השבת אבידה
מבוגרים וילדים כאחד, מכירים את תחושות התסכול והעצב העולות כשמשהו "הולך לאיבוד". סיפורים על השבת אבדה מעוררים בנו הזדהות עם מצבים ורגשות המוכרים לנו מחיינו ומהווים פתח למחשבה ולשיח על מצוות חסד המעניקה ערך משמעותי ביחסים שבין אדם לחברו ומשמחת את ליבם של כל הנוגעים בדבר.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ቪዲዮ - ጠፍተው የተገኙ እቃዎች ያሉበት ሳጥን
ሻቢና ኦዛም ከ”ደስ የሚል ቢራቢሮ” መርሃ ግብር ላይ የጠፉ እቃዎችን እየመለሱ ነው። ኮዱን ስካን ያድርጉና ይመልከቱ።
ፍለጋንና ማግኘትን አስመልክቶ የሚደረግ ውይይት
መጽሐፉን ተከትሎ ከወላጆች፣ ከወንድ አያት፣ ከሴት አያት ወይም ከሌሎች ዘመዶች ጋር በመሆን የፍለጋ ጉዞ ማድረግ ትችላላችሁ፦ ምን አገኛችሁ? ተገረማችሁ? መፈለግና ማግኘት ትወዳላችሁ?
ጨዋታ - የኳ-ኳ ፍለጋዎች
ለሚፈልጉና ለሚያገኙ የሚሆን የጋራ ጨዋታ!
የQR ኮዱን ስካን ያድርጉ
በመመሪያዎቹ መሰረት ፕሪንት ያድርጉ፣ ይቁረጡና ይጠፉ።
ፈለጉ? አገኙ? እንደገና መጫወት ይፈልጋሉ?
ስዕላዊ መግለጫዎች
በመጽሐፉ ውስጥ በቀለማት ያሸበረቁና ጥቁርና ነጭ የሆኑ ስዕላዊ መግለጫዎች ይገኛሉ –
ስዕሎቹ በጥቁርና ነጭ ሲሆኑ እና ስዕሎቹ በቀለም ያሸበረቁ ሲሆኑ መከታተልና መለየት ይችላሉ?
ጨዋታ - የጠፋው ምንድን ነው?
ብዙ እቃዎችን በተከታታይ ያስቀምጡና በጥንቃቄ ይመልከቱ።
በእያንዳንዱ ጊዜ የቤተሰቡ አባላት ዓይኖቻቸውን ይዘጉና ከቤተሰብ አባላት አንዱ አንዱን እቃ ይደብቃል።
ከዚያ በኋላ ዓይኖቻቸውን ከፍተው ይፈልጋሉ – የትኛው እቃ ጠፋ? የት ነው የደበቁት?
በጣም ደስ ይላል - ኢላኒት!
እኔ እንቁራሪት እመስላለሁ ነገር ግን በጣም ትንሽ ነኝ፤
የምኖረው በእስራኤል ነው፣ በዋናነት በዛፎች ላይ፣ የምበላው ነፍሳትን ሲሆን በውሃ ውስጥ እንቁላል እጥላለሁ።
ዛሬ እኔ ጥበቃ የሚደረግልኝ እንስሳ ነኝ ስለዚህም እኔ በተፈጥሮ ብቻ እንጂ በማሰሮ ውስጥ አላድግም።
פינטרסט
פינטרסט
משחקים, שירים והשראה ליצירה מחכים לכם בתיקיית הספר בפינטרסט של ספריית פיג’מה.