סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ይህ አንድ ማየት የተሳነው ወይም ዓይነ ስውር ወንድም ስላለበት አንድ ልዩ ቤተሰብ የሚገልጽ ልዩ መጽሐፍ ነው። ተራኪው ወንድም በቤተሰቡ ውስጥ ያሉትን ችግሮችና በቤት ውስጥ የሚፈለግበትን ውስንነት ጠንቅቆ እያወቀ ነገርግን ዓለምን በአዎንታዊ መልኩ ይመለከታል። ንባቡንና ውይይቱን ከመጽሐፉ ልዩ ይዘት ጋር ለማስተካከል ለእናንተ ወላጆች ከጋራ ንባቡ በፊት መጽሐፉን እንድታነቡ እንመክራለን።
ምን ዓይነት እድል ነው!
ውይይት
በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ እድለኛ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን? በምን እድለኛ ናችሁ? ወላጆችና ልጆች እርስ በርሳችሁ እንደ ቤተሰብ አብረው በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች በተመለከተ ማካፈል ትችላላችሁ። በሳምንት አንድ ጊዜ የቤተሰቡ አባላት ባለፈው ሳምንት ያጋጠሟቸውን አወንታዊ ነገሮች የሚያካፍሉበት መደበኛ ሥርዓት መፍጠር ትችላላችሁ።
ምን ዓይነት እድል ነው!
ምን ታያላችሁ...?
ዓይነ ስውራን ልጆች ሕይወትን እንዴት ይለማመዳሉ? ኮዱን በማድረግ ከዓይነ ስውራን ልጆች ጋር “ለጥያቄው ይቅርታ” የሚለውን ክፍል ማየት ትችላላችሁ። ከቪዲዮው በኋላ መወያየት ጠቃሚ ነው፦ ሕይወታችን እንዴት ተመሳሳይ ነው እንዲሁም በቪዲዮው ውስጥ ካሉት ልጆች እንዴት ይለያሉ?
ምን ዓይነት እድል ነው!
ድጋሜ በማንበብ ምን እናውቃለን?
በሁለተኛው ንባብ አዳዲስና አስገራሚ ነገሮችን ማግኘት ይቻላል። ምስሎችን በመመልከትና የሃጋይን የእይታ እክል ፍንጭ በመፈለግ መጽሐፉን ሁለት ጊዜ ማንበብ ተገቢ ነው፦ ቃላቱና ምስሎቹ ስለቤተሰብ ፈተና ምን ፍንጭ ይሰጣሉ? በመጀመሪያው ንባብ ይህን አስተውላችኋል?
ምን ዓይነት እድል ነው!
ምናባዊ ጨዋታ
ሃጋይ ምናባዊ ታሪኮችን እንዴት እንደሚናገር ያውቃል። እናንተም ሞክሩት! ሁለት እቃዎችን በመምረጥ ምናባዊ ታሪክን ለመተረክ ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ -ብሩሽና ምንጣፍ፣ ጠርሙስና የድመት አሻንጉሊት፣ ኮፍያና መስኮት – እናንተ በጋራ ባሰባሰባችሁት ምናባዊ ታሪክ ውስጥ ምን ሊደርስባቸው ይችላል?
ምን ዓይነት እድል ነው!
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
“ታላቁ የሲማቺ ቀን” ረዘም ያለ መጽሐፍ ነው። ለዚያም ነው በሁለት ክፍሎች ለማንበብ የሚመከረው፦ ሲማቺ ወንድሟ አብራም ለምን የበዓል ልብስ እንደለበሰ ከተገረመች በኋላ ማንበብ ያቁሙና በሚቀጥለው ቀን ማንበብዎን ይቀጥሉ።
የሲማቺ ታላቁ ቀን
ትዝታዎች
በመጽሐፉ ውስጥ አያቱ የልጅነት ጊዜዋን ትዝታ ትተርካለች። ይህ ለእናንተ ለወላጆች ከልጅነታችሁ ጀምሮ ልዩ ጊዜዎችን እንድታካፍሉ እድል ነው። ስላደረጋችኋቸው ነገሮች፣ ከዚህ በፊት ማድረግ እችላለሁ ብላችሁ ያላሰባችሁትን ወይም በእናንተና በወንድሞቻችሁ መካከል ስላለው ግንኙነት ተርኩ። እንዲሁም ልጆቹን ጠይቋቸው፦ ወደ ኋላ በመመልከት በራሳቸው ባገኙት ችሎታ ያስደነቋቸውን ያደረጓቸውን ልዩ ድርጊቶች ማስታወስ ይችላሉ?
የሲማቺ ታላቁ ቀን
የሲማቺ ታላቁ ቀን
አናናስ በራስ ላይ
አብራምና ኔሚ አናናስ ራሳቸው ላይ በማድረግ የመራመድ ጨዋታ ይጫወታሉ። ማን እንደማይጥልም ለማየት ይወዳደራሉ። ተመሳሳይ ጨዋታም መጫወት ትችላላችሁ፦ በራሳችሁ ላይ የምታስቀምጧቸውን ዕቃዎች – ትራስ፣ አሻንጉሊት ወይም ሳጥን ምረጡና፦ ከመካከላችሁ በመራመድ ራሱ ላይ መሸከም የሚችለው ማነው? እስከ ምን ርቀት? የሚለውን አረጋግጡ።
የሲማቺ ታላቁ ቀን
ባህሩን ተከትሎ
ታሪኩ ከባህር ጋር የተያያዙ ብዙ ተግባራትን ይገልፃል፦ የዓሳ እንቅስቃሴ፣ ጀልባ መቅዘፍ፣ ዋና፣ የዓሣ ማጥመጃ መረቦችን መሰብሰብ፣ በመርከብ ምሰሶ ላይ ባንዲራ ማውለብለብ ወይም መስቀል። ከድርጊቶቹ ውስጥ አንዱን በመምረጥ በእንቅስቃሴ ማሳየት ትችላላችሁ። የቤተሰቡ አባላት የትኛውን ድርጊት እንደፈለጉ መገመት የሚኖርባቸው ሲሆን በመጽሐፉ ውስጥ ካሉት ምስሎች ውስጥ የሚፈልጉት ይሆናል። መልካም እድል!
የሲማቺ ታላቁ ቀን
የሲማቺ ታላቁ ቀን
ስለ ፍርሃትና ማበረታታት መወያየት
የሴቶችና ወንዶች ልጆች እድገት ሂደት በተለያዩ ፍርሃቶች የታጀበ ነው። ስለእነርሱ ማውራት እነርሱን ለመቋቋምና የመተማመን ስሜትን ለመፍጠር ይረዳል። ስለ ፍርሃቶች አብረው መወያየት ይችላሉ፦ የሚያስፈራው ምንድን ነው? ለማሸነፍ የሚረዳውስ ምንድን ነው?
እስከ ላይ
እስከ ላይ
በመጫወቻ ስፍራው ውስጥ
ታሪኩን ተመርኩዘው ወደ መጫወቻ ቦታዎች አብረው በመሄድ የተለያዩ መገልገያዎችን በጋራና በተናጠል መሞከር ይችላሉ። እንዲሁም በመገልገያዎች መካከል የሚሄድ ለሁሉም ተሳታፊዎች አስደሳች የሆነ መንገድም ሊያመጡ ይችላሉ።
እስከ ላይ
ቤተሰባዊ ማበረታቻ
ማዕያን ስትፈራ ሁሉም “አይዞሽ ማዕያን!” ይሏታል። እናንተስ እንዴት እርስ በርሳችሁ መበረታታት ትችላላችሁ? በቤተሰብ የማበረታቻ ቃላት ላይ መወሰን፣ ምናልባትም የሚያበረታታ ዘፈን ማግኘት ወይም ደስታንና ጉልበትን የሚሰጣችሁን ንባብ በጋራ ማንበብ ይቻላል።
እስከ ላይ
עַכְשָׁו בָּפּוֹדְקַאסְט שֶׁל סִפְרִיַּת פִּיגָ'מָה!
הַסִּפּוּר לְהַאֲזָנָה – עַכְשָׁו בָּפּוֹדְקַאסְט שֶׁל סִפְרִיַּת פִּיגָ’מָה!
עידוד קריאה משפחתית – כדאי לספר למשפחות שהגיע ספר העוסק בַּכוח ובעידוד שאנחנו שואבים מהמשפחה. הספר מלווה בפסקול להאזנה משפחתית משותפת. הפסקול מתאים גם למשפחות עולים.
እስከ ላይ