סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆኑ ጠቃሚ ምክሮች
ካነበቡ በኋላ ስለ መጽሐፉ ጀግኖች ስሜትና በታሪኩ ውስጥ ከተነሱ ሁኔታዎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት በመነጋገር ከእነርሱ ተነሳሽነትን እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርብዎታል። ሴትና ወንድ ልጆች በታሪኩ ውስጥ ያሉ ገፀ-ባህሪያትን ሲለዩ ለተለያዩ አመለካከቶች ይጋለጣሉ፤ ከራሳቸው ሕይወት የሚያውቋቸውን ስሜቶችና ባህሪያትም ይማራሉ።
ቀጣዩ ተረኛ
መጀመርያ እንዲገባ የሚለው ሃሳብ መልካም ነበር
ታሪኩን በመከተል መወያየት፣ ማጋራትና መጠየቅ ይችላሉ፦ ወረፋ ሲጠብቁ ምን ይሰማዎታል? የእኛ ተራ ከሌሎች የበለጠ አጣዳፊ እንደሆነ ተሰምቶን ያውቃል? አንድ ቡችላ እርሱን ግምት ውስጥ ያስገቡት መሆኑን በምን የሚያውቅ ይመስልዎታል? ኮፊፍና ሌሎች የሚጠባበቁ ሰዎች ተራቸውን ከለቀቁ በኋላ ምን ተሰማቸው? እርስዎን ግምት ውስጥ ስላስገቡ ሰዎች ወይም እርስዎ ሌሎችን ግምት ውስጥ ያስገቡበት ሁኔታ አብረው ለማስታወስ ይሞክሩ።
ቀጣዩ ተረኛ
ተረኛው ማን ነው?
ኮፊፍ፣ ቀጭኔ፣ ዝሆንና አዞ የተራውን ቅደም ተከተል የሚወስን መርህ ለማግኘት ይሞክራሉ። በእነርሱ ተነሳሽነት እያንዳንዱን ጊዜ በተለየ ቅደም ተከተል የሚያስተዳድሩበት ከሁሉም የቤተሰብ አባላት ጋር በመሆን አዝናኝ ጨዋታ መጫወት ይችላሉ። ለምሳሌ፦ በእድሜ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ወይም በሸሚዝ ቀለም ከደማቅ እስከ ፈዛዛ ምናልባትም ምን ያህል አይስ ክሬምን እንደሚወዱ ቅደም ተከተልን መስጠት ይችላሉ። የተለያዩ አዝናኝ ባህሪያትን በአንድ ላይ ማምጣትና ማረጋገጥ ይቻላል- አሁን ላይ ማን ነው ቀጣዩ?
ቀጣዩ ተረኛ
ጠብቆ መዝናናት
ኮፊፍ የጥበቃ ጊዜውን ያሳለፈው እንዴት ነው? አብረውት ከሚጠባበቁት ጋር ተነጋግሮ ለወረፋው ቅደም ተከተል ሀሳብ በማቅረብ አዳዲስ ጓደኞችን አፍርቷል። እርስዎም አንድ ላይ ሆነው አንድ ነገር ሲጠብቁ ጊዜዎን እንዲያሳልፉ የሚያግዙ ሀሳቦችን ማምጣት ይችላሉ። በተጠባባቂ ላይ እያሉ ሊዘፍኑት የሚችሉትን አዝናኝ ዘፈን፣ የጣት እንቅስቃሴ ጨዋታና ጊዜውን እንዲያሳልፉ የሚረዳዎትን ሃሳብ መስራት ይችላሉ – መጽሐፍ፣ የስዕል ደብተር፣ እንቆቅልሽ፣ የመከላክል ኳስ። ወይም ወደ አእምሮዎ የሚመጣ ሌላ ማንኛውም አዝናኝ ሀሳብ።
ቀጣዩ ተረኛ
QR ኮድ
እንዴት ኮፊፍ እንደሚሰማ ማዎቅ ይፈልጋሉ? ዶ/ር ጽቢያ እንዴት እንደምትሰማስ? ኮዱን ስካን ያድርጉና ታሪኩን ያድምጡ።
ቀጣዩ ተረኛ
ለቤተሰብ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
በጋራ ማንበብ ሴቶችና ወንዶች ልጆች በታሪኩ ውስጥ የተለያዩ ገጸ-ባህርያት ያላቸውን እንዲለዩ ያስችላቸዋል። መለየቱ ሲመሰረት ለሌላው እንደ መራራትና መተሳሰብ ያሉ ውስብስብ ስሜቶች ላይ መወያየት ይችላሉ።
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ውይይት - ለእርሱ ... እናት ብሆን
በቤተሰብዎ ውስጥ የእያንዳንዷና የእያንዳንዱ ሚናዎች ምንድን ናቸው? ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጋሉ? በመጽሐፉ መንፈስ ውስጥ በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሚናዎችን መቀየር ላይ አብረው መገመት ይችላሉ – ልጆቹ ከአያት ጋር ቢቀያየሩ ምን ያደርጋሉ? አያትስ ከእናት ጋር ቢቀያየር ምን ያደርጋል? እንዴትስ እርስ በርሳችሁ መረዳዳት ትችላላችሁ?
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ታሪኩን ማዳመጥ
በሰልፉ ውስጥ ምን መጫዎት ይቻላል? በኦርኬስትራ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች እንዴት ይሰማሉ? – እነዚህ ሁሉና ሌሎችም ኮዱን ስካን በማድረግ ታሪኩን ሲያዳምጡ ይጠብቁዎታል።
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ጨዋታ – ሙያዬ ነው
ገጸ ባህርይው ማን ነው፦ ዶክተር ወይስ ምናልባት ቀልደኛ? – በእያንዳንዱ ዙር ተሳታፊዎች አንድ ባለሙያን ይመርጡና በትወና አቅርበው ተሳታፊዎቹ ገጸ ባህርይው ማን እንደሆነ መገመት አለባቸው። ለመገመት ትንሽ ይከብዳል? – ፍንጭ መስጠት ይቻላል።
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ወደ ሥዕላዊ መግለጫዎች መግባት
በታሪኩ ውስጥ ከማን ጋር መለዋወጥ ይፈልጉ ነበር? መጽሐፉን ማገላበጥ፣ መቀየር የሚፈልጉትን ሰው መምረጥና እርስ በርስ መጋራት ይችላሉ፦ ጋጋሪውን መቀየር ይፈልጋሉ? በሰልፍ ውስጥ የሚጫወተውን?
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ጓደኛ ጓደኛን ይቀይራል
ውይይት - ግምት ውስጥ ማስገባት
ግምት ውስጥ ስለማስገባት መወያየት ይችላሉ-“ግምት ውስጥ ማስገባት ” ምንድን ነው? በታሪኩ ውስጥ ማንን ማን ግምት ውስጥ አስገባ? – አንድ ሰው እርስዎን ግምት ውስጥ ያስገባበትን አጋጣሚዎች ማካፈል አስፈላጊ ነው – ምን ሆነ ምንስ ተሰማዎት? በቤተሰብስ ውስጥ እርስ በርስ መተሳሰብ የሚቻለው እንዴት ነው?
ይህ ያገባኛል ያለው ጃርት
משחק – מצאו אותי!
የጃርቱን ቤት የሚያሳየውን ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ።
በእያንዳንዱ ዙር ከተሳታፊዎቹ አንዱ በሥዕላዊ መግለጫው ላይ ያለውን ነገር ይጠቁማል። ይህ ነገር በእርስዎ ቤት ውስጥ የት አለ? ሌሎች ተሳታፊዎች እንዲያገኙት ይጋበዛሉ።
ይህ ያገባኛል ያለው ጃርት
እንስሳትና ሥዕላዊ መግለጫዎች
የመጽሐፉ ጀግኖች ጃርት፣ ጥንቸልና አይጥ ናቸው። በመጽሐፉ ውስጥ በተገለጹት ሥዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ብዙ እንስሳት ይታያሉ – ልታገኟቸው ትችላላችሁ? ስንት እንስሳት አገኛችሁ?
ይህ ያገባኛል ያለው ጃርት
ውይይት
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ቤተሰቦች ባቡሩን ለመስራት እና የወንድ አያት ዶቭን ልደት ለማክበር እየተጣደፉ ነው፣ ነገር ግን አባላቶቹ ለሌሎች አሳቢ መሆን፣ እና እንስሳትን እና አካባቢን መንከባከብን ያስታውሳሉ። ምናልባት አሳቢ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መሞከር እና መወያየት ይፈልጋሉ – ሌሎች ለእርስዎ አሳቢ እንዲሆኑ እንዴት ይፈልጋሉ? ለአስቸኳይ አካባቢዎ ወይም በቤተሰብዎ ውስጥ ለመርዳት ማንን ሊሰጡ ይችላሉ? የቤተሰብዎን ትልልቅ አባላት ለማስደሰት ምን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ?
ይፍጠኑ!
በመጫወት "በፍጥነት ወይስ በዝግታ?"
“ፈጣን ወይም በዝግታ (fast or slow)” የሚባል ጨዋታ መጫወት ሊደሰቱ ይችላሉ፦ አንድን ድርጊት ለመምረጥ ተራ ይጠብቁ እናም ሌሎች ተጫዋቾች በፍጥነት ወይም በዝግታ እንዲጫወቱት ይንገሩዋቸው። ለምሳሌ፣ እጆቻችሁን አጨብጭቡ… በፍጥነት፣ እና አሁን… በዝግታ፤ አንድ መዝሙሩ በጣም በዝግታ ይዘምሩ እና ከዚያ በጣም-በፍጥነት! ከተጫወቱ በኋላ ምን በፍጥነት ማድረግ እንደወደዱ እና ምን በዝግታ መስራት የበለጠ አስደሳች የሆነውን ነገር ለመወያየት እና ለማወቅ ይፈልጉ ይሆናል።
ይፍጠኑ!
የተደበቁ ማብራሪያዎች
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ማብራሪያዎች እጅግ በጣም ዝርዝር ናቸው። የሚወዱትን ገጽ ስለመምረጥ እና በውስጡ ያሉትን ጥቃቅን ዝርዝሮች እንዴት እንደሚፈልጉ? ምናልባት በሥዕሉ ላይ አንድን ዝርዝር ነገር ማየት ይችሉ እንደሆነ አንዳችሁ ሌላውን ለመጠየቅ ተራ በተራ ማድረግ ትችላላችሁ። የወንድ አያት የዶቭ ስጦታ የት አለ? የእግር ኳሱ የት አለ? ቴዲ ቢርን ማን ሊያገኘው ይችላል?
ይፍጠኑ!
ዓይነቶች…
ይህ መጽሐፍ የእጽዋት፣ የአሻንጉሊት፣ የድመቶች እና የሙዚቃ መሳሪያዎች ዓይነቶችን ይገልጻል። ምናልባት ተራ በተራ እንዲመርጡ ያነሳሳዎታል እና ሌሎች ተጫዋቾች በተቻለ መጠን ከእሱ ጋር የተያያዙ ነገሮችን እንዲዘረዝሩ ማድረግ። እንደ ልብስ፣ የጓደኞች ስም፣ የአሻንጉሊት አይነቶች ወይም የሙዚቃ መሳሪያዎች ያሉ ርዕሶችን መምረጥ ይችላሉ።
ይፍጠኑ!