סִפְרֵי הַחֹדֶשׁ
በርትና አርቺ ምርጥ ጓደኛሞች ናቸው። በየቀኑ አብረው ወደ ኮረብታው ይወጡና በካርቶን ሳጥኖቻቸው ውስጥ ይጫወታሉ። ሦስተኛ ልጅ ወደ ቡድኑ ለመግባት ሲሞክር ምን ይከሠታል? ምርጥ ጓደኛሞች ቀውሶችንና ደፋር ጓደኝነትን ስለመቋቋም የሚያሳይ ስሜታዊ ታሪክ ነው።
הוצאה: אגם
ቴይለር የገነባው አስደናቂው የኩብ ማማ ልክ እንዲሁ ሲፈርስበት ጊዜ ሁሉም እንስሳት ሊያስደስቱት ይሞክራሉ። ነገር ግን ማንም አልተሳካለትም። ሁሉም ትተውት እንደሄዱ ያስታውሰናል። አንዳንድ ጊዜ ጓደኛን ለማስደሰት የሚያስፈልግዎ ነገር እርሱን ዝም ብሎ ማዳመጥ ነው።
הוצאה: תכלת
በአያት ጓሮ ውስጥ ፍሬ የማያፈራ ግን... ከዋክብት የሚወጡበት ድንቅ የሆነ ዛፍ ይበቅላል! እውነት ነው አያት ኮከቦችን መሸጥ አልቻለም። ነገር ግን አላዘነም፤ ምክንያቱም "ሀብቱ በእርሱ ዘንድ ስለሚኖርና ገንዘብ እነርሱ ጋር ስለሚሆን"። የከዋክብቱ ዛፍ በገንዘብ ስለማይገዙ ውድ ነገሮች ስለ አያትና ልጅ፣ ስለ ምናብ፣ ስለ ደስታና አስማታዊ ዘፈን ነው።
הוצאה: המבוך
ከሐኪሙ በር ውጭ ወረፋው ረዥም ነው - ዝንጀሮ፣ ዝሆን፣ አዞና ቀጭኔ እየጠበቁ ነው። መጀመሪያ ማን እንደሚገባው እንዴት ይወስናሉ? ቀጣዩ ተረኛ ስለ ትዕግስት፣ ሌሎችን ስለመርዳትና ሌሎችን ስለማሰብ የሚያሳይ ታሪክ ነው።
הוצאה: כנרת
የዋልያ ልጅና የጥንቸል ልጅ ይጣላሉ። እርስ በርስ ለመነጋገር ፈቃደኛ ካልሆኑ እንዴት በመታረቅ እንደገና ጓደኛ ይሆናሉ? ጥንድ ትንሽ እርግቦች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ? ለዘላለም የሚከፈል ስለ ጸብ፣ ስለ ጓደኝነትና ስለ ሰላም የሚናገር የግጥም መድብል ነው።
הוצאה: ספרית פועלים
በሞሻቫ ሪሾን ለጺዮን ትምህርት ቤት የዕብራይስጥ ቋንቋ ብቻ ይነገራል። ትንሿ ንግሥት ይህን ለማድረግ እየሞከረች ነው። ነገሩን ለምትወደው መምህሯ ቃል ትገባለች። ግን ሃባሮን ሮትሺልድ ሊጎበኛት ሲመጣ ምን ታደርጋለች? ቃል የገባች ቢሆንም በፈረንሳይኛ ታነጋግረው ይሆን? ወርቃማ ፀጉር ያላት ልጃገረድ በመጀመሪያው ትምህርት ቤት ውስጥ የማስተማሪያ ቋንቋ ዕብራይስጥ እንደሆነና የዕብራይስጥ ቋንቋን ስለመውደድ የሚያሳይ ታሪክ ነው።
አባዬ ወደ ድብቅ ፏፏቴ በሚደረገው ጉዞ መነፅሩን ሲያጣ ጉዞው ወደ ፍለጋ ይቀየራል። ሁሉም ተጓዦች ከትልቅ እስከ ትንሽ አባዬ እንዲያገኝ ይተባበሩትና በሂደቱም ውስጥ ፏፏቴውን በማጽዳት ሌሎችንና አካባቢን ለመርዳት ያግዛሉ።
הוצאה: עם עובד
יש להזין את הקוד שנשלח כדי להיכנס
להאזנה לחצו