סִפְרֵי הַחֹדֶשׁ
"እንዲሁ ያለ ምንም ልዩ ጥረት አራቱ ሽላፉኖቼዎች ባሕሩ ውስጥ ይጓዛሉ" - ግን ወይኔ በድንገት በጀልባው ውስጥ አንድ ቀዳዳ ታየ! ሽላፉኖቼዎች ምን ያደርጉ ይሆን? ከአራቱ አንዱ ብልሃትን በማምጣት ችግሩን ይፈታ ይሆን? ስለ ግላዊና ማህበራዊ ሃላፊነት በቀልድ የተሞላ ታሪክ።
הוצאה: כתר
ዳዊት በፀጉሩ ላይ አበባ ያለው ልጅ ነው። አንድ ቀን የአበባው ቅጠል መውደቅ ጀመረና ጓደኛው አበቦቹን ወደ ጭንቅላቱ ለመመለስና በፊቱ ላይ ፈገግታን ለመመለስ ይሞክራል። ልዩ የሆነ ታሪክ፣ ለሌሎች ስሜታዊነትና ጥልቅ ጓደኝነት በስሱና ስሜት አዘል በሆኑ ቃላትና ምሥሎች ከፊታችን ቀርቧል።
הוצאה: צלטנר
ሾሃም ልክ እንደ አያት አምባር ተወዳጅና ልዩ የእጅ አምባር አላት። ሾሃምና ቤተሰቧ ዒራቅን ለቀው ወደ እስራኤል ሲሰደዱ ከአምባሩ ጋር ለመለያየት ትገደዳለች። የሆነ ጊዜ እንደገና ተመልሳ ታየው ይሆን? የፒታ ዳቦ ከረጢጽ እንዴት ሊረዳ ይችላል? ስለ ቅርስ፣ ዓሊያና ለአገር ብሎም ለቤተሰብ ስለሚኖር ፍቅር የሚያሳይ አስደሳች ታሪክ።
הוצאה: אגם
ትንሹ ጉጉት ሹፎን ልክ እንደ ጉጉቶች ሁሉ ማንበብን ይማራል። ግን ልክ ከትልቅ የጉጉት ኳስ በፊት - ሹፎን ሁሉንም ነገር ገልብጦ ያነባል። ሹፎን ከሌሎቹ ጉጉቶች ሁሉ ፊት እንዴት ያነብ ይሆን? - ስለ ፈጠራዊ አስተሳሰብ ታሪክ፣ ጥቅሞች ስላሏቸው ድክመቶችም እንዲሁ ዓለምን ከተለየ እይታ የማየት ኃይል ጋር።
הוצאה: הקיבוץ המאוחד
יש להזין את הקוד שנשלח כדי להיכנס
להאזנה לחצו