סִפְרֵי הַחֹדֶשׁ
እየሞከሩ አለመሳካት ተስፋ አስቆራጭ ነው። ነገር ግን በታሪኩ ውስጥ ያለችው ልጅ ተስፋ አትቆርጥም። ምንም እድል የሌለው ቢመስልም የምታስበውን አስደናቂ ነገር ለመገንባት ደጋግማ ትሞክራለች። በራእይና በእውነታው መካከል ስላለው ክፍተት፣ ስለ ቆራጥነት፣ ታታሪነትና ጥሩ መንፈስ ላይ የሚያሳይ ፈጠራዊና ስሜታዊ ታሪክ።
הוצאה: כנפיים וכתר
በቴል አቪቭ ውስጥ የአየር ንብረቱ የሚፈቅድ ከሆነ በክረምቱ ወቅት ወደ አያት ሄዶ አብሮ ወደ ባህር ዳርቻ መሄድ ምን ያህል መልካም ነው። አያቱና የልጅ ልጃቸው የአየር ትንበያውንና በአያትየው የልጅነት ቋንቋ በሆነው በላዲኖ ቋንቋ ከሩቅ ቦታ ሆኖ የሚሰማውን ጣፋጭ የልጅነት ትዝታዎችን የሚያመጣውን የቆየ ዜማ ያዳምጣሉ።
הוצאה: עם עובד
ጥንቸሉ ቺኮ ለጓደኛው ዝሆኑ ፊልሐስ የስድብ ቃል ይናገረዋል። ቃላቱ ከአፉ እንደወጡ ቺኮ ይጸጸትና የጓደኛው ጆሮ ከመድረሳቸው በፊት እነርሱን ለማስቆም ይሄዳል። ቆይ ግን በእርግጥ ቀድሞውኑ የወጣውን ቃል ማቆም ይቻላል? ቃላቱስ በጊዜ ካልተያዙ በፊልሐስና በቺኮ መካከል ያለው ጓደኝነት ምን ይሆን ይሆን? - ስለ ጓደኝነትና ስለቃል ኃይል የሚያትት ታሪክ።
הוצאה: כנרת
አያት ያሽካ በባህር ዳርቻ ላይ ይኖራል። ወፎችን ይፈልጋል፤ ፈጠራዎችን ይፈጥራል። የገንቢዎች ቡድን ወደ ባህር ዳርቻ ሲደርስ አያት ኢሽካና ልጆቹ ኡዲና ታማር ወራሪዎችን ለመዋጋትና በባህር ዳርቻ ላይ ፋብሪካ ወይም ሕንፃ እንዳይቋቋም ለመከላከል ኃይላቸውን ያስተባብራሉ። ግን ግንበኞች ያቀዱት ይህንን ነበር? አካባቢንና ተፈጥሮን የሚያከብር የደራሲና ሠዓሊ ዮሲ አቡላፊያ አዝናኝ ታሪክ።
יש להזין את הקוד שנשלח כדי להיכנס
להאזנה לחצו