דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ወርቃማ ፀጉር ያላት ልጃገረድ


በ: ቴልማ ኤሊጎን-ሮዝ ምሳሌዎች: ኖዓም ናዳቭ

በሞሻቫ ሪሾን ለጺዮን ትምህርት ቤት የዕብራይስጥ ቋንቋ ብቻ ይነገራል። ትንሿ ንግሥት ይህን ለማድረግ እየሞከረች ነው። ነገሩን ለምትወደው መምህሯ ቃል ትገባለች። ግን ሃባሮን ሮትሺልድ ሊጎበኛት ሲመጣ ምን ታደርጋለች? ቃል የገባች ቢሆንም በፈረንሳይኛ ታነጋግረው ይሆን? ወርቃማ ፀጉር ያላት ልጃገረድ በመጀመሪያው ትምህርት ቤት ውስጥ የማስተማሪያ ቋንቋ ዕብራይስጥ እንደሆነና የዕብራይስጥ ቋንቋን ስለመውደድ የሚያሳይ ታሪክ ነው።

የእድሜ ክልል: መዋዕለ ሕጻናት

በቤት ውስጥ የተለየ ቋንቋ መናገር ለምዶ በመጀመሪያው የዕብራይሥጥ መዋለ ሕጻናትና የመጀመሪያው የዕብራይሥጥ ትምህርት ቤት ሴት ልጅ መሆን ምን ይመስላል? በትንሿ ንግስት አጣብቂኝ መንገድ ላይ በአስደሳች ታሪካዊ ጊዜ ውስጥ የዕብራይስጥ ቋንቋ ማንሰራራትና እርሱን ለመቋቋምም ምን ያህል ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ የሕይወት ውስብስብነት ይታያል።
“በነፍሴ ውስጥ ለዕብራይሥጥ ቋንቋ የፍቅር እሣት ተቀጣጥሎ ብዙ የሕይወት ጎርፍ ውሃ ማጥፋት አልቻለም”
(ኤሊዔዘር ቤን ይሁዳ “ሃሐሎም ቭሢብሮ” ከተሠኘው – በቋንቋ ጉዳዮች ላይ የጽሑፍ ዓምድ ምርጫዎች ላይ)

 

የመጀመሪያው የዕብራይሥጥ ትምህርት ቤት
እ.ኤ.አ. በ1886 የትምህርት ቤቱ ህንፃ በሪሾን ለጽዮን ግዛት ውስጥ ተገንብቷል፤ በ1888 በመምህር ዴቪድ ዩዲሎቪች ተነሳሽነት ሁሉንም ትምህርቶች በዕብራይስጥ ቋንቋ ለማስተማር ተወሰነ። ስለዚህም በትምህርት ቤት ተማሪዎች አማካኝነት የዕብራይሥጥ ቋንቋ በግዛቱ ውስጥ በዕለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ ሥር ሰድዷል። የትምህርት ቤቱ መምህራን ለተማሪዎቹ የእሥራኤልን ምድር ፍቅር እንዲሰርጽ አድርገዋል። የዕብራይሥጥ መዝሙሮችን ያስተምሩና የመማሪያ መጽሐፍትን በዕብራይሥጥ ይጽፉ ነበር። ትምህርት ቤቱ አሁን “ቤት ሴፈር ሀቢብ” ይባላል።

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

כנרת

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025