דילוג לתוכן המרכזי בעמוד

ספר החודש

አራቱ ሽላፍኖቼዎችና ድስቲቱ

በ: ኦሪ ኤሎን ምሳሌዎች: ምናሔም ሃልብርሽታት

"እንዲሁ ያለ ምንም ልዩ ጥረት አራቱ ሽላፉኖቼዎች ባሕሩ ውስጥ ይጓዛሉ" - ግን ወይኔ በድንገት በጀልባው ውስጥ አንድ ቀዳዳ ታየ! ሽላፉኖቼዎች ምን ያደርጉ ይሆን? ከአራቱ አንዱ ብልሃትን በማምጣት ችግሩን ይፈታ ይሆን? ስለ ግላዊና ማህበራዊ ሃላፊነት በቀልድ የተሞላ ታሪክ።

የእድሜ ክልል: አንደኛ ክፍል

አራቱ ሽላፍኖቼዎች በመርከባቸው ውስጥ ቀዳዳ እንዳለ ደርሰውበታል። በእውነቱ አንድ ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ሁኔታውን ለማስተካከል ምንም ጥረት አላደረጉም። በአስቂኝ ግጥም፣ ቀላልና አዝናኝ ታሪክ አማካኝነት እኛ አንባቢዎች ለትንሽ ጊዜ ቆም ብለን እንድናስብ ይፈቀድልናል፦ በየቀኑ በመርከባችን ውስጥ ያሉትን ‘ቀዳዳዎች’ እንዴት እናያቸዋለን? በድርጊቱስ ላይ ምንም ዓይነት የተለየ ጥረት ሳናደርግ አንድን ችግር ለመፍታት የምንሞክረው መቼ ነው? መቼ ነው ስለ እርሱ ብቻ ማውራት የምንመርጠው?

“ትንሽ ተናገር፤ ብዙ አድርግ”
(የአባቶች ምዕራፍ 1:15)

ታሪኩን ተከትሎ የሚመጣ ቪዲዮ

ማተሚያ ቤት:

כתר

የስርጭት ዓመት:

תשפ״ה 2024-2025