እናት ኢያሱን ከዶሮው ቤት እንቁላል እንዲያመጣ ትልከዋለች፤ ግን ውይ እንቁላሉ ተሰበረ! ኢያሱና እናቱ ተስፋ አይቆርጡም። በየቀኑ ኢያሱ ወደ ተግባር እየቀረበ ስለ ዓለምና እንዴት አንድ ሙሉ እንቁላል ወደ ቤት እንዴት ማምጣት እንደሚችሉ ትንሽ ተጨማሪ ይማራሉ። ስለ እምነትና ስለ ነፃነት የሚገልጽ በአስቂኝ ዘይቤ በሚገርም ምሳሌዎች የታጀበ ግጥም ታሪክ።
የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች
በየቀኑ ይሆሹዓ ከዶሮ እርባታ እንቁላል ለማግኘት ይሞክራል። እንቁላሉ ሲሰበር እናቱ ትክክለኛውን መንገድ እስኪያገኝ ድረስ መሞከሩን እንዲቀጥል ታበረታታዋለች። በቤት ውስጥ ሥራዎች መሣተፍ ይሆሹዓን እምነት እንዲጥል ያደርገዋል። ታዳጊዎች እንደገና በመሞከር ተግባራትን ማከናወን የሚማሩ ሲሆን እንደገና መውደቅና መነሳት ከአካባቢው የሚሰጠው ማበረታቻ በውድቀትና በመማር መካከል ያለውን ልዩነት በመፍጠር የብቃት ስሜትን ማዳበር ይችላል።
ብላቴናውን እንደ መንገዱ አስተምረው
(ምሣሌ 22:6)
ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ
ማተሚያ ቤት:
אגם
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ה 2024-2025