סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ግንኙነት
ከዚህ በፊት ስለተዋወቃችኋቸው ወይም ስለምታውቋቸው አረጋውያን መናገር ትችላላችሁ። እነማን ነበሩ? ከዚህ በፊት ከእነርሱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ነበር? አሁን አንድ ላይ ምን ማድረግ ይወዳሉ? እናንተ ወላጆች፣ ከልጅነታችሁ ጋር አብረው ሲሄዱ ከቆዩ ገፀ ባህርያት ምን ትዝታ አላችሁ?
ልደታችን ነው
ታሪክ መስማት
ታሪኩን ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ኮዱን ስካን በማድረግ መጽሐፉን እያገላበጡ ቤት ውስጥ፣ እየተጓዙ ወይም በፈለጋችሁት ጊዜ ታሪኩን አብራችሁ ማዳመጥ ትችላላችሁ።
ልደታችን ነው
"ጌታዬ ንጉስ ሆይ ሰላም"
አሚራ በአንድ ወቅት የተጫወተችውን ጨዋታ ለመጫወት አስባለች – እናንተም ትችላላችሁ! እንዴት ነው የምንጫወተው? ከተሳታፊዎቹ አንዱ “ንጉሱ” ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በፊቱ መጥተው “ሰላም ጌታዬ ንጉስ ሆይ!” የሚሉ “ልጆቹ” ናቸው። ንጉሱም መልሶ “ሰላም ውድ ልጆቼ! የት ነበራችሁ? ምንስ እያደረጋችሁ ነበር?” ልጆቹ የት እንደነበሩና ምን እንዳደረጉ ያለ ቃላት የሰውነት እንቅስቃሴዎችንና የፊት ገጽታዎችን በመጠቀም ማብራራት አለባቸው። ንጉሱም መገመት አለበት። ሚናዎችን መቀየር ይቻላል፤ የሚፈለግም ነው።
ልደታችን ነው
የድግስ ሰበብ
ዓልማ በአስማታዊ ቆብና አስደናቂ መጠጥ የጠንቋዮች ድግስ አቅዳለች። ጠንቋዮችና አስማተኞች እንዲቀላቀሉ ጋብዛለች። እናንተም አስማታዊ ድግስ ለማዘጋጀት ማቀድ ትችላላችሁ… በራሳችሁ አስማታዊ ሃሳቦች። ምናልባትም የበዓል ድግስ? የጨዋታ ድግስ? ወይስ በሌላ ርዕስ ላይ የምትወዱት ድግስ?
ልደታችን ነው