሳትን ስም አንድ ላይ ማለትና እነርሱን መወከል ይችላሉ። በሚቀጥለው ደረጃ የሚታወቀውን እንስሳ ስም መጥቀስና በመጽሐፉ ውስጥ ባሉት ስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ መፈለግ ይችላሉ።
በድብብቆሽ መጫወት
ኑ ድብብቆሽ እንጫወት! ጣቶቻችንን በእጅ መዳፍ ውስጥ መደበቅ፣ አፍንጫችንን ሸፍነን መግለጥ፣ በብርድ ልብስ መደበቅ፣ ከሶፋው ጀርባ መደበቅ ወይም አሻንጉሊትን ከጀርባ መደበቅ እንችላለን።
መጀመሪያ መደበቅ የሚፈልገው ማነው?
ድመቱን ፈልጉ
ሜያው! ግራጫው ድመት የድብብቆሽ ጨዋታውን ተቀላቅሏል። በእያንዳንዱ ስዕላዊ መግለጫ ላይ እርሱን መፈለግ ይቻላል፤ ጅራቱን እንዳትረግጡ ብቻ ተጠንቀቁ …
ለንባብ ጠቃሚ ምክር፦ መጽሐፉን ወደ ጓደኛ እንዴት ይለውጡታል?
ከትንሽነታቸው ጀምሮ መጻሕፍትን ማንበብ ለታዳጊ ህፃናት እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። ነገር ግን በሁሉም አዲስ ነገር ላይ ጥያቄ እንደሚነሳው ሁሉ – መንገዱን እንዴት እናገኘዋለን? የእኛ ሀሳብ በዝግታና ቀስ በቀስ መተዋወቅ ነው – ታዳጊው በራሱ መንገድ ከመጽሐፉ ጋር መገናኘት ይችላል፦ በመንካት፣ በመክፈትና በመዝጋት እና በአፍ ውስጥ እንኳን “መቅመስ” ሳይቀር። ከዚያ ማንበብ ይችላሉ፦ በየቀኑ ትንሽ በትዕግስትና በደስታ እናነባለን። መጀመሪያ ላይ አንድ ገጽ እንኳን ማንበብ፣ መተዋወቅና መለማመድ ይችላሉ። እነሆ – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል!
התוכנית שלנו!
הִזְדַּמְּנוּת לִקְרִיאָה, לַחֲוָיָה וְלַהֲנָאָה – למדו עוד על התוכנית!
ውይይት
በቤትዎ ውስጥ ምን ይወዳሉ? በቤት ውስጥ የሚኖረውስ ማነው? ታሪኩን ተከትለው ከልጆች ጋር ስለ ቤትዎ ማውራት ይችላሉ፤ ምንና ማን በውስጡ እንዳለ፦ የቤተሰብ አባላት፣ የቤት እንስሳት፣ ተወዳጅ አሻንጉሊቶችና ሌላስ ማን? (በአንቀጹ መጀመርያ ላይ የታየ ነው)

ሌላ ተጨማሪ ሳይሆን ሳጥን
“ይሄ ቤት ማለት በጠቅላላው የሚኖሩበት ሳጥን ነው…” ኮዱን ስካን ያድርጉና በዳቲያ ቤን ዶር የተጻፈውንና የተቀናበረውን ዘፈን ይቀላቀሉ።
ጨዋታ - ድብብቆሽ
የት መደበቅ ይገባል? – እንደ ያስሚንና እናቷ ታዳጊው ሕጻን ሲደበቅና ወላጁ ሲፈልገው እርስዎም ድብብቆሽ መጫወት ይችላሉ። ተሳካ? – ተጨማሪ ዙር መጀመርና ቤተሰብ አባላትን ማሳተፍ ይችላሉ።
እኛም እየገነባን ነው
እርስዎም ከሣጥን ቤት መሥራት ይችላሉ። የሚያስፈልገው ትልቅ የካርቶን ሳጥን፣ ነፃ ጊዜና ጥሩ ስሜት ብቻ ነው። አሁን እርስዎ በገነቡት ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ጓደኞችን መጋበዝ ይችላሉ። ትንሽ ሳጥን ብቻ ነው ያገኙት? – ወደ አሻንጉሊቶች ቤት መቀየር ይችላሉ።
መነጋገር - ማን ሊያግዝ ይችላል?
ሁሉም ሰው ሌሎችን ታዳጊ ሕጻናትን እንኳን ሳይቀር ሊያግዝ ይችላል። ታዳጊ ሕጻናቱን ሌሎችን በምን እንደሚያግዙ መጠየቅ ወይም በሚከሰትበት ጊዜ እንደሚረዷቸው መንገር ይችላሉ፦ “ጠረጴዛውን ለማዘጋጀት እንደረዳኸኝ አስታውስ?”፣ “መጫዎቻዎቹን ለማዘጋጀት እንዴት እንደረዳሽኝ ተመልከቺ!”
ታሪኩን ማዳመጥ
“ኖኒና እናቱ” የሚለውን ታሪክ ማዳመጥ ይፈልጋሉ? – የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና የታሪኩ የድምጽ ቅጂ ላይ ይደርሳሉ። በሚያሽከረክሩበት ጊዜ፣ በሚጫወቱበት ወይም አብረው ተቀምጠው መጽሐፍ በሚያገላብጡበት ጊዜ ማዳመጥ ይችላሉ።
ታሪኩ በምስል
ስዕሎቹ የታሪኩ አካል ሲሆኑ በእነርሱ አማካኝነት ታዳጊ ሕጻናቱ የታሪኩን ሂደትና ዝርዝሮቹን ያውቃሉ፤ ያስታውሳሉም። ስዕላዊ መግለጫዎቹን አንድ ላይ በማየት ኖኒ ለእናቱ የሰጣትን ዕቃዎች መፈለግ ይቻላል። ‘ቦርሳ የተሳለበት ቦታ የት ነው?’ እና ‘የኮት ምስል የት አለ?’
ጨዋታ - የእቃዎች ግንብ
በእናት ላይ በተቆለሉ ነገሮች በመጠቀም በተራ የእቃዎችን ግንብ መገንባት ይችላሉ፦ በጥንቃቄ አንዱን በሌላው ላይ በማድረግ ኩቦችን፣ መጫወቻዎችን፣ ኮፍያዎችን፣ ቦርሳዎችንና ማከል የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ማስቀመጥ ይችላሉ።
ችግኝ የምንተክለው በዚህ መንገድ ነው
በተጨማሪም በቤት ውስጥ ወይም በአትክልቱ ውስጥ መትከል ይችላሉ፦ በመሬት ውስጥ ጉድጓድ ይቆፍሩ፣ ቡቃያውን በውስጡ ያስቀምጡ፣ በዙሪያው ያለውን አፈር ያጥብቁ እና ውሃ ያጠጡ። እንዴት እንደሚተከል አያውቁምን? በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ…
እንቅስቃሴ - ችግኝ እንዴት ያድጋል?
ቡቃያው እንዴት እንደሚያድግ በሰውነት እንቅስቃሴ ማሳየቱ ጥሩ ሀሳብ ነው፦ ዝቅ ብሎ ማጎንበስ፣ በዝግታ ቀና ማለት፣ በጣትዎ ጫፍ መቆም እና በመጨረሻም እጆችዎን ወደ ላይ እና ወደ ጎን ማንሳት።
ጨዋታ፦ በፍጥነት - በቀስታ
“ችግኝ የሚተክሉት እንዴት ነው? አይቸኩሉምም፣ አይዘገዩምም” በፍጥነት ወይም በቀስታዘና ማለት ይችላሉ፦ “አሁን በፍጥነት… እንሄዳለን። እና አሁን… ቀስ በቀስ!” “እጆቻችንን እናዙር… በቀስታ፣ እና እጆቻችንን እናዙር… በፍጥነት!” በፍጥነት እና በቀስታ ሌላ ምን ማድረግ ይችላሉ?
መዝሙር - "ችግኝ የምንተክለው በዚህ መንገድ ነው"
“ችግኝ የምንተክለው በዚህ መንገድ ነው” የሚለው በማቲ ካስፒ የተቀናበረ ዜማ ያለው መዝሙር ነው። በእንቅስቃሴዎች፣ በዳንስ እና በእጅ በማጨብጨብ አንድ ላይ ሊዘምሩት ይችላሉ።
መዝሙሩ ከኮዱን ስካን በማድረግ ይሰቀላል፦
ውይይት - የሴት አያት ታሪኮች
ወንድና ሴት አያቶች በልጅነታቸው፣ ጥቅም ላይ ስለዋሉና ከአሁን በኋላ ጥቅም ላይ ስለማይውሉ እቃዎች ታሪኮች ወይም ምናልባትም ሌላ ታሪክ? – ታሪኩን ተከትሎ ከወንድና ሴት አያቶች ጋር መነጋገርና ስላለፉት ቀናት ታሪኮችን ከእነርሱ መስማት ይችላሉ።
ጨዋታ - ምርጡ
አያት በጣም ደመቅ ያለ ሳቅና በጣም አስደሳች ታሪኮች አሉትና እርስዎስ በምን “ምርጥ” ነዎት? – እያንዳንዱ በተራው እርሱ በምን “ምርጥ” እንደሆነ ይናገራል። በሚቀጥለው ዙር ሁሉም ሰው ከጎኑ ያለውን ተሳታፊ በምን “ምርጥ” እንደሆነ ይነግራል – ግን በመልካም ነገሮች ብቻ!
ክብ ሰርቶ መደነስ
ለምንድነው ሁሉም ሰው የሚጨፍረው – የእስራኤል ሃገር በመቋቋሟ ሲሆን ይህም ለዳንስ ለመውጣት ትልቁ ምክንያት ነው። ዛሬ እስራኤል ስንት ዓመቷ እንደሆነ ያውቃሉ? ሃገሪቱ ከተቋቋመችስ ስንት ዓመታት አለፉ? እርስዎም ክብ ሰርተው አብረው ሙዚቃው ላይ መደነስና ዳንሱን ለአንድ ሰው ወይም ለሆነ ለተከሰተ ነገር ማበርከት ይችላሉ።
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ወንድና ሴት ልጆች ስዕላዊ መግለጫዎችን “ያነባሉ”፤ በታሪኩ ውስጥ ላልተጻፉ ዝርዝሮችም ትኩረት ይሰጣሉ። በማንበብ ጊዜ እነርሱን መቀላቀል፣ በጋራ ማስተዋልና ስዕላዊ መግለጫዎቹ እንዴት በጽሁፍ ታሪክ ላይ አስደሳችና አስገራሚ ዝርዝሮችን እንደሚጨምሩና ሌላው ቀርቶ በመስመርና በቀለም ሌላ ታሪክ እንዴት እንደሚናገሩ ማዎቅ ይገባል።
ውይይት - ስዕሎችን መጎብኘት
የት ጎብኝተዋል ሌላስ የት መሄድ ይፈልጋሉ? – የቤተሰብ ፎቶዎችን አንድ ላይ በማስተዋል የጎበኟቸውን ተወዳጅ ጉዞዎችንና ቦታዎችን ማስታወስ ይችላሉ። እስካሁን ያልጎበኙት ቦታ አግኝተዋል ወደፊትስ ወደዚያ መሄድ ይፈልጋሉ?
ለኪኔሬት መዘመር
“ኪኔሬት ሆይ ዘምሪልኝ” – እርስዎም ለኪኔሬት መዝፈን ይፈልጋሉ? – ኮዱን ስካን በማድረግ ዘፈኑን መቀላቀል ይችላሉ!
በስዕላዊ መግለጫዎቹ ውስጥ ማን አለ
ጃሙስ? የተለመደ ቀበሮ? የባህር ኤሊ? – ስዕላዊ መግለጫዎችን ካስተዋሉ በእስራኤል ምድር በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ እንስሳትን ማወቅ ይችላሉ። እናንተ፣ ወላጆች፣ የእንስሳትን ስም መጥቀስ፣ ወንድና ሴት ልጆችም በመጽሐፉ ገፆች መካከል እንዲያገኙት መርዳት ትችላላችሁ። ልጆቹ በተለያዩ ምንጮች ተጨማሪ መረጃ እንዲፈልጉና ስለ እንስሳት እንዲማሩ ሀሳብ መስጠት ይቻላል።
ጨዋታ - ኪኔሬት-የብስ
ወለሉ ላይ ገመድ ያስቀምጡና አንደኛውን ጎን “ኪኔሬት” እና ሌላኛውን “የብስ” ያድርጉ። ከተሳታፊዎቹ አንዱ “ኪኔሬት” ወይም “የብስ” ሲል ሌሎች ተሳታፊዎች ወደ ተገቢው ጎን ይዘላሉ። የእንስሳትን ስም ማከል ይችላሉ፤ ለምሳሌ “ኪኔሬት-ዶሮ” ከዚያም ከኪኔሬት አጠገብ ይዘሉና እንደ ዶሮ ይጮኻሉ።
አብሮ ማንበብ
ታሪኩን በማንበብ በንቃት እንዲቀላቀሉ ታዳጊዎቹን ማበረታታት ይችላሉ። እነርሱ የግጥም ቃላትን ማጠናቀቅ፣ በፊት ገጽታ እና በትክክለኛ የእጅ ምልክቶች በእንስሳት መካከል የሚደረገውን ውይይት ማጀብ እና በታሪኩ ውስጥ የሚታዩ የእንስሳትን ድምጽ መፍጠር ይችላሉ።
ሰንበትን ወደ መቀበል
ታዳጊዎችን መጠየቅ ይችላሉ፦ በሰንበት ምን ማድረግ ይወዳሉ? ቤተሰቡ ለሰንበት ልዩ ዝግጅቶች ካላቸው፣ እነርሱን ለልጁ መንገር እና ማጋራት ጠቃሚ ነው
እንስሳቶቹ የት አሉ?
መጽሐፉ ንብ፣ ኤሊ፣ ጉንዳን፣ ዶሮ፣ ላም እና ጥንቸል በተለይ ይገልፃል። በመፅሃፉ ውስጥ ባሉት ስዕላዊ ማብራሪያዎች ውስጥ ታዳጊዎች የተለያዩ እንስሳትን እንዲለዩ ጠይቋቸው እናም እያንዳንዱን እንስሳ በልዩ ድምፅ አጅበው ወይም ሌላ የባህሪይ ዝርዝሮችን ይጨምሩበት፦ ንቧ ኸምምም ትላለች፣ ጥንቸሉ ይፈናጠራል፣ ኤሊ በዝግታ ትሳባለች፣ እና ላሟ ትጮኻለች።
እናም አሁን - ኤሊ!
በእጅዎ መዳፍ ኤሊ እንዴት ይሰራል? መዳፉን በቡጢ ይዝጉና በውስጡ አውራ ጣትን ይደብቁ። ኤሊውን ወደ ውጪ ይጥሩ፣ አውራ ጣትን አውጥተው ሰላም በማለትያንቀሳቅሱት። እቤት ውስጥ ከሚገኙ በሁሉም መዳፎች ብዙ ዔሊዎችን መፍጠር ትችላላችሁ እራስዎ ኤሊ መሆን እና በአራት እግሮች ላይ በዝግታ መሄድ ይችላሉ። ደክሞታል ወይ? በ”ቤትዎ” ውስጥ ለማረፍ ወደ ውስጥ ይግቡ።
Pinterest – የእደ-ጥበቦች፣ መዝሙሮች እና ሌሎች ተግባራት “ሰንበት በጫካ ውስጥ በሚለው መጽሐፍ ገጽ ላይ በሲፍሪያት ፒጃማ ውስጥ በ Pinterest ላይ።
እኛም መርዳት እንችላለን!
ታዳጊዎች በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይችላሉ? ብዙ ነገሮችን! በመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ ብርጭቆዎችን ማስቀመጥ፣ በትንሽ መጥረጊያ መጥረግ፣ የቤት እንስሳቱን መመገብ እናም ኩኪዎችን ማቅረብ ይችላሉ። ታዳጊው በቤት ውስጥ እንዴት መርዳት እንደሚችል እና በምን መሳተፍ እንደሚችሉ ወይም ምን እንደሚፈልጉ ማውራት እና ማቅረብ ጥሩ ሀሳብ ነው።
በቤተሰቡ ውስጥ ያለው ማነው?
በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ ኩኪዎችን ለሌሎች የቤተሰብ አባላት፦ ለአያት፣ አጎት፣ እህት፣ የአጎት ልጅ ይሰጣል። እና የእርስዎ ቤተሰብ አባላት እነማን ናቸው? ስለቤተሰብ አባላት መንገር፣ ስሞቻቸውን እና የያዙትን ሚናዎች መናገር ይችላሉ፣ ለምሳሌ፦ “ሴት አያቴ ብራሃ”፣ “አጎት ባሮክ” እና የቤተሰብ ፎቶዎችን መጠቀም ይችላሉ። እና ያሰራጩ–ኩኪዎች ነበሩዎት…
ባንድነት አንዳንድ ቀላል ያለ ምግብና መጠጥ እናዘጋጅ!
እንደ ቸኮሌት ኳሶች፣ የፍራፍሬ ሳህን ወይም የተቆረጠ ኪያር የመሳሰሉ ምግቦችን አብረው ማዘጋጀት ይችላሉ። የጨዋታ ሊጥ በመጠቀም “የማስመሰል” ምግቦችን ማዘጋጀት እና በቤት ውስጥ ላሉ አሻንጉሊቶች ማቅረብ ይችላሉ።
ጨዋታ፦ አያቴ ኩኪዎች ነበሯት…
“ሴት አያቴ ገንፎ ሰሩ (Grandma made porridge)” የሚለውን ጨዋታ ያውቃሉ? “ልጁ ኩኪዎች ነበረው (The child had cookies)” በተመሳሳይ መንገድ መጫወት ይቻላል፣ ህፃኑ እጇን ወይም እጁን ከፍቶ ወላጁ መቁጠር ይጀምራል፦ “ትንሹ ወንድ ልጅ/ልጃገረዷ ኩኪዎች ነበራት እና አንዱን ለሴት አያቴ (አውራ ጣት በመያዝ)፣ እና አንዱን ለአጎቴ (ጠቋሚ ጣትን በመያዝ) ወዘተ ሰጠ/ች። እና ስለዚህ አንድን የቤተሰብ አባል ለእያንዳንዱ ሰው በመመደብ ጣቶቹን ይቆጥራሉ። የመጨረሻውን ኩኪ ለማን ይሰጣሉ?
ለሁሉም ጊዜያት የሚሆኑ መዝሙሮች
ይህ መጽሐፍ ዓመቱን ሙሉ እንደ ቤተሰብ አብሮዎት የሚሆን ስጦታ ነው፦ በድግስ በዓላት እና በተለዋዋጭ ወቅቶች፣ በበልግ መምጣት እና ለልደት በዓል ዝግጅት። ለእያንዳንዱ ለሚመጣው ዝግጅት ወይም በዓል ተገቢውን መዝሙር ይምረጡ፣ አብራችሁ አንብቡት፣ ስዕላዊ ማብራሪያዎቹን ይመልከቱ፣ ዘምሩ እና አክብሩ። ግጥሞች እና ስዕላዊ ማብራሪያዎች መዝሙሮቹን አንድ ላይ ያንብቡ እና ስዕላዊ ማብራሪያዎቹን ይመልከቱ። የልጆቹን ትኩረት የሚስቡት ስዕላዊ ማብራሪያዎች የትኞቹ ናቸው?
ስዕላዊ ማብራሪያዎች እና ምሳሌዎች
መዝሙሮቹን አብራችሁ አንብቡ እና ስዕላዊ ማብራሪያዎችን አጥኑ። የትኞቹ ስዕላዊ ማብራሪያዎች የልጆችን ትኩረት ይስባሉ?
በስዕላዊ ማብራሪያው ላይ የሚያዩትን እና በውስጡ ምን ዝርዝር ጉዳዮች እንደቀረቡ አንድ ላይ መመልከት ይችላሉ።
ቃላት እና ዜማዎች
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ መዝሙሮች ለሙዚቃው የተቀናበሩ ነበሩ። ጸናጽል፣ የእንጨት ማንኪያ ወይም ድስት እና መጥበሻ ክዳን ወስደው ሙዚቃና ዳንስ በማጫወት መዝሙሩን ማጀብ ይችላሉ። አንዴ ልጆቹ መዝሙሩን በደንብ ካወቁ በኋላ፣ የግምታዊ ጨዋታ መጫወት ይችላሉ፦ ዜማውን ማጉላት ይጀምሩ እና ልጆቹ የቀረውን እንዲገምቱ እና እንዲቀላቀሉዎት ይጋብዙ።
በስዕላዊ ማብራሪያው ውስጥ ምን ተደብቋል?
መጽሐፉን በዘፈቀደ ወይም በሚወዱት መዝሙር ላይ ይክፈቱና እያንዳንዱ ሰው በተራው በስዕላዊ ማብራሪያው ላይ ሁሉም ሰው መፈለግ ያለበትን ነገር ይጥቀስ። በስዕላዊ ማብራሪያው ውስጥ የሚከተሉትን አግኝ፦ ቀይ ጣሪያ ያለው ቤት የት አለ? ሮማኑ የት አለ? አስቂኝ ተዋናዮቹ የት አሉ?
ውይይት
ለአይሁድ ፋሲካ እንዴት ይዘጋጃሉ? ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የቤተሰብ ባህል አለዋት? ምናልባት ከልጅዎ ጋር ሊወያዩበት ይፈልጉ ይሆናል። እርስዎ፣ ወላጆች፣ እርስዎ በማደግ ላይ እያሉ፣ የቤተሰብ ባህልን ወይም ታሪክን በእነዚህ ሁሉ አመታት ከእርስዎ ጋር የቆየውን የአይሁድ ፋሲካ በዓልን እንዴት እንዳከበሩ ሊነግሩዋቸው ይችላሉ።
ስለ ምግብ
በተለይ ከአይሁድ ፋሲካ ጋር የተያያዘ ምግብ በቤት ውስጥ አለዎት? ባንድነት እሱን ስለማየት እና ታሪኩን ስለመናገርስ፦ ከየት ነው የመጣው? ለምን በቤተሰብዎ ተያዘ? በአይሁድ ፋሲካ ወቅት ምን ጥቅም ላይ ይውላል?
ምሳሌዎች ታሪኮችን ይናገራሉ
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ምሳሌዎች ምን እንማራለን? የወርቂቶን እና የአልማዝን ህይወት የኢትዮጵያ ውስጥ በዓይነ ሕሊናችን እንድንገምት ይረዱናል? እሱን ባንድነት በመመልከት እና ከየትኛው ገጸ ባህሪ ጋር ለመወያየት ፍላጎት እንዳለዎት፣ ይህን ገፀ ባህሪ ምን እንደሚጠይቁ እና እሱን/ሷን መቀላቀል የሚፈልጉ እንደሆነ በመወያየት፣ አንድ የተወሰነ መብራሪያ መምረጥ ያስደስትዎት ይሆናል።
ውስጥ ከአዲሱ ጋር
የወርቅቶ ታሪክን ተከትሎ፣ አሁን የተበላሹ ወይም የተቀደዱ የሚወዷቸውን ነገሮች መንካት ይፈልጉ ይሆናል። አሮጌ ቲሸርት መሳል፣ አሮጌ ኮፍያ ቀለም መቀባት፣ አሮጌ ተክልን በሞዛይክ መሸፈን፣ አንዳንድ የወጥ ቤት እቃዎችን ማስጌጥ ወይም ከተሰበረ ሳህን ሙሉ በሙሉ አዲስ ነገር መፍጠር ይችላሉ። የተለወጠበትን መንገድ ይወዳሉ?
האזינו לסיפור "סתם שדה ריק"
אנו מזמינים אתכם/ן להאזין להקלטה הקסומה של הסיפור “סתם שדה ריק”, מאת: תמר וייס-גבאי | איורים: בלה פוטשבוצקי | הוצאת: כנרת (גנים)
יוצרים ומגישים – ירדן בר כוכבא – הלפרין ודידי שחר מוזיקה ונגינה – טל בלכרוביץ’ פתיח – דידי שחר
מוכנים/ות? מת – חי – לים!
ውይይት - መተሳሰብ ምንድን ነው?
“አካባቢ ላይ መተሳሰብ አስፈላጊ ነው”- መተሳሰብ ምንድን ነው? በቤተሰብ አባላት መካከል በቤት ውስጥ አንዱ ለአንዱ እንዴት መተሳሰብ ይቻላል? በአካባቢስ እንዴት እንተሳሰብ? በዚህ ጉዳይ ላይ ከሴቶችና ወንዶች ልጆች ጋር መወያየት ትችላላችሁ፤ ሰዎችና አካባቢ ላይም እንዴት መተሳሰብ እንደሚቻል አስተያየት መስጠት ይችላሉ።
የምልከታ ግብዣ
በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ ክፍል ለመጎብኘት ተጋበዛችሁ፦ በቤቱ አጠገብ ያለን የአትክልት ቦታ፣ ሜዳ፣ ጓሮ ወይም በረንዳ ላይ ያለን የአበባ ማስቀመጫ። በጸጥታ ተቀምጣችሁ ብትመለከቱ ምን ታገኙ ይሆን? በአጉሊ መነጽር መታገዝ ይመከራል።
እርስበርስ መማር
አዋቂዎች ከወንዶችና ሴቶች ልጆች ምን ሊማሩ ይችላሉ? ብዙ ነገሮች! የሚወዱትን ጨዋታ በመጫዎት፣ ሥዕል በማዘጋጀት፣ በመዋዕለ- ህፃናት ውስጥ የተማሩትን ርዕሰ ጉዳይ በማዎቅ ወይም አስደሳች አስተሳሰብን በማካፈል። ወንዶች እና ሴቶች ልጆችስ ከአዋቂዎች ምን ሊማሩ ይችላሉ? አንዱ ከሌላው ምን መማር እንደሚችል ለማወቅ አብራችሁ መቀመጥ እና በትኩረት መከታተል ብቻ ያስፈልግዎታል።
ቀለሞችን መያዝ
ሰማዩ ሰማያዊ፣ መሬቱ ቡናማ፣ እፅዋቱ ደግሞ አረንጓዴ ናቸው። ወደ ውጭ መውጣትና “ቀለሞችን መያዝ” አለባችሁ። እያንዳንዱና እያንዳንዷ ሁሉም በተራ አንድ ቀለም ያሳውቁና ሌሎች ተሳታፊዎች በአካባቢው ውስጥ አንድ ያንኑ ቀለም ያለው እቃ በፍጥነት ማግኘትና ወደ እርሱ ማመልከት ይኖርባቸዋል።
ውይይት
አንተ፣ ልክ እንደ ጥድ ዛፍ፣ አንዳንድ ጊዜ ብቸኝነት ይሰማሃል? ትንሽ ብቸኝነት የሚመስሉ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አይተህ ታውቃለህ? ይህንን “ብቻ የመሆን” ስሜት እና እኛ – ወይም በዙሪያችን ያሉ – እንደዚህ ሲሰማን ምን ማድረግ እንደምንችል መወያየት ይፈልጉ ይሆናል ።
ስለ ጥድ ዛፎች አንዳንድ መረጃዎች
የኢየሩሳሌም ጥድ (በእንግሊዘኛ በተለምዶ Aleppo Pine በመባል ይታወቃል) በእስራኤል ውስጥ የሚበቅሉ የጥድ ዛፎች ዝርያ ነው። በቀርሜሎስ እና በይሁዳ ተራሮች አካባቢ በጣም ተስፋፍቷል። የአይሁድ ማኅበረሰብ፣ ይሹቭ፣ እያደገ ሲሄድ፣ በእስራኤል ምድር ትላልቅ የጥድ ዛፎችን መትከል ጀመረ። የጥድ ዛፉ ሙጫ ይዟል፣ እና በጸደይ ወቅት፣ ቅርንጫፎቹ በጥድ ፍሬዎች ኮኖች የተሞሉ ናቸው። ስለ ጥድ ዛፍ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ምስሎችን እና ተጨማሪ መረጃዎችን በመስመር ላይ ለመፈለግ ነፃነት ይሰማዎት።
የሚቀጥለው ምዕራፍ
ዛፎቹ ካደጉ እና ጫካ ከተፈጠረ በኋላ ምን ይሆናል? ከጥድ ዛፍ ጋር ጓደኛ ይሆናሉ? ሌሎች ጓደኞች መጥተው ይጎበኛሉ? እና ልጆቹ በአዲሱ ጫካ ውስጥ ምን ያደርጋሉ? – ስለ መጽሐፉ ቀጣይ ክፍል መወያየት፣ መተግበር ወይም አንድ ላይ መሳል ያስደስትዎ ይሆናል።
ጨዋታ - እኔ ማን ነኝ?
እኔ የሚነፍሰው ነፋስ ነኝ ወይ? ወይስ የሚወርደው ዝናብ? ምናልባት የሚዘል ጥንቸል? ተራ በተራ በመጽሃፉ ውስጥ ካሉት ገፀ ባህሪያቶች አንዱን በማስመሰል እና ሌሎች እርስዎ የትኛውን እንደመረጡ እንዲገምቱ በማድረግ የ charades አይነት መጫወት ይችላሉ።
አንድን ዛፍ እንዴት እንደሚይሳድጉ
በአካባቢዎ ውስጥ አንድ ዛፍ መምረጥ እና እሱን መንከባከብስ? በዙሪያው ማጽዳት፣ ከእሱ ስር ምንጣፎችን ማስቀመጥ እና እንደ መኖሪያቸው የሚጠቀሙባቸውን ትናንሽ እንስሳት መመልከት ይችላሉ። በጥንቃቄ ከተመለከቱ፣ በፈገግታ እንኳን ሊይዙት ይችላሉ።

የቤተሰባዊ ንባብ ምክር
” ሣጥን፦
አድሪያኖስ ማን ነበር?
አድሪያኖስ ከ117-138 ዓ.ም የገዛ የሮማ ንጉሠ ነገሥት ነበር። በእርሱ መሪነትም የሮማ ግዛት ተስፋፍቶ ነበር። አድሪያኖስ ለባር-ኮኻቫ አመጽ መገደል ተጠያቂ ሲሆን በይሁዲዎች ላይ ከባድ ፍርድ አስተላልፏል። በሚድራሾችም ውስጥ ጥበበኛና ሰፊ አስተሳሰብ ያለው ንጉሠ ነገሥት እንደሆነ ይገለጻል። ነገር ግን ጨካኝና ለይሁዳ ጥፋት ዋነኛ መንስኤ ነበር።”
ስጦታዎችን የተሞላ ቅርጫት
ልዩ ስጦታዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋሉ፦ የቤተሰብ ታሪክ፣ የምግብ አሰራር ወይም ልዩ የበዓል ልማዶች። ማጋራት የምትችሏቸው፦ ከወላጆች፣ ከአያቶች ወይም ከሌላ የቤተሰብ አባል ምን ጠቃሚ የሕይወት ስጦታ ተቀብላችኋል?

ካለፈው ለወደፊቱ
በቤት ውስጥና በዙሪያው አብረው ይፈልጉ፦ ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱ በዙሪያዎ ያሉ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለወደፊት ትውልዶች ተብለው አሁን እየተደረጉ ያሉ ነገሮችንስ ደግሞ ማግኘት ትችላላችሁ? ምናልባትም እየተገነባ ያለ አዲስ ሕንፃ፣ የመጫወቻ ሜዳ፣ ትምህርት ቤት ወይም የዛፍ ቁጥቋጦ?

የጨዋታዎች አልበም
በታሪኩ ውስጥ ያለው አዛውንት ከእርሱ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶች በለስን ለእኛ ደግሞ ታሪኩን አስቀርቷል። የቤተሰብ ፎቶዎችና ታሪኮች ላይ አንድ አልበም መስራት ይችላሉ። ከጉዞዎች ወይም ክስተቶችና በእናንተ ላይ የተከሰቱ ታሪኮችን ወደ አልበሙ ፎቶዎች መጨመር ትችላላችሁ።

עוד על הסיפור באתר ספר האגדה
https://agadastories.org.il/node/531
אדריאנוס קיסר במוזיאון ישראל
http://www.ynet.co.il/articles/0,7340,L-4741710,00.html

"ሌላስ ምን?" ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
በእያንዳንዱ ገጽ መጨረሻ ላይ ክፍት ጥያቄ ወይም ዓረፍተ ነገር የሚተዉ መጽሐፍት አሉ። ስለሆነም ወጣት አንባቢዎች እንዲሳቡ፣ እንዲሳተፉና በሚቀጥለው ገጽ ምን እንደሚጠብቃቸው እንዲገምቱ እድል ይሰጣቸዋል። በማንበብ ጊዜ በገጾቹ መካከል ለአፍታ ቆም ይበሉ፣ ይገምቱ ወይም በሚቀጥለው ገጽ ላይ ምን እንደሚጠብቃቸው አንድ ላይ ያግኙ።

ውይይት እንደ ሁሌው እለተ ዓርብ
ታሪኩን ተከትለን አብረን ማሰብ እንችላለን – በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ምን ያደርጋሉ? እንዲሁም መደበኛ አዘገጃጀቶች፣ ዝግጅቶች ወይም የቤተሰብ ሥርዓቶች አሉዎት? በተለይ ምን ማድረግ ይወዳሉ? ለሠንበት መቃረቢያ ሽር ጉድ ስላሉ ወይም ስለተደሰቱ ሠንበት የበለጠ አስደሳችና ደስ የሚል እንደሆነ ተሰምቶዎት ያውቃል?

ከምስሎች ጋር መጫዎት
የአቭነር ካጽ ክላሲክ ሥዕላዊ መግለጫዎች የዮዮ ብዙ ሥራዎችን ያሳያሉ። አንዳንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ሐብሐብ ይሸከማል። አንዳንድ ጊዜ በብስክሌት ይጋልባል። አንዳንዴም መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ይታጠባል። የአካላዊ እንቅስቃሴ ጨዋታ መጫወት ይችላሉ – እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በተራው የመጽሐፉን በዘፈቀደ ይከፍትና በምስሉ ላይ የተገለጸውን በእንቅስቃሴ ያሳያል – ሌሎች የቤተሰብ አባላት ስለ እርሱ አሁን ምን እንዳለ መገመት አለባቸው።

የሠንበት አዘገጃጀት
የቲማቲም ጭማቂ? የብርቱካን ማርማላታ? ምናልባት የተጠበሰ ፓንኬክ? በታሪኩ ውስጥ ከሚታዩ የተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ውስጥ የመጽሐፉን ገፆች ማገላበጥ፣ መምረጥና ማዘጋጀት ይችላሉ። ከዝግጅቱ በኋላ ማረጋገጥ የሚችሉት – ፓን ኬኩን ለመሥራት ስንት ድንች ተጠቅመዋል? ማርማላታውንስ ለማዘጋጀት ስንት ብርቱካን?

የማስታዎስ ጨዋታ
ታሪኩን ስንት ጊዜ አንብበዋል? የሚያስታውሱትን ለመፈተሽ ጊዜው አሁን ነው! ወንድና ሴት ልጆች አንድን መጽሐፍ ደጋግመው ማንበብ ያስደስታቸዋል። በሚያስታውሱበት ጊዜም በራሳቸው እንዴት እንደሚናገሩ ሲያውቁ በደህንነትና በእርካታ ስሜት ይሞላሉ። ልጆቹን ማስታወስን እንዲያሟሉ የሚያቀርቡላቸው – ስንት ቲማቲሞች? ስንት ብሩሽ? የማስታወስ ችሎታዎን እንዲፈትሹና ስለ ታሪኩ ዝርዝሮች እንዲጠይቁ ይጠቁሟቸው።