גדילה
בתהליך הגדילה אשר מתפרס על פני שנות התפתחות והתבגרות רבות, ילדים וילדות מרגישים לפעמים גדולים ולפעמים קטנים. הם מתנסים, לומדים, לפעמים נופלים וגם קמים. ספרים אשר במרכזם מתוארים גיבורים שעוברים תהליך גדילה והתנסות, מעוררים הזדהות והשראה לשיח משמעותי על רגשות, ולחיזוק הדימוי העצמי.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ምክር
ሴትና ወንድ ልጆች እንደ አዋቂ ሰው ትልቅነት ሲሰማቸው ይደሰታሉ። መጽሐፍን በሚያነቡበት ጊዜ ከልጆች ጋር መጋራትና የብቃት ስሜታቸውን ማጠናከር ይገባል፦ ከመደርደሪያው ውስጥ መጽሐፍ መርጠው መጽሐፉን እንዲይዙ፣ ገጹን ራሳቸው እንዲቀይሩና ሌላው ቀርቶ ታሪኩን ለእርስዎ ወይም ለአሻንጉሊት በራሳቸው ቃላት መንገር እንዲችሉ ማድረግ ይችላሉ።

እኔ አልችልም
አቪቪ ለኤማ በጣም ትንሽ ስለሆነች ክፍሉን ማፅዳት እንደማትችል ትነግራታለች። ታሪኩን በመከተል በጋራ መነጋገርና ማሰብ ትችላላችሁ – ክፍል ማዘጋጀት ቀላል ወይም ከባድ ነው ብለው ያስባሉ? በዝግጅቱ ላይ ምን ሊረዳ ይችላል? “በጣም ትንሽ” ስለነበሩ ከዚህ በፊት ማድረግ ያልቻሉትን ዛሬ ላይ ምን ምን ማድረግ ይችላሉ?

በፍጥነት እናዘጋጅ!
እየተዝናናችሁ ክፍሉን በማስተካከል አብረው “የቤተሰብ ከፍታ” ላይ ለመድረስ ይሞክሩ፦ አሻንጉሊቶችንና የተለያዩ እቃዎችን በቤቱ ማእከላዊ ክፍል ውስጥ ይበትኑና ጊዜን ለመለካት ሰዓት ያዘጋጁ ወይም የጊዜ ዒላማ አስቀድመው ያዘጋጁ። ከ”ማስጀመሪያው” ጊዜ ጀምሮ በተቻለ ፍጥነት በመተባበር እቃዎችን በቦታው በሚችሉት ማዘጋጀት አለብዎት! ምን ያህል ጊዜ ወሰደ? ግቡን አሳክተዋል?

የአሻንጉሊቶች ቲያትር
አቪቪ አሻንጉሊቶቿንና መጫዎቻዎቿን ክፍሉን እንዲያስተካክሉ ጠይቃለች። ግን አንችልም ብለው መለሱ – ዶቢ በጣም ደክሟል፣ እንቁራሪት በጣም ተስኗታል … የእናንተዎቹ አሻንጉሊቶችስ? አሻንጉሊቶችዎ ምን ምን ማድረግ አይችሉም? እናስ ለምን? ምን ልትጠይቋቸው ትፈልጋላችሁ? በአሻንጉሊትና መጫዎቻ ትዕይንት በመስራት የተለያዩ ሁኔታዎችን ወይም ስራዎችን ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር ማያያዝ ይችላሉ።
QR ኮድ
ኮዱን ስካን ያድርጉና በፒጃማ ቤተ መጻህፍት ትራክት ውስጥ “ክፍሉን ማዘጋጀት” የሚለውን ታሪክ ያድምጡ – በማዳመጥ ጊዜ መጽሐፉን እንዲይዙ ይመከራል።

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምከር
በሥዕል የተደገፈ መጽሐፍ የሚሆን የተቀናበረ ግጥም አንባቢዎች በተለየ መንገድ እንዲለማመዱት፣ እንዲረዱት ወይም እንዲያውቁት ዕድል ይሰጣል። ስለዚህ ይህንን ዓይነት መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ስታነቡ “መጽሐፉን ለመዘመር” መሞከር የለብዎትም ነገር ግን ለሁሉም ነገር እንደ ታሪክ ሆኖ ያንብቡት።
ዓይን ሂሌል (1926-1990) ድንቅ የህፃናት መጽሃፍ ደራሲና ገጣሚ ተወልዶ ያደገው በኪቡዝ ሚሽማር ሀዔሜክ ነው። በሙያው የመዋእለ ህጻናት አርክቴክት ነበር። ነገር ግን ለትንንሽና ትልልቆች መዝሙሮችን መጻፍ ከሁሉም በላይ ይወድ ነበር። በእሥራኤል ውስጥ ካሉት አንጋፋ ሠዐሊዎች አንዱ የሆነው ዳቪድ ፖሎንስኪ ለፊልሞች አኒሜሽን ፈጥሯል፣ በብዙ ኤግዚቢሽኖች ላይ አሳይቷል፣ ሽልማቶችንና ዓለም አቀፍ እውቅና አግኝቷል።

ጊዜው እንዲሁ ያልፋል
ጥያቄዎች ውይይትንና ሀሳብን ያበረታታሉ። በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ምሳሌዎች መመልከትና መጠየቅ ይችላሉ፦ ልጁ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ምን ያደርጋል? የመጽሐፉን መጀመሪያ እንዴት ይመለከታል? መጨረሻውንስ? በምስሎች ተመስጦ ካለፉት ጊዜያት ፎቶዎችዎን አንድ ላይ ማየት ይችላሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንዴት እንዳደጉ ይመልከቱና ጥያቄዎችን ይጠይቁ – የአንድ ዓመት ልጅ ሳለሁ ምን አደረግሁ? አሁንስ ምን አደርጋለሁ? ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምን አገኘሁ እና ተማርኩ?

ምን እናድርግ?
የልብስ ማጠቢያ ማሽን ምን ያደርጋል? ጣሪያውስ ምን ያደርጋል? ታሪኩን ተከትለው በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በመራመድ በዙሪያዎ ስላዩዋቸው ነገሮች መጠየቅ ይችላሉ “ምን እያደረጉ ነው?”

ዓለምን ማግኘት
መጽሐፉ የተለያዩና አዝናኝ መልሶች ያላቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉት። መጽሐፉ በጥልቀት እንዲያጤኑና አብረው እንዲመረምሩ ይጋብዝዎታል። ልጆችዎን መጠየቅ ይችላሉ – ዛፎቹ ሌላ ምን ያደርጋሉ? ደመናዎችስ ሌላ ምን ያደርጋሉ? እንዲሁም የራስዎን የጥያቄና መልስ መጽሐፍ በመያዝ በጋራ መስራት ይችላሉ። ይጻፏቸውና ይሳሉዋቸው እና ሌላ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር ወደ ታሪኩ ጨምረው መልሱን መፈለግ ይችላሉ።

QR ኮድ
በጣም የታወቀውና የተወደደው የዓይን ሂሌል መዝሙር የተቀናበረው በኑኃሚን ሼሜር ሲሆን ቀድሞውኑ የእስራኤል ክላሲክ ሊሆን ችሏል። ለማዳመጥ ኮዱን ስካን ያድርጉ።

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
የማንበብ ነፃነት፦
በማንበብ ጊዜ ታዳጊዎቹ መሳተፍና ያደጉ ብሎም ራሳቸውን የቻሉ እንደሆኑ ሊሰማቸው ይችላል። መጽሐፍ መርጠው በማምጣት ገጾችን በመያዝና በማገላበጥ፣ መጠቆምና የሚያውቁትን ቃል መናገር ይችላሉ። ታዳጊው በንባብ እንዲሳተፍ ማበረታታት የብቃት ስሜትን ያጠናክራል። ከመጻሕፍት ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል።

ውይይት
በራሴ ማድረግ፦
ታዳጊዎቹ በራሳቸው ሊሠሩ ስለሚማሩት ነገሮች ማውራት ይችላሉ። እርስዎ ራስዎ በቤት ውስጥ ምን ያደርጋሉ? በምንስ እርዳታ ይፈልጋሉ? ራስዎን ችለው ለመስራት መማር የሚፈልጓቸው ነገሮች አሉ? ማድረግ የሚፈልጉትን ?አዲስ ነገር እንዴት መለማመድ ይችላሉ

QR ኮድ
ኮዱን ስካን ያድርጉና ገጸ-ባህሪያትን ከመጽሐፉ ውስጥ ፕሪንት በማድረግ ቆርጠው በማውጣት በከረሜላ ዱላዎች ላይ በማጣበቅ ታሪኩን ራስዎ ያቅርቡ ወይም በስምንተኛው ቀን የሆነውን ነገር በገጸ ባህሪያቱ እርዳታ በምናብ ያስቡ።
ምስሎች
ብዙ ዝርዝሮች በምሳሌዎች ውስጥ ይታያሉ። ልክ እንደ ቲም ታም በየቀኑ አዲስ ነጥብ እንደሚያገኝ በእያንዳንዱ ንባብ አዲስ ዝርዝር መፈለግ ይችላሉ። ቲም ታም የት ነው? ጥቁር ነጠብጣቦች የት አሉ? ምን ሌሎች ቅርጾችን ያስተውላሉ? በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ምን እንስሳት ይታያሉ? በቲም ታም ቤት ውስጥ ምን እቃዎች አሉ?

ነጥቦችን በመፈለግ ላይ፦
ቲም ታም በአካባቢዋ ያሉትን ነጥቦቹን ለማስተዋልና እነርሱን ለማግኘት ይማራል። በአካባቢያችሁ ውስጥ ነጥቦችንና ክብ ነገሮችን በጋራ መፈለግ ትችላላችሁ። ነጥቦች የት ተደብቀዋል? ምናልባት በሸሚዝ ላይ? ምናልባት በሰውነት ውስጥ? በቤት ውስጥ ምን ዓይነት ክብ ነገሮች አሉን? ከቲም ታም የጥንዚዛ ጓደኛዎች አንዱን እንኳን ሊለዩ እንደሚችሉና እንደማይችሉ።

የጥንዚዛ ጣት፦
በሁለት ጣቶች አማካኝነት ቀለል ባለ ጭብጥ ጥንዚዛን እጅ ላይ፣ እግር ላይ ወይም ፊት ላይ እንደ ማድረግና ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ፣ ምን እንደሚኮረኩረው፣ ምን ላይ ስሜቱ የሚጠነክርበትና የሚቀንስበት እንደሆነ ይሰማዎታል።

ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ምክር - መንገዳችሁን ማግኘት
ከመኝታ በፊት ተረት ማንበብ አለብህ ያለው ማነው? ምናልባት ከሰዓት በኋላ ማንበብን ይመርጣሉ? ምናልባት ምንጣፉ ላይ አብረው ይተኛሉ ወይስ ለማንበብ የቴዲ ድብን ይቀላቅሉታል? እያንዳንዱ ታዳጊ ህጻን የራሱ ባህርይና ፍላጎት አለው፤ በእርግጥ አዋቂዎችም እንዲሁ የተለያዩ ምርጫዎች አሏቸው። እናንተና ልጆቻችሁ ለማንበብና የራሳችሁን ልዩ የታሪክ ጊዜ ለመፍጠር በጣም ጥሩውን ጊዜና መንገድ መፈለግ አለባችሁ።

ጥዝ የሚለው ጣት
ጣታችሁም እንዲሁ ዝንብ ሊሆን ይችላል፦ ጥዝ የሚል ድምጽ በማሰማት ጣታችሁን እንደ ዝንብ በአየር ላይ አንቀሳቅሱት። ታዳጊው “የሚበረው”ን ጣት መከተል እንደቻለ ልብ በሉ። በእያንዳንዱ ጊዜ ጣታችሁን በተለያየ የሕፃኑ አካል ላይ ማድረግ ትችላላችሁ፦ አፍንጫ፣ ጉንጭ፣ እጅ ወይም ጆሮ ላይ። ጮክ ብላችሁ መናገር ትችላላችሁ፦ “ጥዝዝዝዝዝዝ በግንባር ላይ” የአካል ክፍሎችን ስም መለማመድና አንድ ላይ መሳቅ። ታዳጊው ጨዋታውን ካወቀ በኋላ ልክ እንደ ዝንብ በጣቱ እንዲበር ልትጋብዙት ትችላላችሁ።
ለቤተሰባዊ ንባብ ምክር
መጽሐፍ ማንበብ የልጆችን ዓለም ለማወቅ ጥሩ መንገድ ነው። በንባብ ጊዜ አንዳንድ ጊዜ ማቆምና ልጅቷ ወይም ልጁ በታሪኩ ውስጥ ስላሉት ክስተቶች አስተያየት እንዲሰጡ መፍቀድ አለብዎት። የታሪኩ ጀግና ምን ይሰማዋል? እናንተስ አንባቢዎች ምን ይሰማችኋል? ለእናንተም ተመሳሳይ ነገር አጋጥሟችኋል?

ውይይት - ትልቆችም ትንሾችም
ሰላጣ ለመሥራት ረድተዋል? ወድቀው ተጎድተው ያውቃሉ? – አንድ ላይ ወላጆችና ልጆች እርስዎ እንዳደጉ የተሰማዎትን ጊዜና በእራስዎ ሙሉ በሙሉ ማድረግ የቻሉትን ድርጊቶችና እቅፍና ማፅናኛ የፈለጉባቸውን ጊዜዎች ማስታወስ ይችላሉ። ይህ የልጆችን ልምዶች ለማወቅ እንዲሁም ከልጅነትዎ፣ ከወላጆችዎ ልዩ ጊዜዎችን ለመጋራት እድል ነው።

?ትልቅ ወይስ ትንሽ
ሁለት እቃዎችን በመሰብሰብ ማወዳደር – ማን ትልቅ ማን ትንሽ ነው? – አሁን ከእቃዎቹ ውስጥ አንዱን በሌላ እቃ ይለውጡና እንደገና ያረጋግጡ። ማንኪያው ከቡሽ አጠገብ በሚሆንበት ጊዜ ትልቅ ወይስ ትንሽ ነው? ከመጥረጊያው አጠገብ ሲሆንስ ምን ይሆናል? እራስዎን ወደ ጨዋታው በመጨመር ማረጋገጥ ይችላሉ- ትልቅ ወይስ ትንሽ ነዎት? በቤተሰብ አባላትም አጠገብ ሲሆኑ ምን ይከሰታል?
ምስሎችን መመልከት
በንባብ ጊዜ ምስሎችን መመልከትና አስደሳች ዝርዝሮችን መፈለግ አለብዎት። ማታን ምን እያደረገ ነው? ምን ያህል እንስሳት ያያሉ? ማን ትልቅና ማን ትንሽ ነው? ድመት የት ላይ ይታያል? በተለይም የትኛውን ምስል ይወዳሉ?
የትኛውን መሆን ይሻላል... ትልቅ ወይስ ትንሽ?
ምን ይሻላል? – ኮዱን ስካን ያድርጉና ከልጆች ጋር አብረው መዘመር ይችላሉ። የትኛው የተሻለ እንደሆነ ያስቡ፦ ትልቅ ወይስ ትንሽ መሆን?
የንባብ ምክር
መጽሐፉን ወደ ጓደኛ እንዴት ይለውጡታል? ከልጅነት ጀምሮ መጽሐፍትን ማንበብ ለታዳጊ ሕፃናት እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ በረክታል። የእኛ ምክር በዝግታ፣ ቀስ በቀስና ለታዳጊ ሕፃን ተስማሚ በሆነ መንገድ መጀመር ነው፡- አንዳንዶች መጽሐፉን መንካት፣ መክፈትና መዝጋት ወይም እንዲያውም “መቅመስ” ሁሉ ይፈልጋሉ። ከዚያ ትንሽ በትዕግስትና በደስታ ማንበብ ትችላላችሁ። ገጽ አንድ ጀምራችሁ አንብቡ፣ ተላመዱት፣ ገፆች ጨምሩበት፣ እነሆም – መጽሐፉ ጓደኛ ሆኗል…!

"አንድ ላይ ማንበብ - "ደህና አደራችሁ
በንባብ ጊዜ “እንደምን አደራችሁ” የሚሉትን ቃላት በልዩ ድምጽና በሠላምታ አሰጣጥ ምልክት አፅንዖት መስጠት ይችላሉ። ታዳጊውን እንዲቀላቀል፣ ታሪኩን እንዲከታተልና የንባብ አጋር እንዲሆን ይጋብዙት። የእራስዎን ሥነ ሥርዓት መፍጠርና “ደህና አደራችሁ”ን መመኘት ይችላሉ። “ደህና አደራችሁ በኩሽና ውስጥ ላለው ወንበር!”፣ “ደህና አደራችሁ በመንገድ ላይ ላለው ዛፍ!”፣ “ደህና አደራችሁ” ለውሻው ቦቢ!”

ዓለምን መመልከት
በታዳጊ ህጻናት እይታ ሁሉም ነገር ስለ ዓለም የሚያስተምር ድንቅ ነገር ነው። ወደ መዋእለ ሕጻናት በሚሄዱበት ጊዜ ወይም ከመውጣትዎ በፊት የሚኖረው ጊዜ የሕፃኑን ትኩረት የሚስበውን በጋራ ለመመልከት እድል ነው። በመስመር ላይ የሚራመዱ ጉንዳኖች፣ ትልቅ የጭነት መኪና፣ ምናልባትም በሰማይ ላይ የሚበሩ የወፎች መንጋ?