סִפְרֵי הַחֹדֶשׁ
"ዛፎቹ ምን ያደርጋሉ? ያድጋሉ። ቤቶቹስ ምን ያደርጋሉ? ይቆማሉ" - ወደ ታዋቂው የዓይን ሂሌል መዝሙርና ወደ አዳዲሶቹ የዳቪድ ፖሎንስኪ ምሥሎች ተቀላቅሏል። አንድ ላይ ጊዜን በቃላትና በምሥሎች የሚገልጽ አስማታዊ ስራ ይፈጥራሉ።
הוצאה: ספרית פועלים
አንድ አይጥ በአትክልቱ ውስጥ አንድ ነገር እየቆፈረ ነው ... ግን ይሄ የሆነ ነገር ምን ይሆን? - ድንቅ፣ የሚያምር፣ ታላቅና የሚያብረቀርቅ ነገር! ጥንቸል፣ ጃርት፣ ባጀርና ኤሊ አብረውት ይቀላቀሉና ሁሉም በቡድን አብረው የሚዝናኑበት አስደናቂ ነገር እስኪያገኙ ድረስ አብረው የሚፈልጉበት።
הוצאה: זברה
ዮ-ዮ በሠንበት ዝግጅት ላይ በጣም ተጠምዷል። አንድ ሐብሐብ፣ ሁለት ደበርጃን፣ ሦስት ቲማቲሞች... የሸመታ ቅርጫቱ እስኪሞላ ድረስ ይገዛል። የሠንበት ዝግጅትንና ጉጉትን የሚገልፅ የህፃናት ደራሲዋ ዳቲያ ቤን ዶር አዝናኝና አጫዋች ታሪክ።
הוצאה: מודן
አቪቭ ክፍሉን እራሷ ለማፅዳት በጣም ትንሽ እንደሆነች በማሰብ በክፍሏ ውስጥ ያሉትን አሻንጉሊቶች እንዲያጸዱላት ጠይቃለች። ነገር ግን እያንዳንዳቸው አሻንጉሊቶች የራሳቸው ችግር አለባቸው። አቪቭ ክፍሉን ብቻዋን ሆና ማዘጋጀት ትችል ይሆን? የአሻንጉሊት ጓደኞቿንስ መርዳት ትችላለች? - በልጆች ችሎታ ላይ ስለ ነፃነትና እምነት የሚያሳይ ጣፋጭ ታሪክ።
הוצאה: כנרת
በድንገት አንድ ትልቅ አዞ ባቡሩ ውስጥ ይገባና ማንንም ሳያስብ ሙሉ ጋሪ ለራሱ ይወስዳል። ወደ እርሱ ለመቅረብ ማን ይደፍር ይሆን? አዞውስ በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ግምት ውስጥ ለማስገባት ይስማማ ይሆን? - ስለ ጭፍን ጥላቻና ለሌሎች አሳቢነት የሚይሳይ መጽሐፍ።
አንዲት ሴት በመንገድ ላይ ጉዞ እያደረገች እያለ በቀላሉ ሊኖሯት የሚገቡትን ብዙ ብዙ ነገሮችን ትሰበስባለች፦ ፋኖስ፣ የአበባ ማስቀመጫ፣ ቡችላ፣ በቀቀን፣ ማንዶሊን... ግን ብዙ ሰብስባስ ሊሆን ይችላል? አንድ ተጨማሪ ብርጭቆ ጭማቂስ ሲፈልጉ ምን ይሆናል? - ስለ ፍጆታና ስግብግብነት አስደሳች ታሪክ በደራሲው ዮራም ታሃርሌቭ ነፍስ ይማር አስደናቂ ቋንቋ።
ዕብራይስጥ የማይገባት አዲስ ገቢ መሆን ቀላል አይደለም። ኒኖ መዝፈን ትወዳለች፤ ግን ወደ እስራኤል ሃገር ስትደርስ ዝምታን መርጣለች። የእርሷን ድምጽ እንደገና ማግኘት ትችል ይሆን? የዕድሜዋ አቻ የሆነቺው ጎረቤቷስ ምን ልትነግራት እየሞከረች እንደሆነ ትረዳ ይሆን? ስለ ዓሊያና በእስራኤል ውስጥ ስርን ስለ መትከል የሚናገር ታሪክ።
הוצאה: מ' מזרחי
יש להזין את הקוד שנשלח כדי להיכנס
להאזנה לחצו