דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

የከዋክብቱ ዛፍ

በ: ሊብ ሞርጀንቶይ ምሳሌዎች: ናዕማ ቤንዚማን

በአያት ጓሮ ውስጥ ፍሬ የማያፈራ ግን... ከዋክብት የሚወጡበት ድንቅ የሆነ ዛፍ ይበቅላል! እውነት ነው አያት ኮከቦችን መሸጥ አልቻለም። ነገር ግን አላዘነም፤ ምክንያቱም "ሀብቱ በእርሱ ዘንድ ስለሚኖርና ገንዘብ እነርሱ ጋር ስለሚሆን"። የከዋክብቱ ዛፍ በገንዘብ ስለማይገዙ ውድ ነገሮች ስለ አያትና ልጅ፣ ስለ ምናብ፣ ስለ ደስታና አስማታዊ ዘፈን ነው።

የእድሜ ክልል: መዋዕለ ሕጻናት

በዛፍ ላይ የሚያድግ ኮከብ አይተዋል? በታሪኩ ውስጥ ያለው አያት በግቢው ውስጥ ተአምራዊ ኮከብ የሚያድግ ዛፍ ይበቅላል። እነርሱን ሊሸጥ ወደ ከተማ ሲወርድ ሰዎቹ ምንም ፍላጎት አላሳዩም። አልፎ ተርፎም ይስቁበት ነበር። ይሁን እንጂ በደስታ ወደ ቤቱ ይመለስና ኮከቦቹን በእጅጌው ውስጥ ያስቀምጣል።
ምናባዊና አስማት በተሞላው ታሪክ ውስጥ፣ በቁሳዊና በመንፈሳዊ መካከል ስላለው ግንኙነት፣ ስለ እውነተኛ ሀብቶችና ዋጋቸው በገንዘብ ሊተመን የማይችል ውድ ነገር ከልጁ እይታ የሚያነቡ ተማሪዎች – በልቡ ውስጥ ብቻ ይሰማቸዋል።

”ከሃምሳ አመት በኋላ…የምታየው ነገር ሁሉ አይኖርም። ሌሎች ፈረሶች፣ ጋሪዎች፣ ሸቀጦችና ሌሎች ሰዎች… ሰማዩን ለማየት እንኳ ጊዜ እስክታጣ ድረስ ለምንድን ነው የደነገጥከው?”
(ራቢ አብራሃም ሐዛን፣ “ኮሐቬ ኦር” በራቢ ናሕማን ከብሬስሌቭ ስም)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

קרדיט: חוה אלברשטיין

ማተሚያ ቤት:

המבוך

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025