ዳዊት በፀጉሩ ላይ አበባ ያለው ልጅ ነው። አንድ ቀን የአበባው ቅጠል መውደቅ ጀመረና ጓደኛው አበቦቹን ወደ ጭንቅላቱ ለመመለስና በፊቱ ላይ ፈገግታን ለመመለስ ይሞክራል። ልዩ የሆነ ታሪክ፣ ለሌሎች ስሜታዊነትና ጥልቅ ጓደኝነት በስሱና ስሜት አዘል በሆኑ ቃላትና ምሥሎች ከፊታችን ቀርቧል።
የእድሜ ክልል: አንደኛ ክፍል
ዳዊት በፀጉር ፋንታ አበቦች አሉት። ሁሉም ይወዱታል በተለይም የቅርብ ጓደኛው ነገር ግን አንድ ቀን ዳዊት እንደ ቀድሞው እንዳልሆነ አስተዋለ። አበቦቹ ከጭንቅላቱ ላይ ሲወድቁ “እሾኻማና ደካማ” ይመስላል። በቅርብ ከሚቀረውና ለመርዳት ከሚሞክር የቅርብ ጓደኛው በስተቀር ሁሉም ከእርሱ ይርቃሉ። በእርሱ አነሳሽነት ሌሎች ጓደኞችም በመቀላቀል አንድ ላይ ሆነው ስለ እውነተኛ ጓደኝነት ኃይልና ሌላኛውን የሚያዩ ጥሩ ዓይኖች ያስተምሩናል።
ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወዳል። ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።
(መጽሃፈ ምሣሌ 17፡17)
ማተሚያ ቤት:
צלטנר
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ה 2024-2025