סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
በቁጣ በእርጋታ
ከልጆች ጋር መነጋገርና መጠየቅ ይችላሉ፦ ከጓደኛዎ ወይም ከቤተሰብ አባል ጋር ከ”ተናደዱ” ምን ይሰማዎታል? እርስዎና እነርሱስ በትግል ወቅት ምን ዓይነት ባህሪ ያሳያሉ? ለማስታረቅ ምን ሊረዳ ይችላል? “በጭንቀት” ውስጥ ባሉ ጓደኞች መካከል እንዴት ማስታረቅ ይቻላል?
ዘላለማዊ መረጋጋት
ዘላለማዊ መረጋጋት
ሠላምን ማሳደር
በታሪኩ ተነሳሽነት ጥንድ አሻንጉሊቶችን፣ የአሻንጉሊት መኪናዎችን ወይም የመረጡትን ጥንድ እቃዎች በእጆችዎ ላይ የሚለብሱትን ካልሲዎች እንኳን መውሰድ ይችላሉ። ልጆችዎን እንዲገምቱና “እውነተኛ ትግል” እንዲፈጥሩ ይጋብዙ – ስለ ምን እየተዋጉ ነው? እንዴትስ ይታረቃሉ? በራሳቸው ያጠናቅቃሉ ወይንስ መታገዝ አለባቸው? እንዴት? አሁን የዝግጅት አቀራረብ ማድረግ ይችላሉ።
ዘላለማዊ መረጋጋት
መመርመርና ማዎቅ
የዓለት ጥንቸልና የተራራ ፍየል ከእስራኤል ምድር የመጡ የበረሃ እንስሳት ናቸው። መጽሐፉ ለመተዋወቅና ለማሰስ ጥሩ እድል ይሰጣል! በእውነታው ላይ እንዴት ይታያሉ? በምን ይታወቃል? ምን መብላት ይወዳሉ? ስለእነርሱስ ለማወቅ ሌላ ምን ፍላጎት አለዎት?
ዘላለማዊ መረጋጋት
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
በንባብ ጊዜ የተለያዩ ድምፆችን በመጨመር ልጆቹም እንዲያደርጉ መጋበዝ ትችላላችሁ፦ እንባ ያፈሰሰ ሰው ምን ይመስላል? በግድግዳው ላይ ጉድጓድ መቆፈር እንዴት ይሰማል? ምንም እንኳን እናንተ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ባትሆኑም በታሪኩ ውስጥ ያላችሁ ንቁ ተሳትፎ ወደ ጋራ ልምድና ደስታ ይመራል።
ጥሩ ስም ይሻላል
የልጆች ጥበብ
ዳኛው በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዴት እንደሚፈርድ ከልጅቷ ይማራል። እርሱን ተከትሎ ልጆቻችሁ ስላላቸው እውቀትና ጥንካሬዎች መነጋገር ትችላላችሁ፦ ልምዳቸውንና ጥበባቸውን ያመጡበት ክስተት የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ፣ ማስተዋል ወይም የጋራ ትውስታ ሊሆን ይችላል። እናንተ ወላጆች እንዲሁም ማካፈል ይኖርባችኋል፦ ከሴት ወይም ከወንድ ልጆቻችሁ ምን ተማራችሁ?
ጥሩ ስም ይሻላል
በውሃ ላይ ምን ይንሳፈፋል?
የዘይት ጠብታዎች በእውነቱ በውሃ ውስጥ ይንሳፈፋሉ? በውሃ የተሞላ ጎድጓዳ ሳህንንና ጥቂት የዘይት ጠብታዎችን በመጠቀም እራሳችሁን ማረጋገጥ ትችላላችሁ። ከዚያ በኋላ ሌላ ምን እንደሚንሳፈፍ ማረጋገጥ ትችላላችሁ፦ በውሃ ውስጥ ያለ ወረቀት ምን ይሆናል? ለወረቀት ጀልባስ? ሹካ? ቅጠል? ለትንሽ የፕላስቲክ አሻንጉሊት?
ጥሩ ስም ይሻላል
ክፍፍልን ማስወገድ
በታሪኩ ውስጥ እንደሚታየው እርስዎም ባልተስማሙበት ርዕስ ላይ አለመግባባት ለመፍታት መሞከር ትችላላችሁ፦ እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን አቋማቸውን ሲያቀርቡ ሁሉም ያዳምጡና መፍትሔዎችን ይሰጣሉ። እንዲሁም ሚናዎችን መቀያየርና አንድ ላይ መፈተሽ ትችላላችሁ፦ ከእናንተ አንዱ ብቻ ትክክል ነው? ምናልባትም የተለየ ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል ይሆን?
ጥሩ ስም ይሻላል
እውነታ ወይስ ምናብ?
ታሪኮችን መናገርና ታሪኮችን መስማት አስደሳች ነው፤ የጋራ ልምዱ ሁሉም ሰው የተሻለ ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል። አንድ ላይ በመነጋገር ያስቡ – በምናብ ውስጥ መጓዝና ታሪክን መንገር መቼ ተገቢ ነው? ምንም ሳይጨመርና ሳይቀነስ ምን እንደ ሆነ መናገር መቼ ይሻላል? በጥርጣሬ ጊዜ ለማማከር ምቹና ተስማሚ የሚሆነው ከማን ጋር ነው?
ታሪክ ይስሙ
ትናንት ምን ገጠመኝ
ትናንት የሆነውን ማን ያስታውሳል? በታሪክ መልክ ሊገልጹት ይችላሉ? አጋጣሚውን ይጠቀሙና ተሞክሮዎችን ያካፍሉ። እንዲሁም መጫወት ይችላሉ፦ ከተሳታፊዎቹ አንዱ ታሪክን ሲናገር የተቀሩት ደግሞ በታሪኩ ውስጥ በትክክል ምን እንደተፈጠረና ምናባዊ ፈጠራ ምን እንደሆነ ለማወቅ መሞከር ይኖርባቸዋል።
ታሪክ ይስሙ
እዚህ ያዳምጡ
ሻሃር ለመካፈል ወይም ለመመካከር ስትፈልግ ሁል ጊዜ በሄርዝል ሀሾመር አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጣ የሚያዳምጥ ጆሮ ማግኘት ትችላለች። በቤቱ ውስጥ አንድ ጥግ ምረጥ እና ሁልጊዜ መናገር እና መስማት የምትችልበት ጥግ አውጅ። በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ በእሱ ውስጥ መቀመጥ, ታሪኮችን ማጋራት እና ምክሮችን ማጋራት ይችላሉ.
ታሪክ ይስሙ
ውይይት - ብልሁ ማን ነው
መወያየትና ማጋራት ይችላሉ- በእርስዎ አስተያየት ብልሁ ማነው? አንድ ሰው በጥበብ ስላደረገው ጉዳይ መተረክ ይችላሉ? ቀበሮው ብልህ ነው ወይስ ዶሮው? ምናልባት ሁለቱም ወይስ ማናቸውም?
ቀበሮው ሰላምን ያበስራል
ስለ ሌቪን ኪፕኒስ አምስት ነገሮች
ሌቪን ኪፕኒስ በልጅነቱ ምን አደረገ? ከቀልድ [ኮሚክስ] ጋር የነበረው ግንኙነትስ? – የኪው አር ኮዱን ስካን ያድርጉና ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ቀበሮው ሰላምን ያበስራል
ጨዋታ - በእውነቱ ምን ሆነ?
ታሪኩን ተከትላችሁ እናንተ፣ ወላጆች፣ አንድ ታሪክ ይናገሩና ተሳታፊዎች በእውነቱ የሆነ ወይም የተፈጠረ ታሪክ እንደሆነ እንዲወስኑ ብሎም ልጆቹ የራሳቸውን ታሪክ እንዲያካፍሉ መጠየቅ ትችላላችሁ። ያልተለመዱ ክስተቶችን እርስ በእርስ ለመለዋወጥ እንዲሁም አብረው ለመሳቅ ይህ እድል ነው።
ቀበሮው ሰላምን ያበስራል
ራም-ኮልና ሌሎች ስሞች
‘’ራም ኮል’’ የሚለው ስም ስለ ዶሮው ምን ያስተምራል? እርስዎንስ ስለሚለዩ ልዩና ጥሩ ጥራትን የሚያስተምሩ ለራስዎ ምን ስሞችን መፍጠር ይችላሉ? ምናልባት የቤተሰብ አባላት ሊረዱዎት ይችላሉ?
ቀበሮው ሰላምን ያበስራል