סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆኑ ጠቃሚ ምክሮች
ከልጆች ህይወት የታወቁ ልምዶችን የሚገልጹ መጽሃፎች ወደ ዓለማቸዉ በጨረፍታ ለመመልከት እድል ናቸው። በማንበብ ጊዜ በተለይ የልጆቹን ትኩረት የሚስቡትን፣ ምን ጥያቄዎችን እንደሚጠይቁ፣ ከየትኛው ገጸ ባህርይ ጋር እንደሚመሳሰሉ ትኩረት መስጠት አለብዎት። አንዳንድ ጊዜ በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ስለሚፈጸሙ ነገሮች ላይ ማውራትን ቀላል የሚያደርገው መጽሐፉ ነው።
ምርጥ ጓደኛሞች
ውይይት ጨዋታውን መቀላቀል
ልጆቹን በማነጋገር ይጠይቋቸው፦ ሾን ጨዋታውን ሲቀላቀል ብሬት ምን የተሰማው ይመስልዎታል? ከወንድ ወይም ሴት ጓደኛዎ ጋር ተጫውተው እርስዎን ለመቀላቀል የጠየቁዎ ነገር በእርስዎ ላይ ደርሶ ይሆን? ሌሎች ልጆች እንዲቀላቀሉስ ጠይቀው ያውቃሉ?
ምርጥ ጓደኛሞች
ፈጠራ ከጓደኞች ጋር
ከጥሩ ጓደኞች ጋር አንድ ቀላል ሳጥን እንኳን ቤተ መንግስት፣ መርከብ ወይም የጠፈር መንኮራኩር ሊሆን ይችላል። በካርቶን ለመፍጠር ልጆቹ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጓደኞችን ለጋራ ጊዜ እንዲጋብዙ ማቅረብ ይችላሉ። ምናልባትም አንድ ሳጥን ሌላ ምን ሊሆን እንደሚችል ያገኙታል – በትንሽ ሀሳብ፣ መቀሶች፣ ማርከሮችና ከሁሉም በላይ ደግሞ በአንድነት።
ምርጥ ጓደኛሞች
አንዴ ብሬት፣ አንዴ ሾንና አንዴ አርቺ
የቲያትር ጨዋታዎች የሌላውን ልምድ ለመማርና ስሜቶችን ለመግለጽ ጥሩ መንገድ ናቸው። በተለያዩ የቤተሰብ አባላት እርዳታ ወይም በአሻንጉሊት በመታገዝ ታሪኩን በቃል ማቅረብ ይችላሉ። ሚናዎችን በእያንዳንዱ ጊዜ በመቀያየር ታሪኩን ከተለያዩ ገፀ ባህሪያቶች እይታ የሚያገኙ ይሆናል።
ምርጥ ጓደኛሞች
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ልጆች ከመጽሐፉ ጀግኖች ጋር ይተዋወቃሉ። ስለዚህ ከእነርሱ የተለዩትን በተሻለ ሁኔታ ይገነዘባሉ። ከርህራሄና ከአዳዲስ ሁኔታዎች ጋር የመላመድ ችሎታን ያዳብራሉ። በንባብ ጊዜ የመጽሐፉን ጀግኖች አገላለጾች በመመልከት ምን እንደሚሰማቸው ይጠይቁ? እናም ለምን?
ሁለታችን
ውይይት - ለእርስዎ ተስማሚ ነው?
መወያየትና መጠየቅ ይችላሉ፦ እርስዎ ከማን ጋር መጫወት ይወዳሉ? የትኞቹን ጨዋታዎች? ሁሉም ሰው የተለየ ጨዋታ መጫወት ሲፈልግ ምን መደረግ አለበት ብለው ያስባሉ? ምን መፍትሄዎችን ያቀርባሉ?
ሁለታችን
የሚያበሳጭም አዝናኝም የሆነ
ሊቢ የፖፒክን ጉብኝት ወደ ሃካባኢም ጣቢያ መቀላቀል ይፈልጋል፤ ግን ተናደደ – እንዴት መፍትሔ ማግኘት ይቻላል? ቪዲዮውን ይመልከቱ!
ሁለታችን
ከምስሎች ጋር መንቀሳቀስ
መቀመጥ፣ መዝለል፣ ምናልባትም ማጎንበስ? – በእያንዳንዱ ጊዜ ከተሳታፊዎቹ አንዱ ከመጽሐፉ ውስጥ አንድ ገጽ ይመርጥና ከመጽሐፉ ጀግኖች ጋር ተመሳሳይ እንቅስቃሴን ያቀርባል። ተሳታፊዎቹ እንቅስቃሴውን ይኮርጁና ተዛማጅ ገጹን ይፈልጋሉ። ተሳካ? – ሚናዎችን ለመለወጥ ጊዜው አሁን ነው።
ሁለታችን
የጨዋታዎች ጨዋታ
አብረው መጫወት የሚወዷቸውን የጨዋታዎች ስም በገጾች ላይ ይፃፉና ጨዋታውን የሚገልጽ ምስል ይጨምሩ፦ ኳስ፣ ድብብቆሽ፣ ምናልባትም አባሮሽ? – ገጾቹን በሳጥኑ ውስጥ ያስቀምጡና በየቀኑ ማስታወሻ በማውጣት ያረጋግጡ፦ ጨዋታውን አንድ ላይ መጫወት ይፈልጋሉ? – ካልሆነ ሁልጊዜ ሌላ ማስታወሻ ማውጣት ወይም በሳጥኑ ላይ አዲስ ጨዋታ መጨመር ይችላሉ።
ሁለታችን
ውይይት - ለእርስዎ ተስማሚ ነው? የሚያበሳጭም አዝናኝም የሆነ
ሊቢ የፖፒክን ጉብኝት ወደ ሃካባኢም ጣቢያ መቀላቀል ይፈልጋል፤ ግን ተናደደ – እንዴት መፍትሔ ማግኘት ይቻላል? ቪዲዮውን ይመልከቱ!
ሁለታችን
ለቤተሰባዊ ንባብ ጠቃሚ ምክር
ታዳጊ ሕጻናት የታሪኩ አካል መሆንን ይወዳሉ፦ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ቃላትና ድምጾች መድገም ወይም የመጽሐፉን ጀግኖች ድርጊት መተወን። በዚህ መንገድ ታሪኩን ይለያሉ፣ ስሜታዊ የሆነው ዓለማቸውን ያበለጽጋሉ፤ ቃላትንና ጽንሰ-ሐሳቦቻቸውን ያገኛሉ። ስለዚህ የጋራ ንባብ ላይ ጥሩምባን ይዞ “መንፋት”፣ ከበሮውን በእጆቻችሁ “መምታት” እና የሕብረት መዝሙሮች ላይ “መምራት” ይገባል።
ሙዚቃ
ውይይት
ጊሊ ለእርሷ የሚስማማ ሚና አግንታ ኦርኬስትራውን ትመራለች። እርሱን ተከትሎ በቤት ውስጥ ስለ ታዳጊ ሕጻናት ሚናዎች መወያየት ይችላሉ- ምን ያውቃሉና ምን ማድረግ ይፈልጋሉ – መጫወቻዎችን መሰብሰብ? ወለል መጥረግ? ለምግብ ጠረጴዛ ለማዘጋጀት መርዳት?
ሙዚቃ
ሙዚቃ
አብሮ መጫዎት
ማንኛውም ነገር ማለት ይቻላል የሙዚቃ መሳሪያ ሊሆን ይችላል፦ ወደ ዘፈኑ ዜማ እጆቻችሁን በአንድ ላይ ማጨብጨብ ወይም ያገኙትን የሙዚቃ መሳሪያዎች፣ ማራካሾችና መሳሪያዎች መሰብሰብ ይችላሉ። ማንኪያ ያለው ድስት ከበሮ ሊሆን ይችላል፤ ጥቅል ወረቀት እንደ ጥሩምባ ሊያገለግል ይችላል። እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመምታት መሞከርና መፈተን ይችላሉ፦ በእንጨት ሲመታ ምን ዓይነት ድምፆችን ያወጣል? በወለል ንጣፍ ላይስ? በብረት ላይስ? የሚወዱት ዘፈን ላይ ይወስኑና አንድ ላይ መጫወት ይችላሉ።
ሙዚቃ
ኦርኬስትራን መምራት
ማን ነው የሚመራው ማን ነች የምትመራው? – የሚወዱትን ሙዚቃ አንድ ላይ ሲያዳምጡ ትንሽ ዱላ በመያዝ ተጫዋቾቹን “መምራት” ይችላሉ። የሙዚቃው ድምጾች ላይ መደነስና የተለያዩ መሳሪያዎች ላይ መተወን፤ አልፎ አልፎም ሚናዎችን መቀያየር ይችላሉ።
ሙዚቃ
ውይይት - በጋራና በተናጠል
ጋሊና ጋያ ነገሮችን አንድ ላይ ማድረግ ይወዳሉ፤ ግን ደግሞ በተናጠል፦ መወያየትና ማወቅ ትችላላችሁ፦ ታዳጊ ሕጻናት ከወንድም፣ ከሕብረተሰቡ ወይም ከእናንተው ከወላጆች ጋር ምን ማድረግ ይወዳሉ? ብቻቸውንስ ምን ማድረግ ይወዳሉ?
ጋሊና ጋያ
ጋሊና ጋያ ሊጎበኙ ይመጣሉ
ከጋሊና ጋያ ጋር መጫወትና ታሪኩን መተወን ይፈልጋሉ? የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና ሁለት የሚያማምሩ ዳክዬዎችን ፕሪንት በማድረግ ቆርጠው በማውጣት ታሪኩን ከእነርሱ ጋር መተወን ይችላሉ…!
ጋሊና ጋያ
בואו אחריי!
משחק תנועה כמו גלי וגאיה, אפשר לצעוד ביחד: תוכלו להכין בבית שביל ולסמן אותו בחבל או בחפצים שונים, וללכת בטור – זה אחר זה ואולי יחד, זה לצד זה. אפשר גם להתחלף, כשכל פעם המוביל קורא: “בואו אחריי!”
או במעון – המחנכת הולכת בכיתת המעון, והפעוטות הולכים אחריה. מדי פעם המחנכת עוצרת ועושה פעולה מסוימת, והפעוטות מחקים אותה: נוגעים באף, קופצים כמו צפרדע, עפים כמו פרפר, נוגעים בחפצים שונים בכיתה ואומרים את השמות שלהם: שולחן, כיסא או ספר.
ጋሊና ጋያ
እንስሳትና ስዕላዊ መግለጫዎች
በግ፣ እንቁራሪት ወይስ ቢራቢሮ? – ምስሎቹን አንድ ላይ ማየትና የተለያዩ እንስሳትን ማግኘት ይገባል። በስዕሉ ውስጥ ያለውን የእንስሳት ድምጽ ማሰማት ወይም እንደርሱ መንቀሳቀስ ይችላሉ፦ እንደ ቢራቢሮ መብረር፣ እንደ ንብ ጥዝዝ ማለት ወይም … ሌላ እንደ ማን?
ጋሊና ጋያ
ተከተለኝ! - የእንቅስቃሴ ጨዋታ
እንደ ጋሊና ጋያ አብረው መራመድ ይችላሉ፦ በቤት ውስጥ መንገድ ማዘጋጀትና በገመድ ወይም በተለያዩ ነገሮች ምልክት በማድረግ በአንድ አምድ ውስጥ መሄድ ይችላሉ – አንዱ ከሌላው በኋላ ወይም ምናልባትም አንድ ላይ ጎን ለጎን። መሪው “ተከተሉኝ!” ብሎ በጠራ ቁጥር መቀያየርም ደግሞ ይቻላል።
ጋሊና ጋያ
ጋሊና ጋያ
ግጥሞችን ማንበብ
በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት ግጥሞች ትንሽ የሕይወት ጊዜዎችን ያቀርባሉ። በእያንዳንዱ የጋራ ንባብ ውስጥ ሌላ ዘፈን በመምረጥ አንድ ላይ ማንበብ አለብዎት። ዘፈኑ በእርስዎ ላይ የደረሰን ነገር ያስታውሳል? ይህ ለእናንተ፣ ለወላጆች ከልጅነታችሁ ጀምሮ ልምዶቻችሁን እንድትካፈሉና በዚህም ከልጅነትና ከልጆች ጋር መቀራረብንና መጋራትን የምትፈጥሩበት እድል ነው።
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ከሐጊት ቤንዚማን ጋር መተዋወቅ
ደራሲ ሐጊት ቤንዚማን መቼ መጻፍ ጀመረች? እርሷ ስለ ምን ትጽፋለች ለምንስ? – የQR ኮዱን ስካን ካደረጉ ፈጣሪዋንና ስራዋን መተዋወቅ ይችላሉ።
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
የቤተሰብን አልበም መመልከት
የወላጆችን የፎቶ አልበሞች አንድ ላይ በማየት ከልጅነት ጀምሮ ልዩ ጊዜዎችን መፈለግ ጥሩ ሀሳብ ነው። እንዲሁም የልጅነትና የልጆች ቀደምት ፎቶግራፎችን ማየትና የተቀረጹበትን አፍታዎች ማጋራት ይችላሉ። በእናንተ ውስጥ ምን ትዝታ ያስነሳሉ?
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
አንድ ላይ ድራማ መስራት
איזה שיר אהבתם במיוחד? – תוכלו להציג אותו יחד, כשהמבוגרים מציגים את תפקיד הילדים, ולהפך.
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል
ለምን ሁሌም ያስታውሱኛል