የባርላ አያት ለመጎብኘት መጥታ በዓለም ላይ ስላለው በጣም ጣፋጭ ኬክ ትናገራለች። ግን ኬኩ የት አለ? አያቱ ስትተኛ ባርላ በአያቱ ቅርጫት ውስጥ ባሉት ፍንጮች ፈልጎ መልሱን ያገኛል። እስከዚያ ድረስ እርሱና ወጣት አንባቢዎች ስለ ተለያዩ ዕቃዎች አጠቃቀም ብሎም ኬክ እንዴት እንደሚሠሩ ይማራሉ።
የእድሜ ክልል: ታዳጊዎች
“አንድ ላይ የመሆን ምትሐታዊ ጊዜያት –
አያት ባርላን ለመንከባከብ ስትመጣ ልዩ ጊዜ ያገኛሉ፤ የእነርሱ ብቻ። አያት ምናባዊና አስቂኝ ታሪኮችን ትናገራለች። በቅርጫቷም ውስጥ የተደበቁት አስደሳች ነገሮች ጣፋጭና አስገራሚ ይሆናሉ። በቤተሰብ ውስጥ በልጆችና በጎልማሶች መካከል ስላለው ግንኙነት ስለ ትንንሽ ጊዜዎችና የቅርብ ዘመዶች ይናገሩ፤ ይህም የዕድሜ ልክ ልምዶች ይሆናሉ።
.
በሽምግልና ጊዜ ጥበብ በዘመንስ ርዝመት ማስተዋል ይገኛል
(መጽሃፈ ኢዮብ 12 12 )”
ማተሚያ ቤት:
כתר
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ד 2023-2024