ትንሿ ሲምቺ በህንድ ውስጥ በኮቺን ውስጥ ትኖራለች። ነገር ግን የእስራኤል ምድር ህልም አላት። በኦሪት መደሰቻ በዓል ዋዜማ ወንድሟ ከአባቷ የዓሣ ማጥመጃ ጀልባዎች ውስጥ ሾልኮ ሲገባ ታያለች። ወደ እስራኤል በመርከብ እየሄደ ሊሆን ይችል ይሆን? ሲምቺ ከእርሱ ጋር ትቀላቀልና አብረው አስደንጋጭ ጀብዱ ውስጥ ያልፋሉ።
የእድሜ ክልል: ሁለተኛ ክፍል
“ተስፋችን፣ ወደ ሀገሪቱ የመመለስ የድሮው ዘመን ተስፋ … ገና አልከሰመም።
[ዜማ፣ ይስሃቅ ሞሼ ሮቢ፣ የኮቺን ማሕበረሰብ፣ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ]
የማወቅ ጉጉት ያላት ሲማቺ ወንድሟን ተከትላ ወደ አስደሳችና አደገኛ ጀብዱ ገባች። ይህ በወንድሞችና በደቡብ ምዕራብ ሕንድ ውስጥ በሚገኘው ጥንታዊ፣ ትንሽና ልዩ በሆነው የኮቺን የአይሁድ ማሕበረሰብ መካከል ስላለው ትስስር ላይ ያለ የአንዲት ትልቅ ሕልም ያላት ትንሽ ልጅ ታሪክ ነው። የሲማቺ ታሪክ እኛን አንባቢዎችን ከማሕበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤና የእስራኤልን ምድር ናፍቆት በጥቂቱ ያስታውቃል።
የኮቺን አይሁዶችን ታውቋቸዋላችሁ – የኮቺን አይሁዶች በህንድ ደቡብ ምዕራብ በኮቺን ግዛት በዛሬዋ የኬራላ ግዛት ይኖሩ ነበር። እንደ ትውፊት ማሕበረሰቡ የተመሰረተው በሰሎሞን ዘመነ መንግስት ሲሆን የሕልውናው ማስረጃ ከ1000 ዓ.ም ጀምሮ ተገኝቷል። ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የኮቺን አይሁዶች በስፔንና በፖርቹጋል በግዞት ከነበሩ አይሁዶች ብሎም ከሶርያ፣ የመንና ኢራቅ አይሁዶች ጋር ተቀላቅለዋል። የማሕበረሰቡ ሕይወት በአስደናቂው ምኩራቦች ዙሪያ ይካሄድ ነበር – እንደነዚህ ያሉት ዛሬ ላይ በሞሻቭ ናባቲምና በእስራኤል ሙዚየም ውስጥ ይታያሉ። ማሕበረሰቡ በዓለም ላይ ካሉ ሌሎች የአይሁድ ማሕበረሰቦች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የራሱን ስራዎች ማለትም በዕብራይስጥና በማላያላም ቋንቋዎች ግጥሞችን አዘጋጅቷል። እነዚህም በማሕበረሰቡ ሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፉ ነበር። መንግስት ለእነርሱ ያለው ትዕግስት ቢኖረውም አብዛኞቹ የኮቺን አይሁዶች ወደ እስራኤል ሃገር የሚያደርጉትን ዓሊያ ለመደገፍና የጽዮንን ናፍቆት ለማሟላት ንብረታቸውን ለመሸጥ መርጠዋል።”
ማተሚያ ቤት:
טל מאי
የስርጭት ዓመት:
תשפ״ד 2023-2024